የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤
የመፍትሄ መቋሚያ።
„የሥራው ሁሉና የነገር ግዳጅ መጀመሪያ ምክር ነው።“
መፅሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፲፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
23.08.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ
የፖለቲካ ስልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው።
ራስንም የማሸነፍ ልዩ አቅም ነው። ስለሆነም አመሰግነዎታለሁኝ።
- · መነሻ።
‘ለኢትዮጵያ ሕልውና አስጊ የሆኑ ድርጅቶች በመደመር ስም ያለ ቅድመ ሁኔታ መግባታቸው ያሰጋል’ – ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ
·
ወግ!
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ትናንት ማምሻ ላይ ይህን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩተኝ። እርግጥ
ነው ብዙም ደህና ስላልነበርኩኝ ምን እንደሚሰማኝ አልጻፍኩኝም። አሁን ትንሽ ልለት ፈለግኩኝ።
የለውጥ ተጋድሎ ሲጀመር
VOA የአማርኛው ክፈለ ጊዜ ከሁለት የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ያደረገው ውይይት ነበር። ሦስት ተከታታይ ውይይት ነበረው። ተወያዮቹ
ፕ/ ዳንኤል አበራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ ነበሩ።
በውይይቱ ላይ ያልተመቹኝ ነገሮች ስለነበሩ „መቋሚያ“ በሚል እርስ ሃሳቤን ገልጬ ነበር።
ከገለጽኩባቸው ነጥቦች አንዱ አቶ ያሬድ ጥበቡ በኢትዮጵያ
ግጭት አያሰጋኝም ስላሉ ነበር። እኔ ደግሞ ዕድለኛ ነዎት እንቅልፍ ተኝተው ማደር ችለዋል፤ እኔ ግን እጅግ ያሰጋኛል ብዬ
ሞግቻቸው ነበር።
ያልኩትም አልቀረም እስከ 2 ሚሊዮን ወገኖቻችችን መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን ከመፈናቅል
ጋር ተያያዥ የሆኑ እጅግ አሰቃቂ የወገን ሰቆቃ ደርሷል። እንግዲህ ያን ጊዜ ነው። አሁን ደግሞ ባለው „የመደመር ፖለቲካ“ ከነሙሉ
የተነሳበት ባህሪው ጋር ተፎካካሪዎች ወደ አገር እዬገቡ ነው። የስብዕናው ጉዳይም ታክሎ። ስለሆነም ከቀደመው በባሰ ሁኔታ የችግር ዝናብ አገሬ ላይ እንዳንዣባባ አያለሁኝ።
ለዚህ ሻለቃ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስ ጠንከር ያለ አስተያዬት ሰጥተዋል። እውነት በመሆኑ እኔም እጋራዋለሁኝ።
ቀደም ባለው ጊዜ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ተሽሎክሉኮ ነበር፤ አሁን ግን በአደባባይ ህዝብ
ግራቀኝ ተሰልፎ እያጨበጨበ ነው ኢ- ሰባዕዊ ድርጊት እዬተፈጸመ ያለው። ብትፈልገ ነገ ይሄን አደርጋለሁ፤ ነገም መጠበቅ ካላስፈለገኝ
ዛሬ አደረገዋለሁም እዬተሰማ ነው። በራሷ በመዲናዋ በዬጊዜው ተያዘ የሚባለው የመሳሪያ መጠነም የሚዘገንን ነው። እጅግ አስፈሪ ወቅት ናት
ኢትዮጵያ ያለችው።
ይሄ ቃለ ምልልስ ከህብር ራዲዮ ጋር የተደረገ ነው። ህብርን ዜናዎቹን ረጅም ጊዜ
በመደበኝ አዳምጠው ነበር። ነገር ግን ዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ የያዘው አቋም እና በፊት አስበው የነበረው
