በግራ ቀኝ ተረብ ላይ ያላችሁ ቀልዱን እባካችሁ አቁሙ። ዝምታ #ዕውነቱን አለማወቅ አይደለም።

 

በግራ ቀኝ ተረብ ላይ ያላችሁ ቀልዱን እባካችሁ አቁሙ። ዝምታ #ዕውነቱን አለማወቅ አይደለም። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
 
 May be an image of morel mushroom and mushroomMay be an image of ‎11 people and ‎text that says '‎ነፃነት ከፍርሃት አይገኝም!!! محهرا አማራ Amhara Resistance is loading... 1.በላይነሽ መኮነ 2.ሳምራዊትቀ ቀሬ 3.ዘውዴ ግርማ 4ሙሉ ዘውዴ 5.ግርማቸው የኔነህ #BRING BAC Ko UR GIRLS FREE Hostaged Amhara ris Boko Haramin aran Ethiopia! bethe โ ጌቴ 7.ትዕግስት ከፍያለው 9.ዘመድ ብርሃ 10.ሞነሞን በላይ 11.ጤናለም ሙላቴ 13.አሳቤ አየለ 14.ቢተውልኝ አጥናፉ 16.አታለለኝግሉነት 16.አታሌራ ጌትነት 17.ከንድየ ሞላ‎'‎‎May be an image of 14 people and textMay be an image of 1 person and text that says 'STOPHE STOP the ንቤጨቅክር the The world Shoul know the brave and the H Hero Asmra Her Name is Asmira Shumye! She escaped from the Oromo Terrorist Group n Ethiopia & spent 3 nights in a jungle hanging on a tree! E She is now a voice for the remaining kidnapped 13 girls and 4 Boy University students.'
 May be an image of textMay be a black-and-white image of 1 person and childMay be an image of ‎1 person and ‎text that says '‎م Lun ስንግት የኃል እፈጥቆ ז G D o4v 4 ዐ 4A4 ٧ vdb do ۸‎'‎‎May be an image of 1 person and Angel Oak treeMay be an image of 2 people and text that says 'PIC.COLLAGE PIC'May be an image of 1 person and beard
 
 
 
 
 
©እፍታ።
 
አቁሙ ስል ትዕዛዝ አይደለም። የአማራ ፖለቲካ የአማራ #እናት ማህጸን እና የአማራ #አባት አብራክ ቀራንዮ ላይ ማቱን፤ ምጣቱን እያስተናገደ ያለበት ስለሆነ ነው ውስጤን ፍንትው አድርጌ እማጋራችሁ። ለአደባባይ እንደ ቄጤማ የማይነሰነስ ትጋትም ስላለኝ ደፍሬ መናገር እችላለሁኝ። ነዶ አይደለም እዬታጨደ ያለው የአማራ ትውልድ ነው። 
 
ሩብ ብልጽግና፤ ግማሽ ብልጽግና፤ ሩብ ብአዴን፤ ግማሽ ብአዴን፤ ሩብ ኦህዴድ፤ ግማሽ ኦህዴድ፤ ሩብ ደህዴን፤ ግማሽ ደህዴን፦ ሩብ ህወሃት፤ ግማሽ ህወሃት መንፈሱ ያላችሁ ሁላችሁም እራሳችሁን - መርምሩ። አደብ ግዙ። የሞገትንላቸው አሁን ላይ የት ላይ እንደሆኑ መደባቸውን እያዬን ነው። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና።
 
በአማራ ፖለቲካ እጁን ያልነከረ፤ #አብሲት የማያበስል የለም። ግማሹ ለኑሮው፤ ከፊሉ ለዝና፤ ጥቂቱ #በሰባዕዊነት ሊሆን ይችላል። የትግሉ ዝንቅንቅነት አቅም ያላቸውን ጓዳ እያስቀመጠ፦ የአማራ ፖለቲካ የሁሉም የኢቤንት ሜዳ ሆኗል። ሁለት ዓመት ሊሞላው ነው። ጠርዝ ለጠርዝ የሚሄዱ ትጉኃን በዝምታ የባሰውን ብቻ እዬነካኩ የሚገኙት እኔን ጨምሮ። 
 
