ህይወት ያለው ሁሉ #ይተነፍሳል። ይህን መዝጋት ከሰጪው ከፈጣሪ ጋር #መጣላት ነው።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፱።
#እሺ! አይዋ ብልፄው እንዴት ሰነበትክ?
ፌስታውስ እንዴት እያደረገህ ነው?
ብልፄውሻ ደስታው እንዴት እያደረገህ ነው? ጥምር ደስታ 100%: ፓርላማህን ጠቅልለህ ቁብ አልክበት። አባ #ጠቅልልነት በተዘዋዋሪ። ከዚህ እዚህማ ሞናርኪያዊ ለምን አታደርገውም ሥርዓትህን? የምሬ ነው። ተረብ አይደለም።
የሚገርመኝ ደግሞ በለስ ይቀናኃል ፮ኛው ምርጫ ኮረናና ጦርነት፤ ፯ኛው የሆርሙዝ ሰርጥ ፈተና ለአንተ ኮረቻ ድልዳል ሆነውልኃል። በዚህ ውስጥ ስጋት - ጭንቀት - #ይመርጥኃል። ሌላዋ ዲል ያለ ደስታ በነገረ ህወሃት ላይ ደግሞ አገኜህ፤ ቀንቶኃል።
ነገረ ህወሃትን የመቋቋም አቅምህ ግን #አቅቶህ ነበር። ሁለቱንም የምርጫ ሥርዓት ባን ሆኖበኃል። ኮሪደር ሎጂ ብሎ ነገር እዛ እንዳታስብ አድርጎህ ነበር። ትውር ለማለትም፤ ለማዘዝም ጋራ ነበር።
ግን አንድ ትሁታዊ ጥያቄ አለኝ። ስንት #እስር ቤት ለመስራት አቅደሃል? ምን ያህል የኮሪደር ልማት በቅሊንጦ፤ በገላን፤ በዝዋይ ለመሥራት ተልመኃል? የአዲስ አበባው የቢላ እስር ቤቶችህ ያው በአዲስዬ #የመናፈሻ ፕሮጀክት ቅምሻ ቢጤ አላቸው ብዬ ነው። ጠበለ ጣዲቁ ይደርሳቸዋል እንደማለት።
ብልፄው ቆይ እስቲ! ግን አንተ ማሰር - ማፈን - #አይሰለችህም? በቃ! መደበኛ የእስር ሂደት ሥራህ ሆቴል የመሥራቱ ያህል ከቀለለህ ቅልጥፍና ጋር #በአቻነት እያስኬድከው ነው። በድሬ አንድ እጩ ተወዳዳሪ ዶር #ሃኪም ማሰርህን ሰምቻለሁኝ። ማህከነ።
ሌላ ደስ የምትል ለዛ ያላት፤ ቃናዋ የሚጥም ለግላጋ ደመ ግቡ ወጣት የራስህ የሚዲያህ #ጋዜጠኛም ማሰርህን ሰማሁኝ። እግዚኦ! ነው የፍራትህ ጣሪያና ግድግዳ ይናገራል ያናግራልም።
እንዲያው ……… እንዲያው በአዲሱ ፓርላማህ #ማሰር ተዕቅድህ ውስጥ ይኖር ይሆን? ያው በጀት ስለሚጠይቅም? በሌላ በኩል ሃሳብ ፈሪ ስለሆንክ #ማሰር ለአንተ የቧንቧ ውሃ የመክፋትና የመዝጋት ያህል ቀላል ሥራ ነው። ግን እሰከ መቼ???
#በነፃ አገር፤ በነፃ #የተወለደን ሰብዕና ሰርክ ሙሉ ፰ ዓመታት ማሰር፤ ማፈን፤ ማገት፤ ማስፈራራት፤ ማግለል፤ ስጋት #ማደራጀት ምን ያደርግልኃል? በሰው ልጅ ስቃይ እና እንግልት፤ በእናቶች ዕንባ እና ምሬት ውስጥ ተስፋን ማዝለቅ ይከብድኃል። በሌላ በኩል ጭካኔ ሥልጣኔ አይደለም። የጭካኔ ተራማጅነት የለም።
ብልፄው #አትፍራ! ደፈር ብለህ ለመምራት ቁረጥ! ሁሉን ይዘህ ይህን ያህል ሃሳብ የሚያስፈራህ፤ ሃሳብ የሚያርድህ ከሆነ ከአንተ እኩል ያሉት ተቀናቃኝ አገራትን እንደምን መመከት ትችል ይሆን? የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ጫን ያለ ነገር ቢመጣ? እኔ እያሳሰበኝ ያለው ይህ ነው። ኢትዮጵያ እንድትኖርልኝ እፈልጋለሁኝ። #ትርታዬ ናት። ኢትዮጵያ ለእኔ ባጣ ቆየኝ አይደለችም።
ብቻ ብልጽሽ #ተኝተህ እሰበው። ማሰር #መጠቃት ነው። ማሰር #ፈሪነት ነው። ማሰር የሃሳብ ብቃት #የደም ማነስ ሲይዘው የሚከሰት ነው። ኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ አገር መባሏ #ሊኮሰኩስህ ይገባል።
ነፃነትን መንጠቅ፤ ነፃነትን መዝረፍ፤ ነፃነትን #ቁምስቅሉን እንዲህ ማሳየት እርግማን ያመጣል። ባዶነትን ያስተቃቅፋል። ከህወሃት ተማር። ከሁሉ የሚያስፈራው ምርቃት እንጥፍጣፊ አልባ ሲኮን ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን። የእስረኛ ቤተሰቦችን ፈጣሪ ጥንካሬ ይስጥ። አሜን።
የፖለቲካ እስረኛ የማይኖርባት ኢትዮጵያ አብዝታ ትናፍቀኛለች።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
20/06/026.
ፍትህ! ተናፍቀኃልና ና ወደ እኛ። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