ብአዴን ከኦዴፓ አሸብሻቢነት ወጥቶ ራሱን ችሎ ለመቆም ይታጋል።

እንኳን ደህና መጡልኝ
ብአዴን ከኦዴፓ 
አሸብሻቢነት ወጥቶ
ራሱን ችሎ
ለመቆም ይታጋል።
„እግዚአብሄር የጽድቅ ጋሻዬ ነው፤
ልበ ቅንችን የሚያድናቸው።“
መዝሙር ፮ ቁጥር ፲
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


·       ግቢያ።

እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ የኔዎቹ? ማምሻ ላይ ላይ በፈረንሳይ አገር አንድ
ጥንታዊ የሃይማኖት፤ የታሪክ፤ የትሩፋት የትውፊት ቅርስ የሆነ የዓለም ጦርነቶች
እንኳን ድርሽ ያላለበት ታላቅ የጥብብ ጉልላት የሆነው ኖትር ዳም የካቶሊክ 
ሃይማኖት ካቴድራል እሳት ሲበላው አዬሁኝ። በሀዘን ሰመጥኩም። አስከ መንፈቀ
ሌሊት ላይፍ ይተላላፍ ስለነበር አብሬ መንፈሴን አሳደምኩት።

ህዝቡ በሀዘን ድባብ ተሞ እርእስ በእርስ ተደጋግፎ እና ተቃቅፎ ሲጸልይ ተመለከትኩኝ። ይህ ዓለም አቀፍ ቅርስን እያስብኩኝ የስሜን ተራራችን ቃጠሎ አዋደድኩት፤ ከዚህ ጋር የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የላሊበላ ጉዞ እና የአውሮፕላኑ አደጋ የጥቁር ሳጥኑን የምርምራ ገጠመኝም በነፍሴ ቃኘሁት። አንድ ያስተሳሰረን መንፈሳዊ ነገር እንደለ አሰተዋልኩበት።

ይህ ቃጠሎ በሰለጠነው ዓለም የሆነ በመሆኑ ርብርቡ ጠንካራ ነበር። ማተረፍ የተቻሉ ቅርሶች እንደሉ አዳምጫለሁኝ። ፕሬዚዳንት ማክሮንም መልሶ ለመገንባት እንደሚቻል እልህና ቁጭት ባለው ሁኔታ ተናገረዋል። እግዚአብሄር ምህረቱን ይልክልን ዘንድ መማጸን ይገባል። ትናንት ለካቶሊክ ሃይማኖት የሆሳዕና ቀን ነበር። ዛሬ ህማማት። ቀጣዩ እሁድ ደግሞ ትንሳኤ።

·       አቅም።

በዬዘመኑ የራሱን ቤት እያነደደ የሰው ቤት፤ የሰው ታሪክ፤ የሰው ልዕልና ሲገነባ የኖረው የኢህአፓ ቅርንጫፍ ብአዴን ወግ ደርሶት አቅሙን ለማጎልበት ቢታትር መልካም ነው። 
ለኦዴፓ አሸብሻቢነት ከፍ እና ዝቅታ ከሚባዝን።

በዬዘመኑ ጃንጥላ ያዢ ሆኖ የሌላን ድርጅት ልዕልና፤ ገመና ለመከወን ደፋ ቀና ከማለት እወከልዋለሁ ለሚለው ህዝብ ነፍስ ያለው አቅም ገንብቶ መብቱምን ክብሩንም ሊያስጠብቅ ይገባል። በ አስሱ ዳተኝነት ነው ህዝብ ይህን ያህል ሶቆቃ አባቶቹ ባበጇት
አገር በቁርሾ እዬደቀቀ ያለው፤ በስጋት እዬተናጠ ያለው። 

አሁን በዓለም አቀፍ መድረክ ዝናን ያተረፈው ኦዴፓ እንጂ ብአዴን አይደለም።  
ዕውቅና የለውም ብአዴን። እንዳይኖረውም በህብረት ከዛሬ ባለቀለበቶች ጋር በትትርና ተሰርቶበታል። መሬት ላይ ደግሞ ገመና ከዋኙ ይኽው ድርጅት ነው አይዋ ብአዴን።

ስለሆነም አቤቶ ብአዴን ዓመቱን ሙሉ ለኦዴፓ ልዕልና፤ ንግሥና፤ ዕውቅና፤ 
ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ሌት እና ቀን ሲታትር የነበረውን ገመናው ወደ ጎን ተወት
አድርጎ የራሱን አቅም አጎልብቶ አዎንታዊ ተፎካካሪ፤ አዎንታዊ ተጋዳደሪ፤ 
አዎንታዊ አቻ ድርጅት ሆኖ ለመውጣት ከሰንበሌጥ አቋሙ ወጥቶ ከብረት
ቁርጥራጭ የተሰራ ጥንካሬን አምጦ መወለድ ይኖርበታል። ኦዴፓ ከውጭም 
አገር ውስጥም ፡ያስገባቸውን ሊሂቃኑ ቦታ በመስጠት ጥድፊያ ላይ ነው ያለው፤
አማራ ክልል ዩንቨርስቲዎች ሳይቀር። እሱ ደግሞ ለሽ ብሎ ተኝቷል። 

ብአዴን ዘመን ሳያስተምረው የሁሉንም ገመና ከዋኝ እና ሸካፊ ሆኖ እድሜ ልኩን ያረጀበትን የተነጣፊነት አመሉን ከባህር ከገደል ጥሎ ራሱን ችሎ መውጣት እና 
ይህ አገር ምድሩ አይባቅኝ ብሎ የሚፏልለውን የኦነግ መንፈስ ቅጥ ሊያስይዘው
ይገባል። ማሽሞንሞኑም፤ ማሽቃበጡም፤ ማንቆለባበሱም ሊበቃ ይገባል!

የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጎሹ እንዳላማው እና የአብን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ 

በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ውይይት


ብአዴን አቅመ ልፍስፍሶችን ከዬት እንደሚያሰባስባቸው አላውቅም። ሰሞኑን
 አስራት ሚደያ አንድ የብአዴን አመራር እና አንድ የአብን አመራር ጋር ቃለ
 ምልልስ ነበራቸው። 

ብአዴን የማንን ጎፌሬ እያበጠረ ስለመሆኑ ቁልጭ ብሎ ይታያል። የት ይሆን እንዲህ ያለውን የነፈዘ ነፍስ የሚያገኘው? አሁን ለ አብይ ሌጋሲ ዛሬ ላይ አማራ ምን አገኘሁ ብሎ ይሆን ይህን ያህል የሚሟገትልት፤ እና የሚሸፋፍንለት። ነጻነት 20 ሺህ አማራ ታስሮ፤ ሺዎቹ ሙተው ተጨፍጭፈው፤ ተሰደው፤ ጥፍራቸው ተነቅሎ፤ የዘር ማፍሪያቸውን ገብረው የተገኘ ድል ነው።

ብጣቂ ከኦዴፓ የተገኘ ቆራጣ ችሮታ የለም። እኛ ለራሳችን አናንስም። ጥገኛ
 የሚያደርገን ምንም ነገር የለም። ምን እንዳለን፤ ምን እንደምንችል ራሳችን
 የምናውቅ ህዝቦች ነን። ሁላችን ጥርት ያለ ተግባር የማያሰፈር ድርጊት 
ከውነንበታል ለነፃነታችን። በሌላ በኩል ወገኖቻችን ናቸው ብለንም መታመናችን
 የክህደት አቆማዳ ሆኖ ተንጠልጥሎ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ እንጂ። ስለ እነሱም መስክረናል።

የአብይ ሌጋሲ ከመቅደሙ ችግሩን አያምነበትም የአማራ ህዝብ መሰረታዊ 
ጥያቄዎችን። የማንነት እና የወሰን ኮሚሽን አቋቋምኩ የሚለው ኮሚሽን
አንቅልፍ መርፌ ነው ለዛውም ከገዳዮቹ ነው ፍትህ ጠብቁ የተባለው። ራሱ ይህ
ድፈረት ስለመሆኑ ብአዴን አይገባውም። ከዶ/ር አረጋይ በርሄ ርትህ? 
መሳቂያነት ነው። ህወሃትን ሸኝቶ ለሌላ ህወሃት ዘውድ ደፍቶ ሰሞኑንም አይተናል።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ እና የብአዴኑ አቶ ጎሹ እንዳላማው የሚሰጡት መልስ ያቅለሽልሻል፤ ይገለማል። ወዳጄ አቶ ጎሹ እንዳላማው ኦዴፓ ለኦነግ መንፈስ ነው
 ቀን ከሌት እዬሠራ ያለው። የኦነግ መንፈስ ደግሞ አማራዊ ስሪትን መንቀል ነው። የበታችንት ስላለበት። አንድ ቀን ይጸጸተወታል። ማጎብደዱን በልክ … ይሁን እሺ። ማጎበደዱን ግን ከማን ከቶ ከዬት ተማሩት? እግዚኦ!

የኦነግ መንፈስ እውን ሆነ ማለት ደግሞ አማራ ለዳግም መቃብር ተሰናዳ ማለት ነው። ይህም እዬታዬ ነው። ቅርስ ውርስ እዬነደደ ነው። አማራነት መጥፋት ብቻ ሳይሆን ይቀጣላል። ምክንያቱም የበታችነት ያለበት ነፍስ ሁልጊዜም ሰውኛ አይደለምና። 
ለነገሩ ሰው ገድሎ እኮ እሬሳ መቃጠሉንም እያዬን እዬሰማን ነው በዘመናችን። ቤተመቅደሶችም እዬነደዱ ነው። 

ይህን አሽኮኮ ብሎ ላይ ታች ማለት በውነቱ ሬሳነት ነው። አማራ በርካታ ሊሂቃን
አሉት። እነዛን ሊሂቃን በማሰባሰብ እና በማደራጀት፤ ቦታም በመስጠት ብአዴን 
አቅሙን አጎልብቶ በመውጣት ኢትዮጵያ ከተደቀነባት መከራ ሚዛን አስጠብቆ
 መጓዝ የሚቻለው ከሁልጊዜ እሺታ ብአዴን ወጥቶ አሻም፤ እምብኝ፤ አይሆንም
 ሲል ብቻ ይሆናል። ብአዴን ኦዴፓም ይሞግተው። 

በምንም ታምር ኦዴፓ ለብአዴን የነፍስ ወዳጁ ሊሆን አይችልም። መስሎን ነበር
ግን አለቅት አለቀት ነው። እኔ በታሪክ አማራን ያቀረበ ድርጅት ኦህዴድ 
እያልኩኝ ስጽፍ ነበር ግን ለቅበረኝ ነበር ዬተተጋው።

እስኪ አንድ የኦሮሞ ሊሂቅ፤ አክቲበስት፤ ጸሐፍት፤ ጋዜጠኛ ስለ አንድ አማራ ሊሂቅ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ጸሐፍት ሲመሰክር አውቅና ሲሰጥ መረጃ ይቀርብ። እኛ ጅሎች
 ነን። የሰው ቤት ስንሰራ ነው የባጀነው። አይበቃም ወይ?!

