#ነገና ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንዴት ትጠብቀው????
የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኢትዮጵያ የቀደምት ተቋማንቷ አቅም፤ የደረጄ #ክህሎት ለልጅ ካልደረሰ … የትውፊት መዳረሻው ……?
፪) ወይንስ መንበረ ሥልጣኑን መቀመጫ ወደ ሌላ #ለማዛወር ታስቦ ይሆን ለለት ከፈን ያልበቁ ባለማተቦች ሰማዕትነትን የሚቀበሉት?
ሁሉም ተሰጥቶ፤ ዕንባ ተውጦ ስለምን ችግሩ ቀጠለ???? አዲስ አመራር ይፈጠር ተብሎ ተከወነ።
፫) ምን ሲሆን ይሆን የቅድስት ተዋህዶ #ዕንባ የሚቆመው???
፬) በጸሎት ደካማ ሆነን ፈጣሪ ተከፍቶብን ይሆንስ? ምርቃታችን ተነስቶ ይሆን????
፭) ስጋትም አለኝ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተሰውተው ማካካሻ እንዳይፈለግም። የሰው ልጅ #ድህነቱን ችሎ በባዕቱ መኖሩ ጥበቃ ሊደረግለትይገባል። የሰው ልጅ ከፖለቲካ ፓርቲ በላይ፤ በጣም በላይ ነው።
አርሲ ክፍለ አገር ጢቾ አውራጃ እኔ ኑሬያለሁኝ። አምኛ ወረዳ ላይም በባለማተቦች ላይ #ጭካኔ መፈጸሙን ሰምቻለሁኝ። እኔ በኖርኩባቸው ስድስት ወራት #ከፍቅር በስተቀር #ጥላቻ አላየሁም።
ለዛውም የተዋህዶ ልጆች በርትተው ግፍ እና ግፈኞችን አስወግደው። የህወሃት መንበሩን ፈቅዶ ሥልጣኑን ማስረከቡ እኮ የቅድስት ተዋህዶ #ጭምት ልጆቿ ጸሎትም ተደምጦ ነው። እስኪ ከዕለቱ መረጃ ተነስቼ …… ትንሽ ስሜቴን ልግለጽ።
"አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን።
እንዴት ሰነበታችሁልኝ ቅኖቹ።
#ክፍል ፩
"አስደንጋጭ መረጃ አርሲ"
"በውስጥ የደረሰን መረጃ :- እኔ በዛው ቦታ ነው ያለሁት መረጃ እንኳን ለማን መስጠት እንዳለብን ተቸግረናል። በአይነ ቁራኛ ነው የምንጠበቀው። እስከዛሬ ድረስ በጀጁ ወረዳ በአንደጎቼ ሁላጨሌ ቀበሌ በኢጉ ጩካ ቀበሌ በሰንቢጤ ፊንጮ ቀበሌ በጉሬ ሙከጉራቻ ቀበሌ በአቡሌ ሙከጉራቻ ቀበሌ በወንጀሎ ወደይመና ቀበሌ እስካሁን ከመቶ በላይ ኦርቶዶክሶች ታርደ,ዋል።ተጨፍጭ,ፈዋል። ከግማሽ በላይ በጅብ ተበልተዋ,ል።
የጀጁን የክርስታያኖች ጭፍጨ,ፋ ማንም መረጃውን ያደረሰ የለም። ከእነዚህ ከታረ,ዱ ክርስቲያኖች መካከል ወንድማማቾች አባትና ልጅ የአጎት የአክስት ቤተሰብ ይበዙበታል ።
እንደዚህ መረጃ መስጠታችን ቢታወቅ መጀመሪያ እርምጃ የሚወስድብን የመንግስት አካል ነው።
የዛሬ 15 ቀን ልክ በዛሬዋ ዕለት የታገቱ ወገኖችን ትናንት ማለትም ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ ም ብር የሚያስገቡበት የመጨረሻዋ ቀን ናት። እያንዳንዱ 600 ሺህ ብር ነው የተጠየቁት ። ምናልባትም ከፍለውም ሊገደ,ሉ ይችላሉ።"
ከአቶ የሃበሻ ፔጅ ያገኜሁት ነው።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
የደረጄ ተቋም ያላት አገር ከአበጁት ተቋማት ውስጥ ቀዳሚዋ ቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እራሷን ማዳን፤ ለልጆቿ ጥላ ከለለ መሆን ለምን፤ ስለምን ተሳናት? እግዚአብሄር ይህን ጠጣር ሃቅ ይፈታው ዘንድ እለምነዋለሁኝ።
