ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 6, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ።

  #የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ማህበረ አወንታውያውያን እንዴት አደራችሁልን? አወንታውያን የትውልድ #አንበል ናችሁና ደህንነታችሁ በእጅጉ ያስፈልገናል።   #ጠብታ ።   ትናንት ከአዲስ ኮንፓስ ጋር ውይይት ያደረገ ወጣት ጋዜጠኛ ነበር። ብዙ ጊዜ ሳዳምጠው ለእናት አገራችን ለኢትዮጵያ ያለውን ንጹህ ቅንነት አይበታለሁኝ። ለዚህም ነው ጊዜ ሰጥቼ የማዳምጠው። በጋዜጠኝነትም ህይወት ውስጥ ዝልቅ ተመክሮ ያለው ወጣት ነው። በዬትኛም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ #ቅንነት ካዬሁ ወይንም ካዳመጥኩ እሳባለሁኝ። መዳኛችም ቅንነት ነው። ውድቀታችንም የቅንነት ፍልሰት ነው። • https://www.youtube.com/watch?v=AC2qgGIlmbI «የትራምፕ መንገድ፣ ለውጡና ምክክሩ፣ "ጊዜያዊ የተኩስ አቁም"   ወጣቱ ጋዜጠኛ አንተነህ የብልጽግና ጉዞውን የሚደግፍ ይመስለኛል። በጠሚር አብይ አህመድ የአመራር አቅምም ላይ ተመስጦ እንዳአለው አስተውያለሁኝ። ይህ ሙሉ መብቱም ነው። እኛ እንቃወም የለምን? ጋዜጠኛ አንተነህ ሙግት ሲኖርም በቀጥታ ይሞግታል። በተለይ ፕሬስ ህግጋት ላይ።   ስለ አዲስ አበባ ትናንት ሲገልጥም የመከፋት ግን ጊዜን የመጠበቅ አስፈላጊነት ፍንጭ የሚሰጡ ዝንባሌወችን አዳምጫለሁኝ። ዕውነት ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ የሚመቸንም፤ የማይመቸንንም ሃሳብ እኩል አዳምጡ ሳያጋንኑ፤ ወይንም ሳያይሸበሽቡ በሃሳብ መሞገት የተገባ ይሆናል። ያ ሃሳብ በብዙኃኑ ድምጽ ከፀደቀ በዛ መገዛት ግድ ይላል። እኔ እንዲያውም እኔ የማራምደውን ሃሳብ ከሚያነሱት ይልቅ ከእኔ ለዬት ያለ ሃሳብ ያላቸውን ባደምጥ እመርጣለሁኝ።   በአዲስ አበባ የቤቶች ፍርሰት ሁኔታ ዴሞግራፊ አለ ...

የኢትዮጵያ #ሰኔል እና #ከፈን #የገፍ #ሸመታ የጭካኔ ዘመን #መቼ #ያከትም ይሆን?

ምስል
  የኢትዮጵያ #ሰኔል እና #ከፈን #የገፍ #ሸመታ የጭካኔ ዘመን #መቼ #ያከትም ይሆን?   እግዚአብሄር ሆይ! #በግፈኞች ፣ #በጨካኞች ላይ #ፍርድህን እባክህ #አታዘግይ ? እባክህን #አባት #ሆዬ ! እንደዚህ #መንፈሳችን #የሚገድሉትን የበቀል አምላክ አይደለህ? ፍርድህን ስጥ! #አትዘግይ ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ምድሪቱም አቤት የአንትያለህ የሠራዊት ጌታ፣ የህዝብህ እንባሆነ #ከርታታ እያለችህ ነው። #እረፍት #አጣን ። ሰርክ ቀብር???? #አመመኝ ! #ቆሰልኩኝ ! ሥርጉትሻ 06/02/2025 መቼ #ሰው ይከበር ይሆን? መቼ ለትጉኃን #የነፃነት ዘመን ይመጣ ይሆን!