አሁን እኔ አንድ የትግራይ ወጣት ርግታቸውን እወድላቸዋለሁኝ አቶ አምዶምን ግን
አሁን ከሆነ ተቆጠብኩኝ። ቅጣቱ በዛ፤ ይሉንታም የለም። አንድ ሊሂቅ ብቻ ነው
ኢትዮጵያ ስለ አማራ መስካሪ ያገኘቸው። በ50 ዓመት ሙሉ። የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጦፋ ኡመር ብቻ ነው። ይህ መንገድ ብቻም ነው የኢትዮጵያ መድህን።

ይህን መንገድ አለሁበት ብሎ የሸፍጥ ጉዞ የጀመረው የአብይወለማ ጉዞ እክል 
በእክል የሆነውም ከእውነት ውስጥ ስላልነበረ በፅናት መቀጠሉ አቅሙ አልፈቅድ
 አለ። ካለልኩ የተሰፋ እጀ ጠባብ ሆነ ኢትዮጵያዊነት። እውነትን
 መደጋገም ይቻላል። ሃሳትን ግን ደግሞ መግለጽ አይቻልም። እውነት አትረሳም፤
 ሀሰት ግን ወዲያው ትረሳለች። 

ሁሉን አይቷል ብአዴን። ያለዬው መከራ የለም። ስለሆነም ቢያንስ አሁን ራስን
ችሎ ቆሞ አቅምን ማሳዬት የሚገባው ይመሰለኛል።

አየር መንገዱን በተመለክት የተሟላው መረጃ ይሄ ነው!!! (ወንድይራድ ሀይለገብርኤል)
የሃገር መከላከያው ሴክተር ላይ ተደረገ የተባለውሪፎርም” – ወንድይራድ ሀይለገብርኤል
April 15, 2019

·       ግን ማን የማን ናቸው?

እራሱ ም/ጠሚ/ር አቶ ደመቀ መኮነን የማን ናቸው? የኢትዮጵያ ወይንስ  የኦዴፓ? ማለት የብአዴኑ ቀርቶ ማለት ነው።

በተአምር ብአዴን የኦዴፓ የልብኛ አይሆንም።  የመንገድ ማካሄጃ ግን ሊሆን ይችላል። አንድ አመት ሙሉ በጠ/ሚር አብይ አህመድ አንደበት አንድ የአማራ ልጅ በቅርበት የታዬበት አጋጣሚ የለም። እኛም ይኖራል ብለን አናሳበውም። እርምጃችን ሁሉ ምን ያህል ክትትል እንዳለበት ምድር ትመሰከራለች። ጥላችን ይፈሩታል። 

በሚዲያቸው፤ በትርክታቸው፤ ባሰማሯቸው የኔት ወታደሮቻቸው አንድ ቀንጣ ነፍስ ከሊሂቃኑ ጀምሮ ‚አማራ አገዘን፤ ረዳን፤ ለዚህ አበቃን ሲሉ አልተደመጡም‘ ይልቁንም ከሞት አተረፍናቸው ሲሉ ነው የተደመጡት። ታግለን ለድል አበቃናቸው ሲሉ ነው የሚደመጡት። ድንቄም ነው።

ለኢትዮጵያ ነፃነት ቅንጣት አቅም ሲዋጣ አላዬንም እዚህ ውጭ አገር። ለኦዴፓ ዘላቂ የእነሱ ፍቅረኞች ሌሎች ናቸው። የልቤ የተባለላቸው የቅርብ አማካሪዎቻቸው ማን እንደሆኑ ይታወቃል። ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ከአብን አረና ይቀርባቸዋል። ይህ
 እውነት ነው። ስለዚህ እኛ ምን ባይነን?

እና ይህን የግብር ይውጣ ጉዞ ተሸክሞ በለበጣ እና በፌክ ኢትዮጵያን የምታክል 
ገናና አገርን አበሬ እዬመራሁ አለሁበት ማለት ለበጣ ነው። ብአዴን ከፍርሃት 
ቆፈኑ ወጥቶ ራሱን ችሎ ለመቆም ታቱን ይጀምረው፤ ቁሞ መሄድ ባይቻለውም
 አንድ አምት አምልጦት በፎርፌ ስለተወረውረ፤ ቢያንስ ለባጎም ባጉም ይሰናዳ!
 ለራሱ ገመና እንጂ ሌለው ገመና አንጣፊም ጎዝጓዢም መሆን አይኖርበትም።

ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የብአዴን ልፍስፍ ተፈጥሮ በስል ገብተው አዲስ
 ጋሬጣ ስለሰነቀሩበትም ጭምር ነው። የዚህ ባላባት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።
 ከዬትም አትደርሱም በሚል ፈሊጥ የልባቸውን እዬከወኑ የለበጣ አብሮነት
 አይሰራም፤ ሰርቶም አያቅውም። የሚያሰከብርም፤ የሚያስፎክርም የራስነገር የሆነ የክህሎት አቅም ብቻ ነው።

ኦሮማራ ለአማራ አሲድ ነው መራራ!