የኦህዴድ "#ሰብረናቸዋል፤ በትነናቸዋልም" ምንጩ ይኼው ነው። ዕውነቱ #አልተሰበርንም#አልተበተንም። ጉዳዩ ሙሉ ቀን፤ ሙሉ ሌሊት ዲስኩር እና ፎቶ ቢያሰለች ብቻ ሳይሆን፤ "አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል" ሆኖ ነገር አለሙ ለማን? ለምንስ? አቅም ይፍሰስለት ከሞገዱ ፍልሚያስ ማገዶነቱ ምን ሊያተርፍ በሚል ነው። አቅጣጫዊ አመክንዮ የጠራ መንገድ እስኪያገኝ #መጠሞን ግድ ስለነበር።
ሰሞኑን "ልብወለድ ይበሉት" ምን አንድ ሰነድ ሳዳምጥ ማህበረ ኦነግ የተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራንፕ በውስ ተኮር ስለሆኑ የአሻንን በአሰኜን ሰዓቴ እንፈጥማለን የሚል ነገር አዳመጥኩኝ። ከአንከር ሚዲያ የጅማው ዕድምታ ክፍል ሁለት። እራሱን አስችዬ እመጣበታለሁኝ። 
 
እነ ማህበረ ኦነግ ሚሞሪያችሁ ምነው ዳ አለሳ ልላችሁ እፈልጋለሁኝ? ህወሃት ፈቅዶ እና ወዶ ሥልጣኑን ያስረከባችሁ እኮ #በትራንፒዝም ዘመን ነው። ትናንት የነበረው እግዚአብሄር ዛሬም አለ፤ ትናንት የነበረው አላህ ዛሬም አለ። ልባችሁ የሚያውቀው የምትፈተኑበት ጫና ትናንትም አለ ወደፊትም ይኖራል። አትንጠራሩ መታበይ ስንቃችሁ አይሁን። በልክ ሁኑ መሪነት ሎሌነት ነበር ለሚያውቀው። የምድር ነገር ሁሉ አላፊ እና ጠፊ ነው። "የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሄር ይመካ።"
 
©ውስጤ።
 
በዚህ ሂደት የሃቅ ጥግ ማጣት ዘመን ሊተካቸው የማይችሉ የአማራ #ብሌኖችን በመሰወር፤ በመታገት፤ በመታሰር፤ በመገደልም እያጣን ነው። አሁንም ስንት የተስፋ ማህለቆች አፈር ጋር ውስጥ እዬኖሩ፤ ስንት መኖር ተበትኖ፤ ስንት ህፃናት በሞትም በስጋት ተሳቀው፦ ስንት መፈናቀል ደርሶ፤ ስንት ልጆች ከትምህርት ገበታ ተገልለው፤ በአንድ ወይ በሁለት የግለሰብ ሰብዕና እና #ክብር ላይ ያለው ሙግት ቀጥሏል። ዝም ብዬ ሳስበው የዓላማ እና የግብ መሰወር ሆኖ አገኘዋለሁኝ። ከ35 - 50 ሚሊዮን ህዝብ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ተሸጉጠህ ጠብቀኝ ካልሆነ በስተቀር የግለሰቦች ክብር እና ዝና ከዚህ ህዝብ መከራ ሊበልጥ አይችልም። እንደገና እኛ እያለን ይህ የሆነ 20/30 ዓመታትን እሰቡት። የዚህ ሁሉ ተስፋ ነው አብሮ ሞክ እያለ ያለው። 
 
በአንድ ሰው ምክንያት ስንት ነገር ደቆ፤ ስንት ውድመት ተከስቶ፦ የዛ አጃቢወች ዛሬ ኬኒያ እና ኡጋንዳ ተቀምጠዋል። ልጆችን ተሰዶ ማትረፍ ብልህነት ቢሆንም ባልተገባ አመራር ይሁን ጥድፊያ አስፓልት ላይ ደሙ የፈሰሰ የአማራ ልጅ ደም ግን ውስጥን ሊያቆስል አለመቻሉ የፍጥረትነት ትርጉሙ አልገባኝ ይላል። ምንም የሌለው ሰላማዊ ሰው ስንት ዋጋ ከፈለ???? አማራቹ ገበሬ ያመረተውን መሰብሰብ አለመቻል በራህብ እርገፍም እኮ ነው። አይገባችሁም? ጎጃም ላይ ራህብ ሲገባ???? 
 
