ለእናት #ቋሚ የዕንባ ቋት መሆን ከምን ይመደብ ይሆን? ግን እቴጌ ጎንደር ስለምን #የበቀል መሞከሪያ ጣብያ ሆነች?
ለእናት #ቋሚ የዕንባ ቋት መሆን ከምን ይመደብ ይሆን? ግን እቴጌ ጎንደር ስለምን #የበቀል መሞከሪያ ጣብያ ሆነች? እግዚአብሄር በሚያውቀው ሚስጢር በዘመነ ኢህአዲግ የነበሩ አንቱ ሊቃናቶቿ አልቀዋል። በፋኖም በብዛት መሪወቿ አልቀዋል። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፱። እንዴት ሰነበታችሁ ክብረቶቼ? ይህን የመከራ ዜና የሚሰማ መምህር፤ ቤተሰብ እናት፤ አሳዳጊ በተለይ ሰርክ ዕንባ የታወጀለት #የህክምና #ፋክልቲ እንደምን ያስተናግደው ይሆን? ሰርክ ከእነኝህ ንጹህ ሆነው ከተፈጠሩ የህክምና ባለሙያወች፤ እጩወች ላይ ስለምን የበቀል ዱላ ተበራከተ? ከውስጤ ፈጽሞ ሊወጣ ያልቻለ የህክምና ሊቅ አለ። ሁልጊዜ የዶር አንዷዓለም ዳኜ ፎቷቸውን አየዋለሁኝ። ከህሊናዬ ሊወጡ አልቻሉም። ታትመዋል። #ግን ጎንደር ከተማ ማን ይሆነው መሪዋ? በኢትዮጵያ መማር፤ ጥበብን መፍቀድ፤ ስፖርትን መውደድ፤ ሙዚቀኛ - ተዋናይ - ጋዜጠኛ ጸሐፊ መሆን፤ ወይንም ፖለቲከኛ መሆን፤ ሃኪም መሆን፤ #ሰው ሁኖ መፈጠር እራሱ መከራ ነው? እንደምን ይህ #ሰንሰለታማ #የቂም እና #የበቀል ሂደት ሊቆም እንደሚችል አላውቅም። በጣም ብዙ፤ እጅግ ብዙ በህክምና ዙሪያ የሚተጉ ተደግመው የማይገኙ የህክምና ስፔሻሊስቶች ልክ እንደ ዶር አንዱዓለም ዳኜ ዓይነት #በስጋ ተለይተዋል። በሰው እጅ #ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። በርካታ ትዳር ፈርሷል። በርካታ ልጆች ያለአባት ወይንም ያለ እናት ቀርተዋል። ለዚህ ጉዳይ ብቻ ጸሎት፤ ሱባዬ ያስፈልጋል ብዬ የፃፍኩትም ከዚህ ቀደም ለዚህ ነበር። #ይህ አንድ ሃዘን ብቻ አይደለም። ጎንደር እንደ ልማዷ #...