እንደ ግንባር ከሌሎቹ ባነሰ ሁኔታ ማነን አሳንሶ ያያል ቢባል ኦዴፓ ብአዴንን 
ነው። ንቆታል። የግንቦት 7 ያህል ቀርቶ የአቶ አረጋይ በርሄ የሁለት ሰው ድርጅትን
ያህል እንኳን ክብር ኦዴፓ ለአዴፓ የለውም። ሃቁ ይሄ ነው።

ስለምን ክብሩን ብአዴን መሬት ለመሬት እዬጎተተ እንደሚያልፈሰፍሰው አይገባኝም። የአዴፓ ዘመቻ ብአዴን አቅም ሳይኖረው ዘግጦ እንዲቀር በሁሉም መስክ እዬታተረ
 ነው። ስለዚህ የትናንቱ የ27 ዓመቱ ተኝተህ በለኝ አልበቃ ብሎ አሁንም በዛው 
ቀጥል እና ተጫነኝ ማለት ከጅልነት ባለፈ ሬሳነትም ነው።

ንጉሥ ኦነግ ብአዴን አስጎንብሶ እያስረገረገው ስለመሆኑ ተርጓሚ አያስፈልግም። 
አጤ ቄሮም አንበርክኮ እዬገዛው እዬገዘገዘውም ነው። ለዚህ ነበር ወይ ሁለመነው
አሳልፎ የሰጠው ብአዴን? ራሱን ይመርምር? ራሱንም ይጠይቅ? አሁንስ ኢትዮጵያ በጎረምሳ ስብስብ እዬተማሰች በመዲናዋ ሳይቀር መንግሥት አለ ብሎ ለዛ ድርና ማገር መሆን ሙትነት ነው። 

ከሁሉ በላይ ብአዴን ራሱን ማብቃት አለበት። ከፍርሃት ድግምቱ መውጣት 
ይኖርበታል። ለጽድቅ አይደለም የፖለቲካ ድርጅት የሚፈጠረው። ለሥልጣን ነው።
 ባዶ እጁን እያጨበጨበ ግን እስከመቼ ብአዴን ለባለጊዜ ከፍ እና ዝቅ ስጋጃ አንጣፊ
 ሆኖ ይዘልቀዋል?

·       ብአዴን ነፍስ ከላው …

ከምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ከተማ የተጠለሉ በመንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገለፁ

#EBCበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ

…“ፍርድ ቤቶቹ ገለልተኛ አይደሉም”… የቡራዮ ታሳሪ ወጣቶች ጠበቃ Ethiopia: Ethiopis

ከለገጣፎ ለገዳዲ ቤታቸውህገወጥ ነውበሚል የፈረሰባቸው 1200 የሚሆኑ ዜጎች አሁንም የድረሱልን ጥሪ
April 15, 2019

ብአዴን ለእነዚህ ነፍሶች የግንባር ስጋ መሆን ይኖርበታል። አማርኛ ቋንቋ ስለሚናገሩ
ነው ሰማዕትነት እዬከፈሉ ያሉት ልክ እንደ ቡራዩ የጎፋ ወገኖቻችን ጌዴኦም። 
ኣማሮም መሰል እጣ ነው ያለበት። ኦነግ አገር ከገባ ጀምሮ በተከታታይ ጥቃት
ሲሰነዝረበት የቆዬ ህዝብ ነው አማሮ። ወላይታው፤ ጉራጌው፤ ባስኬቶ ማን
አላቸው? 

ብአዴን ከእንቅልፉ ነቅቶ አቅሙን አጎልብቶ ራሱንም ኢትዮጵያንም የማዳን
 ታሪካዊ ተልዕኮውን ለመወጣት መጣር አለበት። የ አዲስ አባባ ህዝብም ሰላሙን
 አጥቶ ባልተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው።

ኦዴፓ ካለው በላይ አቅም ብአዴን አለው። ግን አያውቀውም። ስለማያውቀውም
 ነው በዬዘመኑ ተጠቅጣቂ፤ ተናቂ፤ ተሸናፊም፤ ተሸራፊም ሆኖ ህዝቡን እያስፈለሰ
 የሚገኘው …

ቀድሞ ነገር በዚህ አንድ ዐመት ውስጥ ያን ያህል ግብር የተከፈለለት ኦህዴድ 
በክልሉ ስለሚኖሩ አማራዎች ምን አደረገ? ክልል ፈቀደ? ወረዳ ፈቀደ? ዞን
ፈቀደ? የማዕካለዊ ምክር ቤት አባል አደረገ? የቢሮ አባል አደረገ? ቤሳ ቤስቲን አላደረገም። አማራን በዬቢሮው እያፈናቀለ አዲስ አባባ ላይ የራሱን ሰዎች ነው
 እየሞላበት ያለው። ወይንም ደቡብን።

Ethiopia -የገቢዎች ሚንስቴር በአንድ ወገን ተይዟል | ክፍል 1

Published on Apr 3, 2019

·       የአብይ ሌጋሲና ዴሞክራሲ …

የአብይ የዴሞክራሲ ሌጋሲ በቄሮ ጉልበት ምን እንደሚመሰል አዬን ሰማን።
ተሸፍኖ ነበር የባጀው የአብይ ሌጋሲ … በማን ትክሻ ስለመሆኑም ተፈታተሸ? 
ዴሞክራሲ ጀምሬያለሁ ለሚለው አብይ ሌጋሲ እንግዳ በመቀበል እና በመሸኘት
የከረመለት ብአዴን ነው። እንጂ ሌጋሲው ጸረ ዴሞክራሲ ነው። ከባልደረስ ንቅናቄ
 በላይ መስካሪም፤ አማሳካሪም ነገር የለም። ፈተናውን የወደቀ ነው የ አብይ ሌጋሲ። ሁሉም ነገር ፌክ ነው። 

የባለአደራው ጋዜጣዊ መግለጫ ክልከላ-(ራስ ሆቴል) በድብቅ የተቀረፀ Ethiopia: Ethiopis
Published on Mar 30, 2019
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)ጋዜጣዊ መግለጫ

·       ውል የለሽ ፍቅር ፍሬ ፈርሲከ ነው።

ለመሆኑ ብአዴን ከአዴፓ ምን ስላገኘ ነው ይህን ያህል ከፍ እና ዝቅ የሚልለት?
 ውል አለበትን? ኪዳን አለውን? ወይንስ በመደዴ መነጠፍ ይሆን?