ይህም ሆኖ "#እናቱ የሞተችበት እና እውሃ የሄደችበት እኩል ያለቅሳስ" እንደሚባለው። ልጅን፤ ትዳርን፤ መላ ቤተሰብን #ሁነኛ ቦታ አስቀምጦ መታገል እና ሁለመናን #ቋያ ላይ ምድጃ አድርጎ መታገል እኩል ሚዛን ሊወጣለት ፈጽሞ አይችልም። በሌላ በኩል አፈር ውስጥ ማርጀት እና ቁሞ ፈቅዶ መንገላታትም እኩል ለንጽጽር አይቀርቡም።
 
አንድ ሃኪም ሞቱም ሆነ ድህነቱ፤ ድህነቱም ሆነ ስኬቱ የእሱ አይደለም። #የሚሊዮኖች ህዝብ የህላዊነት ጉዳይ ነው። ምድራዊው ቅዱስ እግዚአብሄር #ሃኪም ነው። ምድራዊው ቅዱስ #ሩፋኤል ሃኪም ነው። ዕንቁ አፈር ውስጥ እዬቀበሩ በሌላ ትርምስ ከዚህም ከዚያም ያለው ውርክብ ሊቆም ይገባል። አቅመ ቢሱ እራሱን መርምሮ፦ አቅመ ቢስነቱን ተቀብሎ ከአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዞር ሊል ይገባል። የመሪነት አቅም በጋቢ፤ በካሊም፤ በወረቀ ዘቦ ቢጀቦን ቅብዓ ከሌለ የለም። ለዛውም የጦር መሪነት ቆፍጣነነትን፤ ኮስታረነትን የሚጠይቅ ነው። ክላሽን ተፈርቶ አይሆንም።
 
እኔ የጦርነት ደጋፊ አይደለሁም። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ነው ያደኩት። ጦርነት በቃን ባይ ነኝ። የፌድራሉን እና የህወሃትንም አጥብቄ ነበር የተቃወሜኩት። ከጦረንት ትርፋ በቀል እና አመድ ስለሆነ። ነገር ግን እሳተፋለሁ፤ እመራለሁ ከተባለ ግን ከክላሽ፦ ከኮልት ጋር እዬተያዩ ሳይሆን ሸክሙንም ቤተኛ መሆን ይጠይቃል። በጦርነት አውድ ሌላው እየተማገደ ሰላማዊ ታጋይነት ቀመሩ አያስኬድም። ከገቡበት ድፍረትም፦ ወኔ ይጠይቃል። ለሚወድመው፤ ላለቀው ነፍስ ሁሉ ተጠያቂነት እና ኃላፊነትን መውሰድም ግድ ነው። ፃድቅ ስድስት ክንፍ ያለው የለም። አለኝ ከተባለ ዋልድባ፤ ደብረ ዳሞ ወዘተ ……… ሁለት ሦስት ወዶ አይሆንም። 
 
በበቂ የተማሩ፤ የተማሩትንም፤ የሚማሩትንም የመሩ፦ ጊዜ ፈቅዶላቸው የአገር ጠቅላይ ሚር የነበሩት የተከበሩ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ እኮ #አልችልም ሲሉ በደስታ አልነበር፤ ከደስታ በላቀው #በሐሴት እንጂ። ሁልጊዜም እንደምለው በደስታ እና በሐሴት መካከል ልዩነት አለ። ሐሴት ምድራዊውን እና ሰማያዊውን ዓለም ያገናኜ እርካታው ዘላቂ ሲሆን፤፦ደስታ ምድራዊ እና ጊዜያዊ ነው። አቃተኝ ማለት ክብር ነው። ደብረ ኤልያስ ገዳምን በ500 ዓመት መተካት ይቻል ይሆን??? እእ። ብዙ ነገር ደቋል። ብዙ ነገር ፈልሷል። ሚስጢርም ተደፍሯል።
አቅም አለኝ የሚለውም ቢሆን "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ" የሚለው የልብ አምላክ አስተምህሮ ተከትሎ ከእላፊ ንግግር፤ ከመታበይ ማማ ወርዶ መሪነት #ሎሌነት መሆኑን አውቆ፦ ከበዛ የፎቶ ዕለት በዕለት ትዕይንት፤ ከበረከተ ተረት እና ምሳሌ፤ ዕድል እና አጋጣሚ የሰጠውን መከበር በቅጡ ሊያስተዳድረው ይገባል። 
 
