ብአዴን ከኦዴፓ አሸብሻቢነት ወጥቶ ራሱን ችሎ ለመቆም ይታጋል።
እንኳን ደህና መጡልኝ ብአዴን ከኦዴፓ አሸብሻቢነት ወጥቶ ራሱን ችሎ ለመቆም ይታጋል። „እግዚአብሄር የጽድቅ ጋሻዬ ነው፤ ልበ ቅንችን የሚያድናቸው።“ መዝሙር ፮ ቁጥር ፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። · መ ግቢያ። እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ የኔዎቹ? ማምሻ ላይ ላይ በፈረንሳይ አገር አንድ ጥንታዊ የሃይማኖት፤ የታሪክ፤ የትሩፋት የትውፊት ቅርስ የሆነ የዓለም ጦርነቶች እንኳን ድርሽ ያላለበት ታላቅ የጥብብ ጉልላት የሆነው ኖትር ዳም የካቶሊክ ሃይማኖት ካቴድራል እሳት ሲበላው አዬሁኝ። በሀዘን ሰመጥኩም። አስከ መንፈቀ ሌሊት ላይፍ ይተላላፍ ስለነበር አብሬ መንፈሴን አሳደምኩት። ህዝቡ በሀዘን ድባብ ተሞ እርእስ በእርስ ተደጋግፎ እና ተቃቅፎ ሲጸልይ ተመለከትኩኝ። ይህ ዓለም አቀፍ ቅርስን እያስብኩኝ የስሜን ተራራችን ቃጠሎ አዋደድኩት፤ ከዚህ ጋር የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የላሊበላ ጉዞ እና የአውሮፕላኑ አደጋ የጥቁር ሳጥኑን የምርምራ ገጠመኝም በነፍሴ ቃኘሁት። አንድ ያስተሳሰረን መንፈሳዊ ነገር እንደለ አሰተዋልኩበት። ይህ ቃጠሎ በሰለጠነው ዓለም የሆነ በመሆኑ ርብርቡ ጠንካራ ነበር። ማተረፍ የተቻሉ ቅርሶች እንደሉ አዳምጫለሁኝ። ፕሬዚዳንት ማክሮንም መልሶ ለመገንባት እንደሚቻል እልህና ቁጭት ባለው ሁኔታ ተናገረዋል። እግዚአብሄር ምህረቱን ይልክልን ዘንድ መማጸን ይገባል። ትናንት ለካቶሊክ ሃይማኖት የሆሳዕና ቀን ነበር። ዛሬ ህማማት። ቀጣዩ እሁድ ደግሞ ትንሳኤ። https://www.citynews1130.com/video/2019/04/15/fire- ...