እንግዳ በቀበል እና በመሸኜት ያሰባጀው የአብይ ሌጋሲ ያ መጠናቀቁ ሲያበቃ
ደግሞ በክልሉ ነፍሶችን ተፈናቀሉለት፤ ያ መልክ ለማስያዝ ሲጣደፍ ብአዴን
ደግሞ በቅርስ ላይ እሳት ነደደ፤ እሳቱ ነደደ እዬነነደ በስሜን ሸዋ እና በከሚሴ
ደግሞ ወገኖች ዜጎች የባሩድ ራት ሆኖ፤ ቅድስት ኦርቶዶክስ ነደደች። ይኸው 
ይሆን ለውጥ የሚባለው? ለውጡ የመጣው ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ 
ለማደረግ በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት መሰረት ማስያዝ ነው። 
ጸጸቱ ከተቻለ መቀጠል ነው። ውል ያስፈልጋል አንድ ነገርህን ስትሰጥ። 

የአማራን ታሪክ እና ዕድል ነው ብአዴን ያሰረከበው ካለ አንዳች ድርድር። 
አዬረ መንገዱ ራሱ ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል መጠበቅ ነው። መከላከያው
 እዬታዬ ነው። የኢትዮጵያ አዬር መንገድ መለያ ትሩፋቶች ሁሉ ይቀረፋፋሉ
 የቆዬ ሰው ይይው። ጸረ ኢትዮጵያ ሰዎቻቸውን ነው ቦታ እያስያዙ የሚገኙት።  

በዚህ ትዕይንት ውስጥ ብአዴን ከኦደፓ ጋር ሆኖ ለጤናችን መቼም እብንነት ነው። 
ከኪሳራ በስተቀር ያተረፈው ነገር የለምና። ተጣሉ ተፋለሱ አይደለም። መብት 
እና ግዴታን ያወቀ ልክ ያለው ግንኙነት ይነሩ ነው። ጥቃት ተሸክሞ ቀብቶ ባይኖር
ይሻላል።

ሁለት ሰዎች ብቻ እኮ ናቸው ብአዴኢን እያሸክረከሯችሁ ያለው። የሚያስፈረው
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በይፋ እና በአደባባይ ለዛውም ለጋዜተኞች የብአዴን
 ሰብሳቢ ነኝ ብለው ሲናገሩ ተሰብሳቢዎች ደፍረው አላፋጠጧቸውም፤ ሁለት
 ድርጅት መሪ ስለመሆናቸው መርህ ጥሰት ነውና።

በእነ አጅሬ ቤት ግን ይህች አትደፈረም። ከጫፋቸው ድርሽ የለም። በአገራዊ ጉዳይ
ጠ/ሚሩ ከውጭ አገር ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ሁሉ ኦህዴድ ጽ/ቤት ነው የሚመስለው። ሁሉ ነገር ተከርችሞ፤ ተመስጥሮ። 

ይህም ብቻ አይደለም አየር መንገድን ቦርዱን ሲያዋቅሩ የትራንስፖርት ሚ/ሯ 
እንኳን አያውቁም። አልተማከሩም። በባዕሉም ላይ የክብር እንግዳ አይደሉም 
ሚ/ሯ። 

ይህን የመሰለ መናቅን መረገጠን መገለልን አሽኮኮ አድርጎ ድርና ማግ
 መሆን ለባርነት እብደት ነው። ግዑዝነትም ነው። ጥቃት ራሱ የሆነ ሰብዕ ሳይፈጠር ሟሙቶ ቢቀር በስንት ጣዕሙ። አለሁ አትበሉ በዘነዛናው።

አንቀልባነት ለፖለቲካ ሊሂቅነት? እእ አይመጥነም … በግንባሬ እንጂ በጀርባዬ ላለ የአንባቸው ሌጋሲም አይመጥንም፤ ቀደም ባለው ጊዜ ብዙም እርግጠኛ አልነበርኩኝም የጋይንት ሰው ስለመሆናቸው ያው መከራው ከዛ አማራ በሚባለው ክልል ነገር በአንዱ ወገኑ እህ፤ በሌላው እም ስለሚሆን።

ኮታውም ጨዋታ ነው አሁንም። ስለምን ብትሉ ስር የሰደደ የ አማራ ጥላቻ ነው። 
አማራ ፖለቲካዊ ዕውቅና ላይ እንዲወጣ ማንም አይፈልግም። አሁን ግንቦት 7
አብይ ሌጋሲ እዛ ያሰለፈው ለዚህ ነው። ያማቸዋል። የሆነ ሆኖ አሁን ግን ከታሪካቸው ተረዳሁኝ።

ታች ጋይንትን እያንዳንዱን ቀበሌ ገበሬ አሳምሬ አውቀዋለሁኝ። ቤቱ ጅብ ገደል 
ይባላል። ግማሹ በድንጋይ ነው የሚሰራው። ህዝቡ ጠንካራ፤ ለማተቡ ያደረ፤ ወለም
 ዘለም የማያውቅ ቆፍጣን ህዝብ ነው። እና አሁን ያን ቆፍጣናነት እጠብቅለሁኝ
 አብዝቼ። ቆፍጣነነት አነሶት ነው የማዬው አመራሩን በጣሙን … 

