30የተኛ ሸክም ዘመን። በለሽታ ልምሻ አሻራ፤ በአልቦሽ ሌጋሲ ለለሽታም አሸኛኜት ……… ተቀለደ። ነገ ደግሞ ገራገሩ አማራ ያልተዘመረለት ትለን ይሆናል፤ ልታጀግን ስትፎክር ትገኝ ይሆናል፤ መጥኔ ብለናል።
30የተኛ ሸክም ዘመን። በለሽታ ልምሻ አሻራ፤ በአልቦሽ ሌጋሲ ለለሽታም አሸኛኜት ……… ተቀለደ። ነገ ደግሞ ገራገሩ አማራ ያልተዘመረለት ትለን ይሆናል፤ ልታጀግን ስትፎክር ትገኝ ይሆናል፤ መጥኔ ብለናል። ሲነሪቲ መነቀል ለስሜናዊ ፖለቲከኞች እንጅ ማህበረኦነግን አይመለከትም። አዛውንት የኦነግ ፖለቲከኞች አሁንም ሥልጣን ላይ ናቸው። ስለዚህ መተካካት የሚለው የኮኔፊውዝድ ዕሳቤ የድቡሽት ቤት ይሆናል። የሆኖ ሆኖ ዘመናቸው በልዝ እንጨት የምመስለው የአቶ ደመቀ መኮነን ሽኝት ወይ አይነድ ወይ አያነድሆኖ የባከነ ዘመን ነው። ለትውልድም አብነት የማይሆን ያልሆነም። የምዕራፍ ፲፩ ማጠናቀቂያ ወጋወግ። እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም እንዴት ነን? አቶ ደመቀ መኮነን ሙሉ 30 ዓመት በቅኑ ዬአማራ ህዝብ ውክልና፦ በተደላደለ ኑሮ እና ምቾት ቤተሰባዊ ኃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተው፤ ለዛ ክብር እና ልዕልና ላበቃቸው ፍፁም ደግ፤ ፍፁም ሰው አማኝ፤ ፍፁም አክባሪ የአማራ ህዝብ ከቀዩ በዬዘመኑ መነቀሉ አልበቃ ብሎ፤ በድሮን ጭፍጨፋ እንዲያልቅ፤ ገዳማውያን በገፍ ሲገደሉ፤ ልጆች በወጡበት ሲቀሩ፤ ህዝብ በስጋት ረመጥ ሲቀቀል፤ በጠኔ ሲርገበገብ፤ እሳቸው ከገበርዲናቸው ጋር ይቆለማመጣሉ። የአማርን ህዝብ በግዞት ይኖር ዘንድ፤ ተተኪ እንዳያፈራ ቀንበጥቹ ለሁለገብ አሳር ሲዳረጉ፤ በድህነት ለመኖር ሰላሙ ሲነጠቅ እዬኖሩ ያልኖሩም ያላኖሩም ሰው ናቸው አቶ ደመቀ መኮነን። ተንሳፋፊም ነው የነበሩት። በእንድም ዬኮሚቴ ሰብሳቢነታቸው ውጤታማ አልነበሩም። የሚገርመው ዛሬ ከአለምንም ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በሽልማት ተንሳፋፊነታቸው ባለማህተም ሆኗል። #ሲነሪቲ የሚባል ደመኛ ያላቸው ጠቅላይ ሚር አብ...