#ፋታ #ለማይሰጥ #ድንገተኛ #ወረርሽኝ #ብሄራዊ ዝግጅት #በአፋጣኝ ሊደረግ ይገባል።

 

ማንነቱ ያልታወቀ #ሥምአልቦሽ በሽታ ሲመጣ #ለእስረኞች እጅግ አሳሳቢ ነው። የብልጽግና መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ጉዳዩ ከከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የደንበር ዝውውሮችን ሊቆጣጠር፤ እስከ #የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ሊያደርስ የሚችል እርምጃወችን በአፋጣኝ መውሰድ ይኖርበታል። አቤቶ ብልጽግና #ብሄራዊ ኮሜቴ ማቋቋም የአለበት ይመስለኛል። 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
ይህን ዘገባ ካለወትሮው BBC ዘግይቶ ነው የዘገበው። የሆነ ሆኖ በጣም #የሚያስጨንቅ ነው። በሽታው ወዲያው የሚያጠቃው #ኩላሊትን ስለመሆኑ ዘገባው ይጠቅሳል። እስር ቤት ውስጥ ያሉ ወገኖች እጅግ ያሳስባሉ። በዩንቨርስቲ፤ በሆስፒታል፤ በመጓጓዣ የተሰማሩትም እንዲሁ። 
 
ለሰመዓታቱ ቤተሰቦች ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁኝ። 
 
እግዚአብሄር ሆይ! እንደ ቸርነትህ ይሁንልን። አሜን። በደላችን በዝቷል እና ይቅር በለን። አሜን።
ሥርጉትሻ 2025/11/13
 
ምህረትህ ይናፍቀኛል ጌታ ሆይ! እባክህ እርዳን! አሜን። 
 
"በጂንካ ከተማ የተከሰተውን በሽታ "ሲያክሙ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሞቱ"
ከ 12 ደቂቃዎች በፊት
 
"በደቡብ ኢትዮጵያ ክል፣ ጅንካ ከተማ በተከሰተው በውል ያልታወቀ በሽታ ለተያዙ ሰዎች "ሕምክና ሲሰጡ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለቢቢሲ ገለጸ። የበሽታውን ምልክታ ባሳዩ ታካሚዎች ላይ "በፍጥነት የኩላሊት ሥራ የማቆም (fail)" ሁኔታ እንደታየም ተገልጿል።
 
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጂንካ ከተማ "ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሔሞራጂክ ፊቨር" በሽታ መከሰቱን ያስታወቁት ትናንት ረቡዕ ሕዳር 3/2018 ዓ.ም. በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው። በሽታው መከሰቱን ያመለከቱት "የቅኝት መረጃዎች" መሆናቸውን የገለጸው መግለጫው፤ ስምንት ሰዎች "በበሽታው እንደተጠረሩም" ገልጿል።
 
"በሔሞራጂክ ፊቨር" የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የመጣው "ከሦስት ሳምንት ገደማ" በፊት እንደነበር የሕክምና ተቋሙ ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰላሙ ታደሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
 
የወባ በሽታ እንደሆነ በመጠርጠሩ በሌላ የጤና ተቋም ሕክምና ሲያገኝ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ሰላሙ፤ ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የመጣው ሁኔታው "በጣም ከባድ" ሲሆን መሆኑን አስረድተዋል።
 
ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተሩ እንደሚናገሩት ታካሚው ወደ ሆስፒታሉ ከመጣ በኋላ ሕመሙ "አስጊ" ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀጥሎም በሆስፒታሉ "አንድ ቀን ገደማ" ከቆየ በኋላ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ከተፈጠረ ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን አሳይተው ለሕክምና መምጣታቸውን ገልጸዋል።
 
"ከሳምንት በኋላ፤ ከዚያ ታካሚ ጋር በተለያየ ምክንያት ጉርብትና፣ አንድ ላይ የነበሩ ጓደኞቹ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ማሳየት ጀመሩ" ሲሉ ያጋጠመውን ተናግረዋል። በሌሎች ታካሚዎች ላይ ተመሳሳይ ምልክት መስተዋሉን ተከትሎ ሆስፒታሉ ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ መላኩን አስረድተዋል።
 
ዶ/ር ሰላሙ እንደሚገልጹት የዚህን በሽታ ምልክት በማሳየታቸው በሆስፒታሉ ሕክምና የተደረገላቸው "ስምንት ገደማ ሰዎች" ናቸው። ከእነዚህ ታካሚዎች ውስጥ ለበለጠ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተማዎች የተላኩ እንዳሉበት ጠቅሰዋል።
 
ታካሚዎች ሪፈር የተደረጉበት አንዱ ምክንያት በግለሰቦቹ የታየው "ኩላሊት በፍጥነት የመክሸፍ (ፌል)" የማድረግ ሁኔታ እንደሆነ አስረድተዋል። "የኩላሊት ሁኔታቸው በጣም ቶሎ ነበር ሥራ የማቆም (fail) የማድረግ ደረጃ የደረሰው። አንዳንዶቹ normal range የነበሩት ሰዎች በሁለት በሦስት ቀን ስታይ 4፣ 5 የመሆን፤ ከዚያም ሰባት የመሆን [ነገር ነበር]። ከሚጠበቀው በላይ ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ነበር" ሲሉ በታካሚዎች ላይ የታየውን ሁኔታ አስረድተዋል"።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።