የገለልተኛነቱ አቋሙ ሊመጥንልኝ ስላልቻለ አቁሜው ቆይቻለሁኝ፤ ወደ አራት ወሬ ነው ካቆምኩት።
አክብሮቴ ቢኖርም ግን ጆሮዬን ልሰጠው አልፈቅድም ነበር። የመረጥኩት
ራዲዮ ባልጠበቅኩት አቋም ላይ ነው ብዬ ስለማምን። ትናንት ከአራት ወራት ዕቀባ በሆዋላ ነው ያዳመጥኩት። ጥሩ ቃለምልስ ነበር።
ሚዛናዊ ነበር። ያልወገነ ነበር። ወገንተኝነቱ ለኢትዮጵያ
ነበር ስለዚህም ነው ቀልቤን እንደ ቀደመው ሰጥቼ የተከታተልኩት። ዛሬም ደግሜ አዳመጥኩት።
እያንዳንዱ የተነሳው ነጥብ እና የተሰጠው መልስ በውስጤ ያለ ነው።
ይውደቅ የምለው አንዳችም ነገር የለም። እጅግ በርካታ ጉዳዮች ነው የተነሱበት። እንዳስብኩት ሻለቃ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስ
ከፖለቲካው አመራር ራሳቸውን ማግለላቸውን ሁሉ ፍንጭ አይቸበታለሁኝ። ትክክለኛ እርምጃም ነው።
ከእንግዲህ እነሱ በምክር አገልግሎት፤ በድጋፍ ሰጪነት ለማገልገል
መፈቀዳቸው እንደ ቅዱሱ ሐዋርያው ወንጌላዊው ቅዱስ ጳውሎስ „ይበቃኛልን“ ማወቅ ስለሆነ በአጋጣሚው ላመሰግናቸው እውዳለሁኝ። ከፖለቲካ ስልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው። ራስንም የማሸነፍ ልዩ አቅም ነው።
ደጋግመው ሲገልጹ እንደ ሰማሁን እኔ ከሳቸው ባለውቅም እያሉ ነው ጠ/
ሚር አብይ አህመድን ያሳሰቡት። እንደዛ የሚሉት በልምድ፤
በተመክሮ የደረጀ አቅም እያለቸው ማለት ነው። በሌላ በኩል እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት እና መልዕክት ይዞም ስለሚወለድ
የራሳቸው የእኔ የሚሉት ጸጋ እና ክህሎትም እንዳላቸው እኔ ሳልሆን ያለፉበት የትግል መስክም፤ እንደ ሰውም ሰው ሆኖ ከመፈጠር
ጋር የሚያመሳጠሩ ዕድምታዎች ይኖራሉ።
ትልቁ ነገር ትግል በቃኝ ሳይሉ እስከዚህች ጊዜ ድርስ የሚያምኑበትን
ዓላማ ሲያራምዱ ቆይተዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ሙሴ አገኘች ከሚል ይመስለኛል፤ ሃላፊነታቸውን የሚሸከም አመራር አለ ብለው ስላመኑ
ይመስለኛል እኛ በቃን ለወጣቶች ቦታውን መልቀቅ ግድ ይለናል ባይም ሆነዋል።
ይሄ መቼም በእኛ ፖለቲካ ያልተለመደ ስለሆነ እጅግ
ሊበረታቱ እና ጎሽ ሊባሉ ይገባቸዋል ባይ ነኝ። ደፋር ጀግናም እርምጃ ነው። „ይበቃኛል“
ከዘመኑ ሁሉ የታደሉበት የምለውም ይህን ቃል ከአንደበታቸው ያወጡባት የትናንቷ የነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ናት።
በፈረንጆቹ 22.08.2018 ብሩክ ማዕልት ናት።
አብሶ ኢትዮጵያ ከ66ቱ ፍልስፍና እና ተያያዥ ችግሮች መላቀቅ
የምትችለው የዛ ጸበለጻዲቅ ተጠማቂ ከሆኑ ነፍሶች ፖለቲካዋ ሲወጣ ብቻ ነው ብዬ አምናለሁኝ። የሁሉም የችግር ምንጭ ያ
የሶሻሊዝም ንድፈሃሳብ እና መዘዙ ስለሆነ። ቅርጹ ቢለያይም ይዘቱ ዛሬም ያው ነው፤ በሁሉም ቦታ ያሉ የሃሳብ ግጭቶች፤ የሃሳብ
ጦርንቶች፤ የሃሳብ ጉግሶች የዛ ጥሪት ውጤቶች ናቸው።
ዘረ ሾሻሊዝም ለዬዘመኑም የተስፋም ይሁን ራዕይ ጽላት የጉሮሮ አጥንት
ነው። የዕድሜ ክፍተት ችግር ብቻ ሳይሆን የጽንሰ ሃሳብ ችግሩ የገዳለ ገደሉ ምንጩ ይሄው ነው። ስለዚህ ከዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ወጥተው በነፃ
መንፈስ ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል አድርገው መንፈሳቸውን ሊለግሱ የተነሱበት መንገድ እና የደረሱበት ውሳኔ ለእኔ ተምችቶኛል። ስለሆነም ነው እኔ ደግሜ ላደምጠው የወደድኩት።