ይህ መንገድ ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም አልጠቀመም እና። ቢጠቅም በኢትዮጵያ ታሪክ ሳይታወቅ በሚሊዮን ፍቅር የከበረ ከሳቸው ሌላ ማን ነበር? ስለሆነም የአማራን ትግል መሬት ላይ የምትመሩ ወንድሞቼ ወደ #ጥሞና፤ ወደ ስክነት፤ ወደ ተደራጀ አመራር፤ ከግላዊ ዕሳቤ ወደ ቲም ወርክ ልትገቡ ይገባል። በስንት ዘመን ይሆን ሰማዕቱ ዶር አንዱአለም ዳኜ የሚተካው?? ልብ ይስጣችሁ አምላኬ። አሜን። 
 
በዬትኛውም ሁኔታ ዱር ቤቴ ላሉ ወገኖች ድክመታቸውን ነቅሶ በጥንቃቄ እርማት መስጠት ሲገባ ዘለፋም፤ ማቃለልም ፈጽሞ አይገባም። የቀደመ ተሳትፎን መድፋትም ግፍ ነው። እያንዳንዷ ቀን የአሳር ዶፍ የተስተናገደበት ነውና። እስር ባቱን አውቀዋለሁኝና። 
 
ዱር ቤቴ ላሉት አክብሮ #መሞገት ሳይሆን፤ አክብሮ የተሻለውን መንገድ በአክብሮት ማሳየት ይገባል። የገጠሩን ኑሮ ብታውቁት ይህን ያህል አትዳፈሩም ነበር። ይህንንም እኔ አውቀዋለሁኝ። ለአንድ የፊልም ተግባር ለሰሞናት እንኳን ይከብዳል እንኳንስ ህይወቱን እዬኖሩ ለመታገል መወሰን። ወንዝ ሞልቶ እስኪጎድል እዛው ቁጭ ተብሎ ተውሎ የሚታደርበት ጊዜ አለ። ክምር ላይ ማደር መዋል ይኖራል። ሰኔል የሚቸግርበት ጊዜ አለ። ዝናብ ማቱን እያወረደ ቁሞ መዝለብ አለ። መጠጊያ ጠፍቶ። ከባድ ነው። አታቅልሉት፤ #አትዳፈሩትም
 
በሌላ በኩል አክሰሱ ላላቸው ልጆች ብዙ አስደንጋጭ ገጠመኞች በንግግሮች ውስጡ አለበት። የሚገርመው በአንድ ጎጆ ውስጥ ሁለት የተቃራኒ የቦክስም ዓውድም አለ። አይገርምም??? የሆነ ሆኖ #አብነት በዬትም ሁኔታ ሊኖር ይገባል። ጭንቅ ላይ፤ ምጥ ላይ ስጋት ላይ ያሉ ልጆች በተለይ መሬት ላይ ለሚገኙ አማራ ክልል ለሚኖሩ ልጆች በሚሰማው ነገር ሁሉ ተስፋቸው #ይጎሳቆላል። ሚዲያ ተመቸኝ ብሎ የስድብ ናዳ፤ የዘለፋ ወርክሾፕ፤ የማዋረድ ፓናል ዲስከሽን በፍፁም ለዚህ ዘመን ሥልጣኔ የሚመጥን አይደለም እና ሊቆም ይገባል። እራስን ማረም እንደምን ያቅታል???? እራስን መቅጣት ብድር አያስኬድም እኮ????
 
…… ግን ታውቃላችሁ ክብረቶቼ የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪወች እስቲ የምታደርገውን እናያለን ተብሎ በፋክክር #በግፍ እንደታገዱ? ምክንያቱም የአማራ ህዝብ የመከፋት ጅማሬ የጉዳዩ የአያያዝ ዝበት ስለነበረበት፦ ለዛውም አልተቀጠለበትም። የሆነ ቦታ ልኩስ ትውት የፌንጣ ፖለቲካ። 
 