ሱባኤ፤ ጥሞና፤ ጸሎት በትጋት መቀጠል ብቻ ነው የእኛ አቅም። #ኦ! ሻሸመኔ በሚለው አውዲዮ ሁሉንም መከፋቴን ገልጫለሁኝ። አቅሜ ያ ብቻ ነው። በዛን ጊዜ ሰማዕታቱ ሚሊዮን ነበሩ። መደበኛ ሥራቸውን ያጡም ሰማዕታት ናቸው። ፊት ለፊት ወጥተው የሞገቱም ሰማዕታት ናቸው። ማገዶነቱ ግን ምን አተረፈ? በምን ተቋጬ #ዛሬ እራሱ ራዲዮ ነውና ይነግረናል።
ዝምታው ዝም ነው። ከድምጽ #ዝምታ ይከብዳል። የሻሸመኔ ሰማዕታት ዛሬ ጠያቂ አላቸውን? በኦሮምያ ከዚህ ቀደም በተለያዬ ጊዜ ሰማዕትነትን የተቀበሉ አራስ ነፍሰጡር አንስት ባለማተቦች ጠያቂ አላቸውን? ቤተክርስትያናችን ከኢህአዴግም፤ ከብልጽግናም የበጄት ድጎማ እንደማታገኝ ልጅ ተክለ ሚኬኤል አበበ ሲናገር ሰማሁኝ።
ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እና ልጅ ተክለሚኬኤል አበበ ኢትዮጵያ ሲሄድ ባለቤት አልባወችን የፖለቲካ እስረኞች በቀጠሯቸው በፍርድ ቤት ተገኝቶ፤ ቀጠሮ ሳይኖር በእስር ቤት እየተገኜ ይጠይቃቸዋል። በዚህ አጋጣሚ ከመቀመጫየ ብድግ ብዬ ከውስጤ እግዚአብሄር ይስጥልኝ ወንድም ዓለም ልለው እፈልጋለሁኝ። እንደ ታላቅነቴም ተባረክልኝን ልከለው።
የሆነ ሆኖ እራሷን በራሷ የምታስተዳድር ቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለእነዛ ለለት ጉርስ፤ ለከፈን ላልበቁ ልጆቿ #ጥግም ፤ #መጠለየም መሆን ካልቻለች ተቋምነቷ ምን ይባልላት? ብሄራዊ ናት። ዓለም ዓቀፍ ናት። ሰማያዊ ናት። ልምዱ ተመክሮው በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በአርምሞ፤ በጥሞና፤ በጸሎት፤ በሰጊድ፤ በአርምሞ እና እዮራዊ ጸጋም የተባረከ ነው። በብዙ ነዲድ አልፋ ነጥራ የወጣች ሃይማኖት ናት ቅድስታችን። ግን፤ ግን፤ ነገር ግን ተስፋቸው ላጡ ልጆቿ ምነው እንዲህ አቅም አነሳት??? እንደ ልዑቅነት፤ እንደ ዊዝደም ባለቤትነት እንደ ንጽህና እና ቅድስና ስለ ሰማዕታት ዝምታዋ ያስፈራል። ያርዳልም።
ዘግይተውም ይሁን ቀድመውም አምርረው የተናገሩ ብጹዓን አባቶች እንዳሉ አዳምጬያለሁኝ። እኔን የሚያሳስበኝ መከፋት፤ ፍልዕንባ መፍትሄ ማፍለቅ አለመቻሉ፤ አለኋችሁ የሚል የአዶናኝ ድምጽ መራቁ ነው። እግዚአብሄሩም እንዲህ መዘግየቱ ምን እንድንማር ፈልጎ ይሆን?
#ተቋም ያለውም፤ ተቋም የሌለውም እኩል መከፋት ከሆነ የተቋም አስፈላጊነት ምኑ ላይ ይሆን? በፊት በፊት ለፖለቲካ እስረኞች በአንድም በሌላም የሚናገሩ፤ መረጃ የሚጠናቅሩ ተቋማት ነበሩ። ዛሬ የለም። ለምን የተቋማት መሸብሸብ ይመስለኛል። ግን ነገር ግን ቅድስት ተዋህዶ ሥርዓቱን የጠበቀ፤ በፈርኃ እግዚአብሄር የተቀመመ ከታች እስከ ላይ ድረስ ድርጁ ተቋማት አሏት። የአሰራር መርህ እና የቁጥጥር ሥርዓት አላት። ይህ አቅም ለምን #ተዝለፈለፈ ነው የእኔ በኽረ ጉዳይ። ከፋኝ ተከፋልኝ፤ አዘንኩ እዘኑልኝ። አለቀስኩ አልቅሱልኝ። ሱባኤ ላይ ነኝ ተከተሉኝ። ያለችንን ሁሉ ፈጽመን መቋጯው ግን ………?
አንዳንድ ጊዜ ሃይማኖት ባይኖር ብየ ምድርን ሳስባት ድቅድቅ ትሆንብኛለች። ሃይማኖት የተስፋ ብርሃን ነው። ሃይማኖት የመንፈስ መታደስ ነው። ሃይማኖት ጭካኔን እንዳንተባበር ልጓም ነው። ሃይማኖት መኖርን አሰልጥኖ በሥርዓት የሚመራ ንጹህ ኦክስጅን ነው። ሃይማኖት የለት ለት መኖር ነው። መኖር በምድራችን ሲታመም፤ መኖር በባድማችን ተስፋ ሲያጣ በአገር፤ በመሬታችን በባዕታችን ተሰደን ለምንኖረው ምን ግብረ መልስ ይኖረው ይሆን????