በተጨማሪም ብሎጌ ላይ ልለጥፈው የወደድኩት።
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋንም ላዳምጠው የወደድኩት በዚህ መስመር ነው።
እርግጥ ነው ከህብር ጋር ብለያዬም ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳን ግን አዳምጠው ነበር። ለዬት ያሉ፤ ያልተደጋገሙ፤ ይለተገነኑ፤ ቅጂ
ያልሆኑ አብሶ በኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዕላዊነት ያለው የማይናወጽ አቋሙ እምነቴ ሙሉ ስለሆነ ልዩ ትንታኔዎቹን አዳምጥም
ነበር። ስለዚህ በከፊል ታዳሚ ነበርኩኝ። በተለመደው ሁኔታ ቀልቤ ሙሉ ባይሆንም ከህብር ጋር ግን በታሜ ትንታኔ አልተጨከነም እንደ
ማለት።
- · የመፍትሄ መቋሚያው።
የነበረው ችግር አሁን የሚፈጠረው ችግር ነገ ያለቀድናቸው ችግሮች እና
የአብይ ካቢኔ ምን እና ምን? እንዴት እና እንዴት ይቀጥሉ? መተንበይ አይቻልም።
እርግጥ ነው ሻ/ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ያነሷቸው አመክንዮዎች ፍሬ
ሃሳቦች አድማጭ ካገኙ በተወሰነ ደረጃ ችግሮችን የመቋቋም አቅም ማመንጨት የሚቻል ይመስለኛል።
አሁን ባለው ዝርግ ፖለቲካ ግን አሁንም እንቅልፍ የሚነሱ አደጋዎች ይታዩኛል። የመቆጣጠሪ ስልቱና፤
ለመቆጣጠር የሚዘረጉ መንግሥታዊ ስልቶች ማዕከላዊ አቅማቸው እጅግ አሳሳቢ ነው። እራሱም በግንባር ድርጅቶች ያሉ ኢጓዊ አመክንዮዎች በራሳቸው የችግር መደበሮች ናቸው። አንድ የአገር የወገን ኮከብ የሆነ ባተሌ ማህል
አዲስ አበባ ላይ በጠራራ ጸሐይ ተገድሎ መንግሥት እያለ፤ ክልሎችም እያዬዩ እዬሰሙ፤ አዲስ አባባም አስተዳደር እያላት ምንም አለመባሉ በራሱ አሁን ያለው የአብይ ካቢኔ ምን ችግር ገጠመው
እንድንል ግድ ይለናል?
ይህን ሃቅ ወደ ውስጥ ገብተን በሚዛን ስናስቀምጠው የአብይ መንፈስ
በቀደመው የራስ መተማምኑ ውስጥ ነው ወይ ያለው ያሰኛል? በወንጀሎች ማጋለጥ ውስጥ እርግጠኛ የማያደርጉ፤ ደፍሮ እርምጃ ለመውሰድ
የሚያግዱ ነገሮች የቅድመ ሁኔታዎች እስር እንዳሉ ምልክት አለ?
ቀደም በለው ጊዜ ፍቅርን በመስጠት እና በመቀበል በነበሩ የጊዜ
ውርርሶች፤ የጊዜ ቅደም ተከተሎች፤ የጊዜ አቅርቦት እና የፍላጎት አለመመጣጠን የፍላጎት ግሽበት
ተመልክተናል። አሁንም
ካቢኔው ወንጀሎኞችን መቆጣጠር ሳይሆን ማስተማም የፈገበት ምክንያት የዙር ታሪክ አለመድገም ፍላጎት ስለመሆኑ የወል ስምምነት
ነበር። ስንበቃቀል መኖር ይቁም ስለነበር መርሁ፤ ያ ግን ችግሩን አባባሰው፤ ለውጡን አፈነው እንጂ፤ ለውጡ ስሞታ እንዲበዛበት
አደረገው እንጂ የመፍትሄ ቀለበቱን ኪዳናዊ ሊያደርገለት አልቻለም።
አሁን ቁልፉ ጥያቄ ቀጣይ ቀውሶች ቀጣይ መሆናቸው ነው። „አያያዙን
አይቶ ሸክሙን ይቀሙታል“ እንዲሉ ስለሆነ ቀጣዮችን ቀውሶች የአብይ ካቤኔ በምን ሁኔታ ሊያስተዳድራቸው አስቧል ነው? ምን
አልባት የሰሞናቱ የግንባሩ ስብሰባ አንድ ማሰሪያ አበጅቶለት ከሆነ መልካም ነው።
በስተቀር ግን ስንት መንግሥት እንዳላት ኢትዮጵያ ግር እስኪል ድርስ ዝብርቅርቅ ያለ ዝንቅ ሁኔታ ነው ያለው። ይህ መቼም አሊ አይባልም።
አብሶ የኦብነግ እና በበርካታ ቅርንጨፍ ላይ የተመሰረተው የኦነግ ጉዳይ
እንዲህ እንቅልፍ የሚያስተኛ አይደለም እንደ መሪ እንደ ሙሴ ሲታይ። ፈተና ብቻውን ሳይሆን ፈታይም ነው። ገማጂም ነው።
የአብይ ካቢኔ ሙሉ ለሙሉ በመንፈሱ አቅም ልክ መሬት ላይ መዋቅራዊ