በወለጋ ከ1000 በላይ በአንድ ቀን ያን ያህል የወል መከራም የተፈፀመባቸው ንፁኃን ሥጋወቻችን ሰቆቃ በዚህው አግባብ ነው፤ ልኩ እብስ በሚል ቅጽበታዊ ክንውን። በአዲስ አበባ የወለጋ ተፈናቃዮች ከደብረብርሃን አርሲ፤ ከአርሲ ዶሮ ማርቢያ #ዶሮኩስ ስቶር ተፈልጎ የተከዘኑትም የእልሁ መንገድ ያመጣው መከራ ነው። የወይብላ ማርያም መከራም እንዲሁ፤ የገዳማት፤ የአብነት ተማሪወች ፍጅትም፦ መደፈርም፦ የፖለቲከኞች የአቅም ፋክክር ጦስ ነው። በ10/20/30/50 ዓመታት አይደለም በ500 ዓመታት የማይገኙ የተከደኑ እኛነቶች ተጋልጠው ለጥቃት በቅተዋል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የቅዱሱ ገዳም የደብረ ኤሊያስ የቀራንዮ ውሎ ከበቂ በላይ ነው። የቀረን ነገር የለም። ተጎርጉሯል። ተበርብሯል። ብልህነት ጎደለ። ጥበብ ተሰወረ።
 
አላቅም ውጥን ኪሳራው ለዘመን ጠገብ እኛነት ነው። ይህ ሊጠዘጥዝ ሲገባ አሁንም እዛው ላይ ሲዳከር አስተውላለሁኝ። ሁለት ፍሬ ወጣቶችን አዲስ አበባ አምጥቶ ዲል ካለ ሠራዊት ጋር አጋጥሞ የሳት እራት በማድረግ የአማራን እናት ተስፋ ሪሚጦ ማድረግ መሪነት ወይንስ ገርጋሪነት ምን ይባል? ይህ የብልህነት ልቅና ሳይሆን የብልህነት #ተዘቅዝቆ መሰቀል ነው።
 
ትውፊት ዳንቴል መሰለ። የቀደመ የልቅና ልዕልና የቅርስ፤ የውርስ ዲታነት ተከድኖ ሊያዝ የሚገባው የሥልጣኔ ቅኔ ነበር። ላወቀበት። ዛሬ ጠሚር አብይ ሌት እና ቀን የሚባትሉበት እኮ የስሜን ስልጣኔን አኮስሶ አደብዝዞ በውዞም በአብይዝም ሥልጣኔን ለመትከል ነው። እራስን ማስከበር የነበረን በማክበር ሊሆን ይገባ ነበር። አንዷ የቤተ- መቅደስ የክዳን እሳር ዘለላ የራሷ ቅዱስ መንፈስ አላት። ያለንን ሳናውቅ፦ ሳናስከብር፦ ሳናመሳጥርም የማናውቀውን አንፈልግ። የአማራ ህዝብ ሥልጣኔ ትቢያ ለማልበስ ቀን ከሌት ትግል ላይ ላሉት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ምን እሚሉት ስሌት እንደ ሆነ አልገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም። 
 
ታሪክ የሚሠራው፤ ሥልጣኔ የሚጀምረው በቀደመ ህዝብ ነው። የሆነ ሆኖ አዲስ አበባ የአማራ ሥልጣኔ ጫና አለበት ተብሎ፤ እዛው አማራ ክልል ስለራሱ የሚናገረው ዕውነት #ይፍለስ ካልሆነ በስተቀረ፦ ቅዱሳን ገዳማት የጦር አውድማ እንዲሆኑ ምሽግ ባልሆነ ነበር። ከስረናል። ይህን መቀበል የአባት፤ ማረም እና እራስን መገሰጽም የተገባ ነበር። እንዴት ውስጤ እንደ አረረ ብታውቁ። እኔ ያልታዩ እዬተባሉ የሚገለጡት ሁሉ ለዚህ ዘመን የተገባ አለመሆኑን ቀደም ብዬ አስገንዝቤያለሁ። ምክንያቱም የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ አሉታዊ ዴሞግራፊ ስለሆነ። የሆነ ሆኖ አንድ ባለማተብ እንዲህ ሊያደርግ አይገባም ነበር። በገዳማት ውድመት ትርፋማው ዲያቢሎሳዊው መንፈስ ነው። የእናት ቤተክርስትያናችን ዝምታም ይህው አመክንዮ ይመስለኛል። ምን ታድርግ? የቤተ- መቅደስ ተልዕኮ ቤተልሄም ነው። የጦር ግንባርነት ጉድብነት አይደለም። 
 
