ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 8, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዕብለት ተደርሮ።

ምስል
ምሬት። „ቃልህን ወደ ደመናት ታነሳ ዘንድ ትችላላህን።?“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፴፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                             ልታነጋ የመሸብህ … የሞት ቀጠሮ በስሌት ተቀምሮ ነገን አሳምሞ በሃሞት ተሮሮ ዕውነትም ተማሮ እንዲህ ተክኖ አሮ የሽንገላ አውራ ዶሮ፤ ስላቅን ሰንዝሮ የዝበት መርዶን ድሮ የዕብለት ድርድር በቀረርቶ ተደርሮ። https://www.youtube.com/watch?v=AhlL80R74h4 Ethiopia: የኢንጂነር ስመኘው ሞት ዝርዝር የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ !! [ እራሱን አጠፋ ?] ድንቄም ስንታዬን መግለጫ፤ ለኮሜዲነት ይልቅ ይመቻሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ …. ·        ሥጦታ ለምስክኔታ ሙያዊ የሚዛን ርትህ። ዕውነት ስተፈጠር ማዬት ሽው አለኝ።  

የችሎት ህልፈት...

ምስል
              እስከ ህልፈት ያልቀጠለ የዜግነት ክብር …       የችሎት ህልፈቱ። „የሰጎን ክንፍ በደስታ ይንቀሳቀሳል፤ ነገር ግን ክንፍና ላባዋ ጭምተኛ ነውን?“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የችሎት ህልፈቱ መውደቅ ብልሃቱ የችሎት ንቅዘቱ በዕብለት መፈታቱ የችሎት ጭላጩ ዕውነት መደፋቱ የችሎት ራህቡ ሚዛን ማጣፋቱ የችሎት ጥማቱ ጠያቂ ማጣቱ። ·        ሥ ጦታ ርትህ ለጠማት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ይሁንልኝ። መኖርን ያከበረ ዘመን ይናፍቀኛል። የኔዎቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።

በልጥ መወራረድ? ህም - እም - እህ!

ምስል
ዕውነትን የሚገልጸው ዕውነት እራሱ እንጂ ዓዋጅ አይደለም። „እያሱም ህዝቡን፤--- እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፤ እርሱ ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሄርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላላፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።“ መጽሐፈ እያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ባለወረፋው ቆፍጣናው ጎንደሬ! ·        ልብ ሊሰጠው የሚገባው የዕውነት አደባባያዊ ፍርድ - በልጥ ተወራረደ። https://www.youtube.com/watch?v=AhlL80R74h4 Ethiopia: የኢንጂነር ስመኘው ሞት ዝርዝር የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ !! [ እራሱን አጠፋ ?] ድንቄም ስንታዬን መግለጫ፤ ለኮሜዲነት ይልቅ ይመቻሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ …. ከአብይ ሌጋሲ የማልጠብቀው እንግዳ ነገር ነበር መግለጫው። የግፍ ችሎት ነበር ፍርዱ። ደመከልብ። ልክ እንደ ፕ/ እምሩ ስዩም። እሳቸውም ተከሳሽ አልነበራቸውም። ችሎቱን ሰጪው ሞት የግፍ ብቻ ነወብ። የሆነ ሆኖ በቆሞስ ስመኘው በቀል አሟሟት ከጅምሩ ሂደቱ የሰጠኝ ጭብጥ ግብረ ምላሽ ቢኖርም ትንሽ ብጣቂ የሚመስል ተለጣፊ ማሰተባባያ ጠብቄ ነበር ግን በረዶ ለቀቀበት። እግዚኦ! ብላለች ልዩ የመንፈስ፤ የታማኝነት ወዳጁ ሥርጉተ ሥላሴ በዘመነ አብይ።  … ከአብይ ሌጋሲ ታማኝነቱን የሚያሰተጓጉሉ ለጠፎች ቁሮዎች ወይንም ቀዳዳዎችን ማድመጥ አልሻም።  እርግጥ ነው ፍጽምና አልጠብቅም፤ ግን በዜግነት እኩልነት ላይ ድርድር አላውቅም። ሲሶ እርቦ ዜግነት መሮኛል፤ ተመልሰሽ ያን ከርቤ እና ሃሞት ተጎንጪ ደግሞ ህልፈቴን መራራ ያደርገዋል። ሞትን ፈርቼው አላውቅ...