ሰንሰለቱን ለመምራት ሁሉም በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ መዳፍ ላይ ቢኖር ተስፋ ሰጪ ነገሮችን ማሰብ ይቻል ነበር። እንደማዬው ግን
ጥገናዊ ለውጡን ለማስቀጠል እንኳን በተደራጀ የሽፍታ ቡድን፤ በተፈቀደለት መንፈስ አፍራሽ ቡድን፤ በቀደመው ሥልጣን ቀረብኝ
በሚለው አውራ ፓርቲ በወያኔ ሃርነት ትግራይ በኩል ያለው አሉታዊ ዕድምታ፤ እንደ መረብ እርስ በርሱ የተተበተቡ ጉዳዮች
አሉበት። ራሱ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መርህ ሴራ - ሸር ምቅኝነት የሥልጣን ቅጥ መጠኑ የጠፋ ሱሰኝነት ነው።
አንድ በተወሰነ ደረጃ ነፍስ የሚያሳርፍ ነገር ቢኖር ከኤርትራ ጋር
የተመሠረተው ግንኙነት ብቻ ነው። የሱማሌው፤ የጁቡቲ የሱዳኑ የግብጽ ጥረት ተድርጓል ግን ቀን ጠበቂ ችግሮች ጋር ተቃቅፎ ነው።
የኤርትራም ቢሆንም አሁን ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር ያለው ሁኔታ
በራሱ የሚጭረው የሃሳብ ተፋሰስ አለው። ከ ኦህዴድ ጋርም በምን ሁኔታ እንደነበረ የሚታወቅ ነገር የለም። አማራ ሆነ ኦሮምያ ክልል ሉዕላዊ ናችሁም ነህም እዬተባሉ ነው። በፖለቲካ ትርጓሜ ሲቃና።
ከዚህ አንፃር ሳዬው የሻለቃ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስ ትንተና እና ጭብጥ
ካዳመጡት ለዶር አብይ አህመድ እጅግ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ለሳቸው ብቻም ሳይሆን በዚህ በለውጡ መንፈስ ላይ ለተጠመደው
ሚሊዮን ኢትዮጵውያንም ተስፋም እጅግ አቅጣጫ አመልካች እና ፍንጭ ሰጪ ነው። ጠቃሚም ነው።
በሌላ በኩል ሽግግር ላይ ስላለን ለሚለው ሽግግሩ ያስደሰተን ሰላማዊ ነው በሚል ነበር። ነገር ግን አሁን ሰላማዊ
ነው ለማለት አያስደፍርም። ቀዝቃዘቀው ጦርነት በኢትዮጵያ ማለት እችላለሁኝ። ስንት መሪ ነው አሁን ያለን?
ምን ያልሆነ ምን ያልተደመጠ ኢ- ስብአዊ ድርጊት አለና። ጠ/ ሚሩ
ከመግደል ጀምሮ ያሉት እውነታዎች እና አሁን ያለው ደመናም አዬር በራሱ ሹክ የሚለው ብዙ ነገር አለ። በዚህ ውስጥ መታመን
እና ታማኝነት፤ መቻል እና አክብሮተ፤ ትህትና እና ቸርነት አደጋ ላይ ነው ብዬ አስባለሁኝ። መቼም በዚህ እኔ በርቀት በሚታዬኝ ሁኔታ ውስጥ
ዶር አብይ አህመድ ተስፋ ያደረጉት፤ ያመኑት፤ የጽናቴ ልዕልና ያሉትን ከሰሜን አሜሪካ መልስ እንዳጡት አስባለሁኝ።
ይህ መቼም ምን ያህል አጥንት እንደሚተረትር እኔ በዚህች ምስኪኔታ
ህይወቴ የገጠሙኝ ብቻ ሳይሆን ተነጥዬ እንድኖር ያደረገኝ አመክንዮ ነው። እሳቸው ግን የሚሊዮን ሙሴ ስለሆኑ ከነ ስብራቱ፤ ከእነ ቁስለቱ መቀጠል ግድ ይላቸዋል። የህዝብ የተስፋ ጽላት ስለሆኑ። ልጅ ያላት እናት ቢያማት ሽብልል ብላ ህመሟን ማስታመም
አትችልም።
የእኔ ቢጤ ተማላ ግን ሲያመው ጥቅልል ብሎ ተኝቶ ያሳልፈዋል። አሁን
ዶር አብይ አህመድ የሚሊዮን የተስፋ እናት ናቸው። ስለዚህ በቃህኝ፤ በቃችሁኝ ብለው እርግፍ አድርገው የማይተውት የሚልዮን
የፍቅር አደራ ዕዳ አለባቸው። ስለሆነም እስከ ቻሉ ድረስ መግፋታቸው አይቀሬ ነው።
አንድ የሚያጽናናኝ የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ድዋ ከአዲሱ ለውጥ ቅዱስ መንፈስ ጋር መሆኑ ብቻ ነው እንጂ ልብ የሚያስጥል ነገር የለም። መካዳቸውን አስተርጓሚ አያስፈልግም። መጠራቅቅ ውስጥ እንዳሉም
እንዲሁ … "የመንታ እናት ተነጋለ ሞተች" እንዲሉ ነው ...