አገር ያባጁት አባቶች እናቶች ሌጋሲ የት ገባ? የዛ ሁሉ የቅኔ ቤት ልቅና፤ ልዕልና፤ ብጡልነት፤ ነብይነት፤ ሊቀ ሊቃውንትነትስ? የአቅም  ትውስት? የትርጉም ብድር? የክህሎት ፍርፋሪ ለቃማ? ያሳፍራል? የብልጠቱን ሆነ የሴራውን ፓለቲካ ብልቱን
 አውጥቶ ለአገር አቅም በሚጠቅም መልክ መሞገት ጊዜው አሁን ነው። 

ይህ የሰንበሌጥ የጮሎዎች ጉዞ ሊገታ ይገባል። አቅም እያገኙ በሄዱ ቁጥር ነገ ጣራ ነው የሚሆነው። ስብስበው እስር ቤት ነው የሚያጉሩት ... "እንሟሟታለን" 
ነው ያሉት ... ይህ ፉከራ ለማንም አይደለም። 
  
በተገኘው አጋጣሚ መዋቅር ላይ ያሉ አማራ እዬተነጠሉ ከሥራ ቦታቸው ይመነጠራሉ። ምን እስከሚሆን ይሆን የሚጠበቀው? ላሊበላ እስኪቃጠል? ፋሲል ግንብ 
እስኪነድ?

·       ብአዴን አጅንዳው ሊሆን የሚገባ ይህ ነው።

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

ማንንን ለማጥፋት ነው የአብይወለማ ሌጋሲ በትጋት እዬሰራ ያለው? ይህን ቁጭ 
ብሎ በአጀንዳ ደረጃ ሊወያዬበት የሚገባ ጉዳይ ነው የብዴን ማዕከላዊ ምክር ቤት።
ማንን ለማክሰል ነው አዴፓ እየታተረ ያለው ይህ እኮ የህልውና ጉዳይ ነው። ይህ እኮ የሳሙና አረፋት አይደለም። በ አገር ላይ ሌላ አገር መንፈስ የመገንባት ተልዕኮ ነው እዬፈጸሙ ያሉት።

የቀደሙት የኦሮሞ ሊሂቃን ለኦሮሞ አልሰሩም ሲሉ ርዕሰ መሰተዳደር ለማ መገርሳ
ለማን ነበር የቀደሙት የኦሮሞ ሊሂቃን የሠሩት ብሎ ማፋጠጥ ይገባል? 
ዛሬስ ያሉት ቲም ለማ ለማን ነው የቆመው ብሎ ላይ ላዩን ከመጋለብ በተደሞ
ታሪካዊ ግድፈት እንደ እነ ጥላሁን ግዛው ላለመስራት ከውስጥ ሆኖ የራስን
ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ይገባል። ይህ አሉባልታ አይደለም እኮ። 
በተጨባጭ የሆነ ጉዳይ ነው።
  
ለዛሬ መነሻ እኮ ትናንት ነው። የፊት የፊቱን ይቀር የሚባለው ተራ ነገር ሲሆን ነው።
ዘርህን፤ ቋንቋህን፤ ትውፊትንህን፤ ትሩፋትህን ለማጥፋት በትጋት በመንግሥት ሙሉ
አቅም በጀት ተመድቦለት አዬተሰራበት አንተ ለጸጉር አስተካካይነት መሰለፍ 
እብደት ነው ለእኔ።

ይሉኝታ የላቸውም እነሱ። ጥድፊያ ላይም ናቸው ያሉት። ይሉንታውም ይቅር ርህርህና በኖራቸው። እርዳታ እንዳይደረስ የሚሰራ ድርጅት የአገርን ብሄራዊ ሃላፊነት ይወጣል
ብሎ ትራስን ከፍ አድርጎ ሃሳብን ጣል አድርጎ መተኛት አለመታደል ነው። 
የተዛናጋንበት ጊዜ በቂ ነው። ኦዴፓ እንደ መሪ ድርጅት ፈተናውን አላለፈም። 
ስለዚህ ቢያንስ ራስን ለማዳን ጊዜ ማቃጠል አይገባም። ቢያንስ ሂደቱን በማስተዋል
ሆኖ ማጥናት እና አቋም መያዝ ይገባል።

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ 

መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡

Published on Mar 9, 2019

ብአዴኖች ገና ህወሃትን ደስ ይለዋል ተብሎ ለራሳችሁ ልዕልና መታገልን የውሽማ
 ሞት ልታደርጉት አይገባም። እያፈረሷችሁ ነው ያለው። በክልላችሁ ተግብቶ 
እኮ ነው ያ ሁሉ ህዝብ የተፈናቀለው። አማራ ሙቶም፤ ተፈናቅሎም 
አላልቅላቸው ስላለ።

የአማራ ህዝብ ወዳጆች የሉትም ማለት አይቻልም። አሉት ግን ቀረቤታ እንዲኖር አይፈቀደም። አሁን ጅጅጋ ከአማራ ጋር መገናኘት ይፈልጋል። ግን አልተፈቀደም።
እነሱ ሲፈልጉ ግን ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ደረጃ የታቀደ ከቤኒ ጉምዝ ጋር ንግግር ነበራቸው። ኦሮቢኒ ማለት ነው። ያው የማደንዘዣው መርፌ ለማዘዝ።

ኦዴፓ በስልታዊ መንገድ ታሪካዊ ድርሻውን እዬተወጣ፤ ብአዴን ደግሞ በአፍዝ
አደንዝዝ የተደገመበት ሆኖ ተቀምጧል። በግራ ቀኝ ተከርችሞ። እሰከመቼ?
 አይታወቅም። 

