ልጥፎች

ከኖቬምበር 13, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ተስፋ ሰጪ ዜና WHO ምስጉን ተግባር ፈጸመ። (ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።)

ምስል
  ተስፋ ሰጪ ዜና ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     እንዲህ ፈጣን እና የተደራጄ የርህርህና እርምጃ ተስፋ ይሰጣል። ያጽናናል። አይዟችሁን በአጽህኖትም ይልካል። ተመስገን። «አስቸኳይ ዜና!»    «በደቡብ ኢትዮጵያ በቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ፈጣን ምላሽ ሰጠ!   የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠረጠረ የቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ ዙሪያ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።»   «የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች በቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።   WHO ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት አስቀድሞ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦   1. ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለጤና ሰራተኞች የሚሆን የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE) ወደ ተጎዱ ከተሞች ተልኳል።   2. በወረርሽኙ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ንክኪን የመከታተል (Contact Tracing) ሥራን ድርጅቱ ይደግፋል።   3. ሊኖር የሚችለውን ድንበር ዘለል ስርጭት ለመከላከል ከደቡብ ሱዳን WHO ቢሮ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።   4. የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት፣ ለአስቸኳይ ድጋፍ እንዲውል 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ከWHO የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለኢትዮጵያ ተለቋል። ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፉን ...

ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር // ሚር ክብርት #ዶር #መቅደስ #ዳባ። አዲስ አበባ።

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር // ሚር ክብርት  #ዶር #መቅደስ #ዳባ ።   አዲስ አበባ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #መቅድም ።    ጤና ይስጥልኝ ክብርት ዶር መቅደስ ዳባ እንዴት ሰነበቱ። ዕንቅልፍ አጥቼ ያደርኩበትን ውስጤን ልልክለወት እንሆ ወሰንኩኝ። ትናንት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር ያወጣውን መግለጫ ከፌስቡክ ፔጁ ላይ አግኝቼ ደጋግሜ አንብቤዋለሁኝ። በአሉኝ የማህበራዊ ሚዲያወች እና ኢሜሎቼም ተጠቅሜ ሼር አድርጌዋለሁኝ። እንዲህ አይነት ድንገተኛ እና አጣዳፊ ሥም አልቦሽ ወረርሽኝ ሲገጥም ከፍጥነት ጋር እርምጃ ለመውሰድ የተደረገ ንቅናቄ መኖሩን አረጋግጫለሁኝ። እርግጥ ነው በግንባር ቀደምትነት ለተሰውት የጤና ባለሙያወች መግለጫው ምንም ያለው ነገር የለም የሚል ቅሬታም አንብቤያለሁኝ። በመግለጫው ላይ ሰመዓታቱን ባልደረቦቹን የጤና ሚር አስቦ ቢሆን ቀጣዩን የገዘፈ ፈተና ለመቋቋም አቅምን በቅንነት ለማሰባሰብ ሆነ በተስፋ እነኛ ንጹኃን የህክምና ባለሙያወች ይሠሩ ዘንድ ይረዳቸዋል። ባለሙያወቹ በተቋማቸው ላይም ሙሉ ዕምነት አሳድረው #አለኝታችን የእኛነት ስሜት ፈጥሮ ውስጥነትን በፈቃደኝነትን ሊፈጥር ይችላል። በሌላ በኩል ይህንን ክፍተት አቻችሎ ችግሩን በወል ለመቋቋም #በሰፊነት ህሊናን ማሰናዳት የሚገባ ይመስለኛል። የጎደለውን ነገር አቅም ያለው እየሞላ፤ የጎበጠውን ነገር እያቃኑ ቢያንስ የአስቸኳይ ጊዜ የወረርሽኙን መከራ ለመግታት በብሄራዊ ጉዳዮች ላይ መረባረብ፤ የተዘናጉ ቦታወች ላይ እንዲህ አክብሮ ማስታወሻ በመላክ መሳተፍ ያስፈልግ ይመስለኛል። "ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት" ለዚህ ጭብጤ ልኩ ይመስለኛል። #የነፍስ #አድኑን እንቅስቃሴ በቅንነ...

ለመከላከያ ምርጥ ዘር እና የአዘቦተኛ ዘር ልዩነት የሚጠቅም ጉዞ አይደለም። ለዛውም በዞግ ርዕዮት በምትመራ አገረ - ኢትዮጵያ። የኢትዮጵያ እናቶች የአገርም እናቶች ናቸው ክብርም ሽልማትም የሚገባቸው።