#እያሰገረ በሚነሳው የዚህ የሃይማኖት መጠቃት መጨረሻው ምን ይሆን?
ብዙ ሃሳብ ማንሳት ይቻል ይሆናል። ግን ሃሳቡ ለማህበረ ምዕመኑ መከራ ደራሽ ካልሆነ ምን ያደርጋል? ትንሽ የማስባቸውን ልጥቀስ ፩) ምን አልባት ቅድስት ተዋህዶ መንበር ፕትርክናዋን እንድታጋራ ጫና የመፍጠር ስልት ሊሆን ይችል ይሆን?
**** #ፕትርክና #የጋርዮሽ ቢሆንስ የቅድስ ተዋህዶ ምስኪን ምዕመናን እረፍታቸው ሰላማቸው ይጸድቅ ይሆን? ለመሆኑ በብልጽግና ካቢኔ ውስጥ ምን ያህል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን አሉ? የቅድስት ተዋህዶ የፖለቲካ ውክልና ማጣትም ከዘመነ ደርግ ጀምሮ ስለሆነ ይህ ቅድስቷን ፈተና ውስጥ ከቶ ሰላሟን እየነሳት ይሆን???? ሁለት ወይንም ሦስት የብሄር ብሄረሰቦች ፕትርክና
2) እንደ ሻሸመኔ፤ አርሲ ነገሌ፤ ሽዋ ሮቢት ወዘተ ለ2013 ዓም የምርጫ ሂደት የመሃል አገሩ ማህበረ ምዕመን ለመጪው ምርጫ ህሊናውን ለማሰናዳት ይሆን?
ለምርጫ ተብሎ፤ ወይንም ለቤተ ክህነት አዲስ የጋራ የወልዮሽ የፕትርክና ልዕለ መመራር በፕትርክና ተፈልጎ ይሆን??? ግን ለምን ደሃ ፍጹም አቅመ ደካማ፤ ለፍቶ አዳሪ፤ ቅዱሳን ህፃናት ስለምን በየዘመኑ ይንገላቱ በማተባቸው ብቻ? ለምን ይሰቃዩ የሰው ልጆች? እናት አልባ ልጅ፤ ወላጅ አልባ ልጅ ቅድስቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንደምን ታስተዳድራቸው? ትመራቸውስ ይሆን????? ነገስ? ከነገ ወዲያስ? ከዚያ ወድያስ? አደባባይ ሚዲያ ጉዳዩን በተከታታይ እንደሚሰራበት ገልፆል። እንደ ዋና አዘጋጁ ቀሲስ መላዕከ ኤዶም ገለፃ በየለቱ #እስከ ፭ የሚደርሱ ምዕመናን ሰማዕትነትን እንደሚቀበሉ፤ ንብረታቸው እንደሚዘረፍ ኃላፊነት ወስደው ዘገባውን አቅርበዋል። መቼ ቅድስት ተዋህዶ ይህን ታስቆመዋለች ነው የእኔ ጥያቄ። መቼ????? መቼ ነው በኦሮምያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የፖለቲካ ውክልና የሚኖራቸው???? መቼ???? ይህን የማስደረግ አቅም አንድ ተቋም ከሌለው??? ……………
#ክፍል ፪
"ለምሳሌ በአንጎደቼ ቀበሌ 400 ሺህ ብር ከፍሎ የተገ,ደለ ወንድማችን መምህር ግርማ መለሰ ሌላም ስሙን ያላወኩት 280ሺህ ከፍሎ የተገደ,ሉ ናቸው።
በወሸባ በረከት ቀበሌ አንድ ካህን አባት 500ሺህ ብር ከፍለው ተገድ,ለዋል። እሬሳቸ,ውን ጅ,ብ ነው የበላ,ው ።
በአምሽራ መንጋግሳ ሁለት ወንድማማቾች 400ሺህ ብር ከፍለው እንደወጡ ቀርተዋል።
ይሄ ደጋማና ቆላማውን ክፍል ሳይጨምር የወይና ደጋውን ክፍል ነው ።
እንደ ወረዳው ከ500 እስከ 1000 ሺህ ኦርቶዶክሳዊያን ተጨፍጭፈ,ዋል።.............. "
#habesha #ኢትዮጵያ2018 #ሐበሻ #ኢትዮጵያ #Ethiopia
#እርገት።
ሳጠቃልለው አቅም ያላት ተቋም ያላት ቅድስት ኦርቶዶክስ የነገዋ ተስፋ ዕንባ ወይንስ ተንስዔ??? "ባለቤቱን ካልናቁ ደጁን አይነቀንቁ" አቅም በፀሎት፤ በምህላ፤ በንጽህና፤ በሱባኤ ይፈጠራል ብየ አምናለሁኝ። ቅንነቱ ካለ።
በመጨረሻ የራሄል ዕንባ የሰማ አባታችን አማኑኤል፤ እናታችን ድንግል ማርያም የሃዘን መጨረሻ ያድርግልን። አሜን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/11/2925
በቃችሁ ይበለን ፈጣሪያችን። አሜን። ድንግልም ትርዳን። አሜን።


አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