ተከድነው የሚንተከተኩ የአማራ ህዝብ የ6 ዓመታት አሳሮች ገብያው መድራት "ያላዋቂ ሳሚ ነገር" ያመጣው ጎለጎታ ነው። ወይንም ያለልኩ የተሰፋ ቦላሌ መሆኑ ላይ ነው። አቅም + ቅቤዓ + እርጋታ። ፖለቲካ መማሩም፤ መስራቱም፤ መቆርቆሩም ብቻ ለድል አያበቃም። ሚስጢር አለው። ቅብዓ ይጠይቃል። ዊዝደም ይጠይቃል። ስልት ይጠይቃል። ብልህነት ይጠይቃል። እርጋታ ይጠይቃል። አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ አይሆንም። ቁጭ ብሎ መሥራትን ይጠይቃል። በየቦታው እንደ ድመት አራስ መመድም ሳይሆን የያዙትን ጠበቅ አድርጎ መሥራት ይጠይቃል። የሰው ግብር ሰርክ? የሰው ላብ ዘወትር፤ የአቅም ፍሰት ብክነት፤ ተጀምሮ እስኪጨረስ መንበር ሥሩልኝ መገራት ይኖርበታል። ከሁሉ ምን አተረፍኩ ቀዳሚ የራስ በራስ ጥያቄ ሊሆን ይገባል። እራስን ማረም ልቅና ነው። የተማገድልነትን ተጋድሎ እኮ በማዶ የተመለከትነው የኮነሬሉ ብዛት እስኪ እንዬው ብለን ነበር። እንጂማ………
 
አቅም የሚያስመካው በራስ ጥረት የተገነባ ነው። የሰው የትውስት ከሆነ ይናዳል። ቀዳዳ በቀዳ ይሆናል። ሲጀመርም ነዳላ ስለሆነ። መሪነት ቅልሞሽም፤ ገበጣም፤ ሰኞ ማክሰኞም ጨዋታ አይደለም። ወይንም የእብድ ሃሙስ የሰርግ ውሎ አይደለም። እብድ ሃሙስ ለሁዳዴ ፆም መግቢያ የመጨረሻው ሃሙስ ነው። ያ ሁሉ እርድ፤ ያ ሁሉ ፌስታ ያጠረ ቀን ብቻ ስለመኖሩ አመላካች ነው፦ የእብድ ሃሙስ ሰርግ።
በሌላ በኩል መሪነት ግጥግጥ እና ቅልቅልም አይደለም። ይህ በሞድ ትዕይንት በበለፀገው የጠቅላይ ሚር አብይ ያሉትን ሁሉም 11 ይሁኑ 12 መስተዳድሮች፤ ሁለቱን ምክትል ጠ/ ሚ፦ ሁለቱን አፈጉባኤ፤ አንድ ከንቲባ፤ ጉልቻቸውን የራሳቸውንም ይዘው የሰርክ ድግስ ላይ እንዳሉትም አይነት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም የወል የምቾት ጉዞ አይደለም። ሳስበው ሞትም ቢመጣ ለዘር አንብቃ ዓይነትም ይመስላል። የኢትዮጵያ የመሪነት ጥሪ እና ተስፋ አልተግባባም። ገና ነው ገና። 
 
ከሁለት ዓመት በፊት በአማራ ትግል ላይ በጓዳ ለሚመጡ ወጣት ታጋዮች ጋር ሰፊ ሙግት ነበረኝ። ከዚህ ሁሉ ጥፋት ትድኑ ዘንድ ነበር በእርጋታ ረጅም ጊዜ ወስጄ ሳስረዳችሁ የነበረው። አሁንስ ገባችሁን? አጀማመሩም፤ አያያዙም የፖለቲካ ፓርቲ የአደረጃጀት መርህን የጣሰ ስለነበር ብቻ ሳይሆን ሂደቱ የተመክሮም ስስነት ስለነበረበት ነው። 
 
ብዙ ያልተነገሩ ስኬቶች ምንጫቸው አንድ ህይወት ሳይገበር፤ በቀላል ወጪ እና ተከታታይ ትጋት፦ አንዲት ቅርስ ሳትወድም፤ አንድ የህዝብ አገልግሎት ሳይስተጓጎሉ በዝምታ በዝመተኛው ማህበረሰብ የተከወኑ ነበር። ዛሬ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) ስለ ሥርዓት ለውጥ ባለአቅም ባለቤትነቱን የሚነግረን በመድረክ ላይ ባሉ ዲስኩሮች ወይንም የወል ሞገዶች የተከወኑ አልነበሩም። ዝምታ በዝምታ የዝምታ ስኬት ነበሩ። ከእሱ በኋላም ጦፈው የወጡ ስንክሳሮች ሰከን ያሉት የአጃቢ ሠራዊት በገፍ ባላቸው አልነበረም። ወደፊትም እንዲሁ። ሁሉ በልኩ ለልኩ እንዲሆን አበከረን እንመክራለን። ትምክህት ለማንም ስለማይበጅ። 
 