ሌላው ግን የሰብዕዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት ዝም በሉ፤ የአብይን
ካቢኔ አታሳጡት የሚለው ጅልነት ነው። አንደኛ እሳቸው ቆንጥጡኝ ብለዋል፤ ሁለተኛም የሳቸውን ካቢኔ ለሚያውኩት ተጨማሪ ጉልበት
ይሰጣል ዝም በተባለ ቁጥር፤ ሦስተኛ ጠ/ ሚር አብይ ያሉበትንም ሁኔታ በውነቱ አናውቀውም። ድፍን ያሉ ነገሮች አሉበት።
እውን ኦህዴድ እዬደመቁ ሲመጡ፤ እዬጎሉ ሲታዩ፤ ኢትዮጵያዊነትን
ሲያደምቁ፤ የዓለም ሚዲያ አምደኛ ሲሆኑ ከሳቸው ጋር ነበርን? አሁንስ አለን ብሎ ለመናገር የማያስደፍሩ ምልክቶች አሉን?
ኦህዴድ አኮ አዲስ ጠ/ ሚር ሾሟልን ነበር አቤቶ ጃዋር መሃመድን።
ካቢኔም አለው። ኦነግም ዓርማውን አዲስ አባባ ላይ በፍንደቃ አውለበለበለን እኮ። ብሄራዊ ሰንደቅዓላማውም አጀንዳ ሊሆን አይገባም ድፍረትም አለ። አሁን እኔ እንደማስበው ይህም የመከራ ዘመን
እንዲሸከም የሚፈለገው የአማራ ክልል ነው እንደ ተለመደው በኢትዮጵያዊነት ጫና።
ለዚህ ነው በላይ በላይ አንዱም ነገር ሳይከውን አማራ መሰረታዊ ጥያቄዎችን
በሚያዘናጉ የጫን ተደል የቤት ሥራዎች እንዲወጠር የተፈለገበት ሁኔታ። ተጋድሎው እውቅና ተነስቶ ግን በግዳጅ ጥድፊያ ላይ ያለው። ሌላ ቦታ የመንፈስ ራፊ ለማግኘት እሳት ረመጥ ሆኗል።
አማራ የቀደመውን የአባቶቹን ሌጋሲ ያስፈጽም የሚል የግዴታ ካቴን በመንፈሱ ላይ
የተጣለ ይመስለኛል። ለዚህ ደግሞ ሚናውን እንዲወጣ አቤቶ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተግተውበታል ብዬ አስባለሁኝ።
ይህ መስመር ብቻውን ግን የ100 ሚሊዮን ህዝብ መከራ ተሸክሞ
ለሚፈለገው ግብ ያደርሳል ተብሎ አይገመትም። ይህን ነጥብ ማንም ሰው ላያነሳው ይችላል። አውቆም ይሁን ሳያውቅ ግን ያለው
ዕውነት የሚነግረን ይሄው ነው።
27 ዓመት በጨለማ ውስጥ የኖረን ማህበረስ አሁን ደግሞ ለሌላው ብርሃን ጎብጠህ፤ ዘግጠህ
ተሸክመህ አሻግር ነው ብይኑ … እኔ የማዬው ይሄውን ነው …. ሌላ ቦታ የሚጫንበት የቤት ሥራ የለም። ስለዚህም በራሱ ጥያቄ
አመላልስ ላይ ተግቷል። ነፃነትም አለው። አማራ ላይ ግን የብሄራዊ መንግሥት ተግባር ከውን ነው ሂደቱ ሁሉ የሚያመልክቱት። ይህን ግን ሻ/ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ አላነሱትም። እኔ ግን ማንሳት እችላለሁኝ። ግልጥነት ብቻ ነው መፍትሄ ማመንጭት የሚችለው።
እርግጥ ነው ወስብስብ ክድን ትይንቶቹ ብስለትን፤ ስክነትን፤ እርጋታን ይጠይቃሉ። ዛሬ
ያልታረሙ ነገሮች ነገ የመርዝ ቋት ስለመሆናቸው አዋቂ ቤት መሄድ አያስፈልግም፤ ስለሆነም የሚታዩ ግድፈቶች እና ስህተቶች ዝም
ባይባሉ ምርጫዬ ነው።
ነገር ግን ሁሉንም ጫና ደግሞ ዶር አብይ አህመድ ላይ ሳይሆን ሁሉም
የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። አንድ ዕጣ ነፍስ፤ አንድ ዕጣ መንፈስ የፈለገ አቅም ቢኖረውም ይህን ወዘተረፍ ችግር ብቻውን ተሸክሞ
ሊያሻግር አይችልም። በዬሰከንዱ እኮ እንደ ኤሌክተሪክ የእንቁላል ማሽን ችግር ፈልፋይ ሆኗል።
ሁሉም ሳዬው የራሱን የማንፌስቶ ክብር እና ልዕልና ለማዝለቅ እንጂ
የህዝቡን ተስፋ በማስቀጠል ከእኔ ምን ይጠበቃል ሲል አልሰማሁኝም፤ አላዬሁኝም። እኛን ይወቅሱናል ነው። ይወቅሱናል ማለትም
እራሱ ተናጋሪው ይህን ሲል ሌላውን እዬወቀስ ስለመሆኑ አያገናዝበውም።
በሌላ በኩልም ወያኔ ላይ አተኩሩ የሚልም አባባል አለ። ምን አሁን
ወያኔ ብቻ ሳይሆን መሰሉን የሚከውነውም ያውን ከደገመው ምኑን ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ተሻለና ማፈን፤ መጫን፤ ማግለል፤
ማጠልሽት፤ አቅም መሰንጠቅ፤ ማጣጣል፤ ራስን ከፍ ማድረግ ከሆነ ነገም ያው ነው …
ስለዚህ
ራስን ማረም ነው መፍትሄ ሊሆን የሚችለው … ለዚህ መቼም ማርከሻ የሆኑ ጭብጦችን ሻለቃው አንስተዋል። ወቅታዊ ነው፤ ተደማጭም
ነው። መፍትሄ አምንጭም ነው ለእኔ ….