ምስል
  ለመከላከያ ምርጥ ዘር እና የአዘቦተኛ ዘር ልዩነት የሚጠቅም ጉዞ አይደለም። ለዛውም በዞግ ርዕዮት በምትመራ አገረ - ኢትዮጵያ። የኢትዮጵያ እናቶች የአገርም እናቶች ናቸው ክብርም ሽልማትም የሚገባቸው።        "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     የአንድ አገር መከላከያ ለእኔ የአገር ሃኪም ነው። ሃኪምነት ሰብአዊነትም ነው የተፈጥሯዊነት ሚስጢርን ለተረዳ አቅም ላለው የአገር ምሶሰነቱን በፖለቲካ ሊቃናት ካልተበወዘ። ሠራዊት፤ ደህንነት፤ የጸጥታ አካላት ጉዳያቸው ሰው ሊሆን ይገባልም። ከግለሰቦች የሥልጣን ፍላጎት ተቋማት ሊሆኑ ይገባልም። በመርኽም በዲስፕሊንም። ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ሲማጥ የተኖረበት ግን ያልተገላገልነው የፈተና ቋት።   #ምዕራፍ ፲፯   እንዴት አደርን? ጭምቷ ኢትዮጵያስ እንደምን አደርሽ ይሆን? እምዬ ሲዊዝሻ እየኖርኩብሽ የምትናፍቂኝ፤ የማልጠግብሽም የከተማ ገዳሜ፤ ደጓ ቪንትዬስ? ማህበረ ቅንነት የሥርጉትሻ ፔጅ ደጋጎችስ እንዴት ናችሁ።    #እፍታ ።    በኢትዮጵያ የችግሮች ሁሉ መነሻ ምንጭ ይሁን መዳረሻ፤ የመፍትሄወች መቃረቢያ ይሁን የስኬት ሲሳይ የተቋማት ግንባታ አትኩሮት ዝቅተኝነት ይመስለኛል። ተቋም የትውልድን ሽግግር ቅብብሎሽ በሥርዓት የመምራት አቅም የሚኖረው ከአመሰራረት #ጥራቱ ይነሳል። የአንድ ተቋም የሂሳብ ሥርዓቱን ሰነድ ካልተዝረከረከ የዛ ተቋም ብቃት መስካሪ አያስፈልገውም። ራዲዮሎጂው ነው። በኢትዮጵያ እራሳቸውን ችለው፤ እራሳቸውንም አስከብረው ከዘለቁት ተቋማት ውስጥ ዕድለኛው፤ በዕውነትም ዕድለኛው ተቋም የኢትዮጵያን አየር መንገድ ማንሳት በቂ ይመስለኛል። ክብሩ ልዕልናው ዝቅ ከፍ ሳይል የቀጠለው የአመሰራረቱ ጥራት ...

#ነገና ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንዴት ትጠብቀው????

ምስል
  #ነገና ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንዴት ትጠብቀው????       የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኢትዮጵያ የቀደምት ተቋማንቷ አቅም፤ የደረጄ #ክህሎት ለልጅ ካልደረሰ … የትውፊት መዳረሻው ……? #ዕንባ #ሲያነባ ።    ፩) የብሄር ብሄረሰቦች #የወል #የፕትርክና ማዕዶት ፍላጎት ይሆን ይሆን ዕንባን ያስቀጠለው???  ፪) ወይንስ መንበረ ሥልጣኑን መቀመጫ ወደ ሌላ #ለማዛወር ታስቦ ይሆን ለለት ከፈን ያልበቁ ባለማተቦች ሰማዕትነትን የሚቀበሉት? ሁሉም ተሰጥቶ፤ ዕንባ ተውጦ ስለምን ችግሩ ቀጠለ???? አዲስ አመራር ይፈጠር ተብሎ ተከወነ። ፫) ምን ሲሆን ይሆን የቅድስት ተዋህዶ #ዕንባ የሚቆመው??? ፬) በጸሎት ደካማ ሆነን ፈጣሪ ተከፍቶብን ይሆንስ? ምርቃታችን ተነስቶ ይሆን???? ፭) ስጋትም አለኝ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተሰውተው ማካካሻ እንዳይፈለግም። የሰው ልጅ #ድህነቱን ችሎ በባዕቱ መኖሩ ጥበቃ ሊደረግለትይገባል። የሰው ልጅ ከፖለቲካ ፓርቲ በላይ፤ በጣም በላይ ነው። አርሲ ክፍለ አገር ጢቾ አውራጃ እኔ ኑሬያለሁኝ። አምኛ ወረዳ ላይም በባለማተቦች ላይ #ጭካኔ መፈጸሙን ሰምቻለሁኝ። እኔ በኖርኩባቸው ስድስት ወራት #ከፍቅር በስተቀር #ጥላቻ አላየሁም።    #ዛሬ ለምን??? #ጭካኔን ማንፈቀደለት? #ጭካኔን ማንስ ወለደው? ? #ዛሬ አርሲ ላይ #ርህርህና እንዲህ መነ? እንዴት???? ለዛውም የተዋህዶ ልጆች በርትተው ግፍ እና ግፈኞችን አስወግደው። የህወሃት መንበሩን ፈቅዶ ሥልጣኑን ማስረከቡ እኮ የቅድስት ተዋህዶ #ጭምት ልጆቿ ጸሎትም ተደምጦ ነው። እስኪ ከዕለቱ መረጃ ተነስቼ …… ትንሽ ስሜቴን ልግለጽ። "አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን። እንዴት...