አሁን የሰሞኗን ተርብ እንመልከት። አንድ ቀን በ10 የአማራ ከተሞች ቅልጥ ያለ
ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ያን ሰልፍ አቅጣጫውን ለማሳት ጠ/ሚር አብይ አህመድ
በድንገት ተነስተው ጣና ደራ እና ላሊበላ ጣና ላይ ነበሩ። አሁን አሁን ፍጥረታቸውም
ግራ እዬገባኝ።  ስብሰባ ጋዜጠኛ እስክንድርን አሳግደው በቄሯቸው ከኪጋሊ መልስ 
ደግሞ የአስኮባ ሰርግና መልስ ነበር።

እንቅስቃሴያቸው እያደባ የሚሄደበት መንገድ በእኔ ዕድሜ ያላዬሁት ጉዳይ ነው።
ስንት ሰው ሆነው እንደሚንቀሳቀሱ ግር እስኪለኝ ድረስ … አቅም ያሸከምናቸው፤
 ፍቅር ያሸከምናቸው፤ መታመን ያሸከምናቸው ሰው ምን ዓይነት እንደሆኑ 
በማስተዋል ልንመረምረው ይገባል። ንጹህ፤ ንዑድ፤ ጻድቅ ሆነው ለመገኘት
 የሚሄዱበት መንገድ ሁሉ የሚገርም ነው።

ወደ ስሜን አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት በዋዜማወው ደልዳላው ቀዳማዊት 
እመቤት ጎንደር ነበሩ ለሰባዕዊ ተግባር ዜናውን እና ራሴ ሰርቸዋለሁኝ፤ ከዛ
ስሜን አሜሪካ ጉዞ አብረው ይሁን በተናጠል ባላውቅም እሳቸውም ነበሩ።
የጠ /ሚር አብይ አህመድ ልዑክ ጉዞ ላይ እያለ ጎንደሬው ቆሞስ እንጂነር
ስመኛው በቀለ መሰዋትነት ተደመጠ። ተመልሰው ብጹዕናኑ አባቶቻችን በክብር
ይዘው ሲገቡ ደግሞ 9 አብያተ ቤተክርስትያነት ነደዱ … አንደ ግራኙ፤ እንደ
ጉዲት ዘመን።

አሁን ከሰሞናቱ ብአዴን ለተጎዱ ወገኖች የእርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም 
በተደረገበት ወቅት የአዲስ አባባ ከንቲባ  አላዬሁም፤ ግንቦት 7 ኦነግን
አቀባበል ላይ አይቻለሁኝ። እኛ ለአቀባባል አልተደልንም ለሞት ነውና።

ብቻ በዛ ላይ የከንቲባ ቢሮ እርዳታ አልሰማሁም እርዳታ ሰሞኑን 10 
ሚሊዮን ሰማሁኝ፤ በሌላ በኩል የስሜን ቃጠሎው ኡእታ ባጅቶ ሰሞኑን
አንድ እንቅስቃሴ አለ ስለምን?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

Published on Apr 15, 2019

ሄሊኮፕተሯ ውኃ መርጨት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እሳቱ መስፋፋት እንዳይችል መደረጉና መጥፋት በሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱም ታውቋል፡

Published on Apr 16, 2019

ለዚህ የኢህዴግ ማዕካለዊ ምክር ቤት ስበሰባ ደርብ ያለ የድጋፍ ሸማ ከብአዴን
 ስለሚፈለግ የአፍ መክደኛ ማለት ነው። እርዳታ ሲደረግ፤ መንፈስ ሲለገስ
 ወይንም ቅጣት ሲደረግ በመያዦ ታቅዶ እና ታልሞ ነው።

#etv ኢቲቪ ምሽት 2 ሰዓት አማርኛ ዜናሚያዝያ 07/2011 .


እንዲህ ዓይነት ፍጥረት ለማህበራዊ ኑሮም ከባድ ነው እንኳንስ ለአገር መሪነት።
 በውነቱ ነፍስ ሁሉ በጥንቃቄ መጓዝ እንደለበት አለርም አለበት። ነገር አለሙ 
እንዴት እና እንዴት ሆኖ እንደሚወናጨፍ። ቀዳዳ፤ ክፈትት እንዳይኖር ያለው 
ነገር የልቤ ማለት ይገባል።

እውነተኛውን አብይን ገና አላዬንም፤ አላገኘነም። ይህ ቅርፊቱ ነው። ይህን ሳስብ
ማን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለችሁ። የፕ/ ብርሃኑ ነጋ አምነዋለሁ አብይን ያሉት
ነገር። እንኳንስ እሳቸው አቶ ለማ መገርሳም አውቀዋለሁኝ ብለው ደፍረው 
መናገር አይችሉም። ዶር አብይ ሰብዕናቸውን ለማወቅ የሰማይ መላዕክት 
ይጠዬቁ። ንግግራቸውም ተግባራቸውም ውስጣቸውን የመግለጥ አቅም የላቸውም።
 ነገ ምን ሊሰሩ እንዳሰቡም እንዲሁም ማወቅ መተንበይ አይቻልም።

ገፅ ገፅ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር

/ ብርሃኑ ነጋ ጋር የተደረገ ውይይት OBN 19 07 2011

Published on Mar 28, 2019

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ የአዲስ አባባ የጠረጋ ጉዳይም እንደዚኽው ነው።
በለማኝነት ተክህኛለሁ ብለዋል ጠ/ሚር አብያ አህመድ አንዲዚህ ዘው ብሎም
የልብን ለመከወን የማዘናገትም ስልትም ሌላው ተሰጥዖቸው ነው። 