በትንሹም በትልቁም ሟርት እዬተፈለገ የአብይ ካቢኔ አይብጠልጠል ነው
እንጂ ክፍተቱን ማመላከት፤ ግድፈት ሲኖርም ኢትዮ ጨዋነትን ተላብሶ መተቸት መቀጠልም መለመድም ያለበት ጉዳይ ነው።
ማንም ከቁጥር ባላስገባቸው ሰዓት ነበር እኔ ስለ ዶር አብይ አህመድ
የታገልኩት፤ እንደ እኔም የሞገት የለም ለአብይ ንጹህ መንፈስ፤ ለራሱ
ለኦህዴድም ፤ ሳተናውም በጣም በትጋት ነበር የሰራው።
ግን ሳይመቸኝ የሚቀረውን ደግሞ በአለባሶ ልሂደበት አላልኩኝም። አብይ
ሆይን በተጨማሪነትም ርትህን 7 ክፍል ላይ ማንበብ ነው አፋር የመጨረሻው ክልል ስለነበር በዛ ላይ ሰፊ ነገሮችን አንስቼለሁኝ።
የተሰማኝን ግልጥልጥ አድርጌ ምንም ሳላስቀር በግልጽ ሞግቻለሁኝ። ወደፊትም ዶር አብይ አህመድ አቅም አላቸው፤ ሃይል አላቸው ብዬ ሳስብ
ሙግቴ ይቀጥላል። አሁን ግን እንደ አጀማመራቸው ከአቅማቸው ጋር ናቸው ብዬ ስላማላስብ ግዴታም ሙግትም ክርክርም ላቀርብባቸው
አልችልም።
ለምሳሌ የኦነግ አርማ በአፍሪካ መዲና አዲስ አባባ ላይ በድል ርካብ ሆኖ ሲውለበለብ
እሳቸው የማይችሉበት ወቅት ላይ እንደ ነበሩ አስባለሁኝ። ወይንም ኦህዴድ በቅደመ ሁኔታ አስሯቸዋል። የአቤቱ ጃዋር መሃመድ ፉከራ እና ቀረርቶ በተደመጠበት ሰሞናትም
እሳቸው ነበሩ ብዬ አላስብም።
አሁንም ልሞግታቸው እማስበው በሙሉ አቅማቸው መንቀሳቀስ መጀመራቸውን ሳረጋግጥ ብቻ
ነው። አሁን እኔ ከሙሉ ሥልጣን ጋር ናቸው ብዬ ማሰብ አልችልም።
ቅድመ ሁኔታ ቀርቦላቸዋል በድርጅታቸው በኦህዴድ ውስጥ ብዬ አስባለሁኝ። ሌላም ቅድመ
ሁኔታ አለባቸው እኛ በማናውቀው አካል። ሥርዓተ አልበኝነቱ የመጣው በዚህ ነው።
ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ተወቃሺም ተነቃሽም አሁን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ
ናቸው ብዬ አላስብም። የራሳቸው ድርጅት ኦህዴድ ራሱ ፈተና እንደ ጫነባቸው ነው እኔ እማስበው። ይሄ ለሌላው ላይገለጥ ይችላል፤
ወይንም እንቶ ፈንቶ ሊመስል ይችላል፤ ግን መንፈሳቸው በግራ በቀኝ ውጥረት ውስጥ እንደሆነ ይሰማኛል - ለእኔ። ስለሆነም አቅሜ ጸሎት ነው እና እጸልይላቸዋለሁኝ።
አብይ ሙሉ ነፃነቱን ተቀምቷል ብዬ አስባለሁኝ። በልክ ሁን ተብለዋል። የወጡበት ድርጅት በልክ እንዲጓዙ ያደረጋቸው አመክንዮች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁኝ።
የአብይ መንፈስ የልቅና ሌጋሲ ተቀባይነት ለኦህዴድ ምቾት የሰጠው አይመስልም። በሌላ በኩል ለ ኦህዴድ የአማራ ብሄርተኝነትም ቢሆን እንዲሁ
ስላሰጋው ጫናው እዛ ላይ እንዲሆን አቅዶ እዬሠራበት ነው። መሪው ፓርቲ እሱ ነውና። መሪው ፓርቲ ስል በድምጽ ብልጫ ኦህዴድ
ውስጥ አቅሙን ስትመዝኑት አሁን ባለው የነገሮች ሽክርክሪት የትኛው ሚዛን እንደደፋ አመላካች ጨረሮች አሉ አነግውያን መንፈሶች አና ያሉ ይመስላሉ።
ለዚህ
ለራሱም መዳን ሲል ወያኔ ሃርነት ትግራይ የለውጡ ሙሉ ለሙሉ አካል ከሆነ ብቻ በዬድርጅቶች ያበጡ ነገሮችን፤ ያፈነገጡ
ሁኔታዎችን መቆጣጠር ይቻላል ያፈነገጡ አመክንዮዎች በአብይ ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል። ለራሱ ለግንባሩ ለነገሩ ግንባሩ አለ ለማለት አያችልም ቢሆንም ግን ወሳኙ ጉዳይ አብይን ከሚያስሩ ነገሮች ውጪ በነፃ መንፈሱ ማስቀጠል ሲቻል ብቻ ነው። በስተቀር አደጋው መጠነ ሰፊ ነው>...
