የደህሚት መሳቂያ ቀረርቶ በኔት ሲሰለቅ ...
የደህሚት ቀልድ። የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ፤ ለነገሩ ከነፍጠሩቱ ነው … ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018 (ከጭምቷ ሲወዘርላንድ) „እግዚአብሄርን እንዲህ በሉት፣--- ሥራህ ግሩም ነው፤ ሃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ“ (መዝሙር ምዕራፍ ፷፭ ቁጥር ፭) · መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92907 „ደህሚት የትጥቅ ትግል አቆመ“ · የማተብ ወለምታ እንደ መግቢያ። ወይ ቀልድ፤ ስንት ቧልተኛ፤ ስንት አላጋጭ፤ ስንት ስንጥቅ፤ ስንት ትርትር፤ ስንት ብልዝ፤ ስንት ዝብርቅ፤ ስንት ጥንዙል፤ ስንት ማድያታዊ ወግ ይሆን ዘንድሮ የሚደመጠው። ትናንት ተዚህም ተዚያም ስል ቆያይቼ በደከመኝ ሰዓት ነበር ዘሃበሻን እንዴት አመሸህ ስል አዳዲስ ዜናዎች ይዞ የጠበቀኝ። ልቤን ሳብ ያደረገኝ የአላጋጩ የደህሚት የማተብ ወልምታ ነው። ሳቅ በሳቅ ነው የሆንኩት የእውነት ልቤ ፍርጥ እስኪል ድረስ ሳቅኩኝ። ቀልድ አይሉት መቦጫረቅ፤ መቦጫረቅ አይሉት መንጨባረቅ፤ መንጨባራቅ አይሉት መዛቀጥ፤ መዛገጥ አይሉት ማንዳላጥ ቅጥ አንባሩ ግርም ይላል፤ ቡጭቅጭቅ አንባርጭቃ! · የላ ንቁሶ ልግጫ። እንዲህ ይለናል ትራሱን ከፍ አድርጎ ሲያለግጥ የከረመው ደህሚት … . „ድርጅታችን ይህ አሁን በአገራችን ወደ ስልጣን የወጣው በዶር አበይ የሚመራው የለወጥ ሃይል የድርጅታችን እና የመላ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ውጤት መሆኑን ...