እኔ አማራ የማንነት እና የህልውና ሁለት ግዙፍ ትግል አለበት ብዬ ነው እማምነው። ለዚህ ድርብ ትግል ወርድ እና ቁመናው የማይመጥን፤ ከትርፍ ኪሳራን እያባዛ የሚገኝ ሰብዕና ሁሉ በውጭም ይሁን በአገር ውስጥም ያለ ጥሞና እስኪ ውሰዱ እና ኪሳራ እና ትርፋን መዝኑት። መመለስ ከቻላችሁ እነኝህን የተሰው ሰማዕታት ትግታጎች መልሱልን???? ስለታሰሩትም፤ ካቴና ላይ ስላሉትም፦ ስለታገቱትም፤ ሰማዕትነት ስለተቀበሉትም እስቲ ትጉ? 5 ሚሊዮን ተማሪ ከትምህርት ውጪ? ምን ማለት ነው ይሄ? ቋያው ውስጣችሁ አልደረሰም። ዲል ባለ ደጋፊ ምን በመሰለ ስቴዲዮ በተዘናከተ ሳሎን እና መናፈሻ፤ ፈሰስ ባለ ሥልጡን መኪና??? 
 
ለምን ስለምን ሙሉ የተጋድሎ አድማሱ ቀዘቀዘ ብላችሁም ጠይቁ። አደብ። ስክነት። የአማራ ህዝብን ህይወትን የዝብሪት ቤት አታድርጉት እባካችሁን????
 
ውቦቼ ውዶቼ እንዴት አደራችሁ የኔወቹ። ፎቶወችን ተመልከቱ። ድቀቱን ለኩት። ጥፋቱን መዝኑት። ተስፋን እዘኑለት። ለማግስትም እሰቡ። ትእዛዝ አይደለም የባተሌ እይታ ነው። ክቡር ሰማዕት አንዱአለም ዳኜ ውስጤን ፈተነው። መተኛት አልቻልኩም። ያቺ ቅኒት የአማራ እናት ጉዳይ አንጀቴን በላው። ከፋኖ ንቅናቄ በኋላ ትንሽ ገርበብ ያለ ዕይታዬን ነው ያቀረብኩት ለዛሬው። አንድ ጊዜም ፋኖ ለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴሉ፤ እናቱም አናቱም በማለት አውድዮ ከሰራሁት በስተቀር ዝም ምርጫዬ ነበር። ዱር ቤቴ ያሉትን መጉዳት ስላልፈለግሁኝ። ሊንኩን እለጥፋለሁኝ። ለእኔ የሚበልጥብኝ የግለሰብ ሰብዕና ግንባታ ሳይሆን ቀራኒዮ ላይ ያለው የአማራ እናት ማህጸን፤ ጎለጎታ በር ላይ የሚገኜው የአማራ አባት አብራክ ነው። ፈጣሪ አላህ ይርዳን። አሜን። 
 
እኔ ግን በአማራ ህዝብ ህልውና ብቻ ሳይሆን የትምህርት ጆኖሳይድ፤ የሃብት ማፍራት ጆኖሳይድ፤ የሥልጣኔ ጆኖሳይድ፤ ህዝብ የመቀነስ ጆኖሳይድ ተፈጽሞበታል ብዬ ነው እማምነው። ልል ዕሳቤ የለኝም። ቅጽበታዊነትም ይህን መከራን ያሸንፈዋል ብዬ አላስብም። ለዚህ የሚመጥን ቀን ለአማ እናት እንዲመጣላት እጸልያለሁ። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ስኬት ይመጣል። ለዚህም የበዛ ትእግስት። አባ ቅንዬ አማራዬ አይዞህ!!!!
 
የአመራር ብቃት መለኪያ ስኬት ይሁን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን። 
 

·       https://www.youtube.com/watch?v=EyZE2-zczT8&t=981s

ፋኖን ወደ አንድ ዕዝ ማዕከል ማምጣት ይቻል ይሆን?

·        

 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/02/2025
የአማራን ሊሂቅ ማራቆት ይቁም!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?