የሚታዬው ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላይ አብዮታዊ ዴሞክራሲን እናስቀጥል ነው። ይህ
የማይሆን ነው።
የትኛውም ኢትዮጵያዊ መንፈስ ለዚህ አጀንዳ ቀጣይነት አይተጋም። ወያኔ
ሃርነት ትግራይ አውራ ፓርቲነቱ እንደ ተቀበረ መቀበል አለበት። ግን በአብይ መንፈስ ታላቅ ስጦታ አግኝቷል። በደሉን እርሱለት ተብሎለታል።
ይህ ታላቅ ዘመቻው ሞቶ ነበር የዶር አብይ አህመድ። ይህ ደግሞ ጠቃሚው ለነተጋሩ ነው።
ለዚህም ነው ተለይቶ በደል የደረሰበት የለም የሚሉትን የተፎካከሪ ፓርቲዎች አጀንዳ ወራሽ እሳቸውም የሆኑት። ይህን አጀንዳ እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ደግሞ ማን ሊሆን ይችላል? ይህ ሃሳብ ከመቼ ዕለት ጀምሮ
ለሚለው ጉዳያችን ለሆን ነፍሶች አይጠፋንም። ያው መቻቻል በሚበላው ቅጥብጥርሶ ቀጨር መጨሬ ገሸሼ እናድርገው እንጂ እውነቱ ከአንድ ዕጣ
ነፍስ ውጪ አያደለም … መርዞች መርጫ ካገኙ ... ሰከንዷን ይጠቀሙበታል።
- · ነፍሱና ኦህዴድ፤ ተስፋችን እና ኦህዴድ።
ኦህዴድን ካማኑት ሞኞች መካካል ዋንኛዋ እኔው ነው ነኝ። ስለምን?
በዶር አብይ አህመድ እና በዶር ለማ መገርሳ እምነቴ ሙሉ ስለነበር። ከእነሱ ያፈነገጠ መንፈስ ሊኖር እንደሚችል ባስብም
በዚህን ያህል መጠን ይሆናል የሚል ግን አልነበረም። አሁን ኦህዴድ በተገለበጠ አጀንዳ ላይ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው።
ሌላ ተስፋ ያለው የደቡብ ህዝቦች ነው። በዚህ ዙሪያም ያለው ውስጠት እና ፍንዳታው ያዬነውን አይተናል።
በጥቅሉ ሲታይ ለውጡን ባስበነው ልክ መጠበቅ የምንችልበት ሁኔታ ላይ
አለን ብዬ አላምንም። ለውጡም አይቀለበስም ብዬ አላምንም። ተቋማዊ ስላልሆነ ባለሰብነው ወቅት እና ሁኔታ አቅም ያለው ሃይል
ሊቀለብሰው ይችላል። የዶር አብይ አህመድ ታማኝነት እና ለዘመኑ የማይምጥን ብቃት እና ቸርነት በራሱ ካልታጋዘ፤ ካለተደገፈ
መዋቅራዊ መሠረት ለመጣል ካልደፈረ ምኞት ብቻ ሆኖ፤ የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው።
ምዕራፍ አንድ ላይ ያዬናቸው ብርቱ ተግባራትን በምዕራፍ ሁለት
ለማስቀጠል ምዕራፍ አንድ ተጠናቆ ምዕራፍ ሁለት ለመግባት ሽግግር ላይ አያለ ነው ችግር የገጠመው። "በሽታውን ያልተነገረ
መዳህኒት አያገኝም" ሆኖ ተከድኗል። መጽሐፉም ዝም ቄሱም ዝም ሆኗል። የሚጋለጠው የውጪ ገማና ሲሆን ነው። የውስጥህ፤ የራስህ
ገመና ከሆነ የውሽማ ሞት ነው የሚሆነው። ጭጭ።
በምዕራፍ አንድና በምዕራፍ ሁለት መሃከል ሽግግር ላይ የተፈጠረው
ችግር ሳይፈታ ነው ምዕራፍ ሁለት የተጀመረው። ምዕራፍ አንድን የደገፉ ነፍሶች በተለይም ዘግይተው ነበር። ቀድመው ቢሆኑ ኖሮ ብዙ ነገሮችን ማሸነፍ ይቻል ነበር። የለውጥ ፈላጊው መንፈስ የህሊና መሰናዷቸውም
ያን ያህል ስለነበረ የውጪ እና የውስጡ አቅም ሃዲድ ተሰርቶለት ምዕራፍ ሁለትን ለመጀመር የሚያስችሉ ፈርታይል የሆኑ መንፈሶች