ስለዚህ ቀላል መሪ አይደሉም … በቀላሉ አምነዋለሁም፤ በቀላሉ አውቀዋለሁም፤
በቀላሉም ተገብቶ የሚወጣተበት ልብ አይደለም የላቸው።

ረቂቅ ናቸው ማለት አልችልም፤ ግን አጋጣሚዎችን አጥንቶ በዛ የልቦናን
ለሞሙላትቅንጣት ጊዜ የማያጠፉ ሰው መሆናቸውን ታዝቢያለሁኝ። ሚዲያ
 ዋናው የጦር ማዘዣ ጣቢያቸው ነው … እንደ አዬር መቃወሚያ ነው የሚጠቀሙበት።

ስለሆነም ቅኔም፤ እድምታም፤ ተደሞም፤ ሊቃውንትነትም ብድር እንዲሄድ
 የማይገደደው ብአዴን ሙያን በልብ ይዞ አቅሙን አደራጅቶ በርትቶ የራሱን
 ተልዕኮ ለማሳካት ዘንብሊነቱን አሸቀንጥሮ ተፎካካሪ፤ ብርቱ ተጋዳደሪ ሆኖ 
ለመውጣት መቁረጥ፤ መወሰን ይኖርበታል። ፈተናው ግን ከህወሃትም የከፋ ነው።

አንድ ሰው እንደ ማዕከላዊ ኮሜቴ፤ አንድ ሰው እንደ ጉባኤ፤ አንድ ሰው እንደ 
መንግሥት ሆኖ እኔ አሻግራችሁ አለሁ ሲል ምን ማለት ስለመሆኑ ልብ ሊባል 
ይገባል? በማን ሃይል? በምን አቅም? በምን እሳቤ ማለት ይገባል? እርግጥ ነው 
ይህ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ሆኖ ቢሆን በረከት ነበር። ግን የማዬው ነገር አሰፈርቶኛል። 

ስለዚህ እወዳደራለሁ፤ እፎካከራለሁ የሚል ሁሉ በራሱ ብቻ እምነት ሊኖረው
ይገባል፤ ከፈጣሪውም ጋር የቀረበ የእርዳታ ጥሪ ማቅረብ ይኖርበታል። ከማን ጋር እንደሚፎካካር፤ ከማን ጋር እንደሚታገል ጠንቅቆ አውቆ በስልት መራመድ ይኖርበታል።

 ለብአዴን አንዲትም ቅንጣት ነገር ትራፊ ወይንም ቅርጥምታሚ የአቅም ብልጽግና 
 እድገት ከፍታ ኦዴፓ ሊፈቅደለት አይችልም። በሩ ተከርችሟል። ስለዚህ እውነትን ፈልጎ በማግኘት ሂደት በማስተዋል ሆኖ ሊታታርበት ይገባል። የፖለቲካ ድርጅት የግብረሰናይ ድርጅት አይደለምና። 

ዶር አብይ አህመድ ውጭ እንደሚታዩት ገር፤ ለስላሳ፤ ቸር፤ ዝንጉ፤ አማኝ፤ አቅራቢ አድርጉ ማዬት ቢበቃ የሚሻል ይመስለኛል። ኢትዮጵያን አስባዋት እኛ ብንጎዳም 
ቢሆንታላቅ የሰማይ ስጦታ ነበር። ግን እሳቸው ለኦሮማማ ነው የሚታገሉት፤ ኦሮማማ
 ደግሞ የአማራ ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ውርስ፤ ቅርስ፤ ትምህክት፤ መነሻነት ጠላት ነው።

ስለሆነም ብአዴን በዬሰከንዱ የሚሰጠውንም የጠ/ሚር አብይ አህመድም ሆነ
የዶር ለማ መገርሳ አፍዝዝ አደንዝዜ ክንኒን አሻም እያለ በራሱ መንገድ በጨዋነት
ራሱን የማሰከበር ተግባሩን መወከወን ይኖርበታል። በእሱ ሥም ያሉ ሊሂቃንም
ሞራል የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ወጣ ገብ የሆነ አያያዝ ነው ፌድራል ላይ ያለው።
አንዱ ቤተኛ ሌለው የእንጀራ ልጅ አይነት። 

ብአዴንን አስመልክቶ ተፎካከሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ የሚባሉት ራሱ ለአንደበታቸው ልጓም የላቸውም እስከ ሚዲያቸው ለመዘልፍ፤ ለማንኳሰስ፤ ለመውቀስ እና ለመክሰስ።
ስለምን? ራሱን ያስደፈረው ራሱ ድርጅቱ ብአዴን ስለሆነ። „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ ጎንደሮች ሲተርቱ። ሁሉም ልኩን አውቆ እንዲንቀሳቀስ ልክን
 አደራጅቶ በቅቶ ነቅቶ በልጽጎ ሆነ መገኘት ይኖርበታል ብአዴን።

የኦነግን ሥያሜ ከመቀበልም ለአለሙ ሁሉ አብነት የሆነው ቅኔውን ጎጃም ላይ 
ተቀምጦ ትራፊ ሥም ይዞ መጓዝም ፍዝነት ነው ለእኔ … ለዚህ ነው እኔ ብአዴን
 እምላችሁ  … ከኦነግ ቅርፊት ስም ልሙጡ፤ ሞላለው፤ ጠፍጣፈው መባል 
በስንት ጣዕሙ …
  
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አረመኒያዊ የጭካኔ መንፈስ 
አጋር ሊሆን አይችልም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
መሸቢያ ገዜ። 



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።