ተስፋ ሰጪ ዜና WHO ምስጉን ተግባር ፈጸመ። (ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።)
ተስፋ ሰጪ ዜና ከኖር በእግዜር ፔጅ ከጉታማ ካራሌ ሼር የተደረገ ነው። ፎቶውንም የወሰድኩት ከዚው ፔጅ ነው።
እንዲህ ፈጣን እና የተደራጄ የርህርህና እርምጃ ተስፋ ይሰጣል። ያጽናናል። አይዟችሁን በአጽህኖትም ይልካል። ተመስገን።
«አስቸኳይ ዜና!»
«በደቡብ ኢትዮጵያ በቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ የዓለም ጤና ድርጅት
(WHO) ፈጣን ምላሽ ሰጠ!
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠረጠረ የቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ ዙሪያ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።»
«የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች በቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።
WHO ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት አስቀድሞ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦
1. ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለጤና ሰራተኞች የሚሆን የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE) ወደ ተጎዱ ከተሞች ተልኳል።
2. በወረርሽኙ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ንክኪን የመከታተል (Contact Tracing) ሥራን ድርጅቱ ይደግፋል።
3. ሊኖር የሚችለውን ድንበር ዘለል ስርጭት ለመከላከል ከደቡብ ሱዳን WHO ቢሮ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።
4. የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት፣ ለአስቸኳይ ድጋፍ እንዲውል 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ከWHO የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለኢትዮጵያ ተለቋል። ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፉን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የWHO ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ጤና ባለስልጣናት መረጃውን በወቅቱ በማጋራታቸው እና ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ቃል ገብተዋል።»
«Via WHO»
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ አሜን።
ሥርጉትሻ 2025/11/13
እግዚአብሄር ሆይ ለሁሉም የመኖር ዘርፍ ምህረትን ላክልን። አሜን።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