መዳፍ ላይ እያሉ ነው የውሽማ ሞቱ የተከሰተው።
ታስታውሱ እንደሆነ ቅኖቹ ታዳሚዎቼ ምዕራፍ አንድ ያን ያህል ወጀብ እና
በረድ ቢበዛበትም የአብይ መንፈስ ሙሉ ነጻነት፤ ሙሉ አቅሙን ኦህዴድ ይቀልበው ስለነበር ሁሉንም ተቋቁሞ በ10 ዓመት
የማይታሰቡ የብርሃን ወገገኖችን አቃንቶልናል። ያን ጊዜ ተሰውረው ሲደራጁ የነበሩ ሃይሎች በዛ ሞገድ ሥር ነበሩ፤ አሁን ግን
አይመስለኝም።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላይ ብቻ ሳይሆን በግንባሩ ውስጥ ባሉ ድርጅቶችም
ውስጥ በተለይም እሳቸውን ለዚህ ሃላፊነት ባጫቸው ኦህዴድ መንፈሱ ዛሬ ላይ ወጣ ገባ ሆነ ይሰማኛል። አብሶ ተፎካካሪዎቹ
ከመዋጣቸው በፊት የአብይ ሌጋሲን መንገዱን ጥበቃ ሊያደርጉለት
ይገባል። በስተቀር ለሁሉም ሳይሆን ይቀራል።
ለዚህ ብልህነት ይህ የሻለቃ ዳዊት ወ/ ጊዮርጊስ ቃለ ምልልስ የልብ
አድርስ ነው - ለእኔ። እርግጥ ነው እሳቸው ያመላከቷቸውን መስመሮች ላይ ለመትጋት አሁን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከነበራቸው የሥልጣን
አቅም ላይ፤ ሙሉ በራስ የመተመማን የማድረግ አቅም ናቸው ወይ? አንኳሩ ጥያቄ ይሄ ነው። እኔ አይመስሉኝም ነው የምለው። አቅም አላቸው፤ ግን እማቸውን ወደ ተግባር እንዳያሸጋጋሩት የውሻ ሞቱ ማዕቀብ ጥሏል።
አይናገሩት ነገር አልተፈቀደም፤ ዝም አይሉት ነገር በተሰጣቸው የግዳጅ መስመር መሄድ ግድ ብሏቸዋል። ማሰበብ የሚፈለገው ደግሞ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ላይ ነው። ሌላውን መንካት ጦሱ ከምናስበው በላይ ነው። የሰጠነህ ስልጣን በዚህ ልክ ብቻ ነው ... ነው ነገርዬው ...
የዋህ ህዝብ አዋቂም ሊቅም የሚባለውም ይህን ፍሬ ነገር ገፍቶ ሊሄድበት አልተቻለውም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ የለዬለት ነው። ያለዬ ጉሽ ነገር አለ በራሱ ውስጠት። እሱን ነው ብልህነት ያላገኘው ነገር እምለው። ቀዝቃዛው ጦርነት እምለውም ይህንኑ ነው። ይህን ሚሰጢር ደግሞ መቼውንም ቢሆን አያወጧትም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ። ንፁሃን ነፍሳት ድርድር አለበትና።
ኦህዴድ በሳቸው የአቅም ሙሉነት፤ የተቀባይነት ከፍታ፤ የእኔ የራሴ
የድርጅቴ ብሎ ስለመቀበሉ፤ አክብሮትም ስለመስጠቱ፤ የድርጅቱን ሁለገብ ብቃት ስላመመስከሩ፤ ዕውቅና ለግሶታል ወይ ለሚለው ለእኔ
እእ ነው። ወይንም አይ ነው።
አይ አንድ የታገድሎ አንባ ነው … ከታውቀበት ወደ ይሁንታ ለመስቀዬር ይቻለዋል፤
ግን ከወረቅተ አምልኮት ከተወጣ ብቻ ነው። የሚታዬው ጥሬ የጽዋ ማህበርተኝነት ነው …
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ቸር ወሬ ያሰማን።፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