የደህሚት መሳቂያ ቀረርቶ በኔት ሲሰለቅ ...

የደህሚት ቀልድ። የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ፤ ለነገሩ ከነፍጠሩቱ ነው

ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018
(ከጭምቷ ሲወዘርላንድ)
„እግዚአብሄርን እንዲህ በሉት፣---
ሥራህ ግሩም ነው፤ ሃይልህ ብዙ
 ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ“
(መዝሙር ምዕራፍ ፷፭ ቁጥር ፭)



  • ·       መነሻ።

 „ደህሚት የትጥቅ ትግል አቆመ“

  • ·       የማተብ ወለምታ እንደ መግቢያ።

ወይ ቀልድ፤ ስንት ቧልተኛ፤ ስንት አላጋጭ፤ ስንት ስንጥቅ፤ ስንት ትርትር፤ ስንት ብልዝ፤ ስንት ዝብርቅ፤ ስንት ጥንዙል፤ ስንት ማድያታዊ ወግ ይሆን ዘንድሮ የሚደመጠው። ትናንት ተዚህም ተዚያም ስል ቆያይቼ በደከመኝ ሰዓት ነበር ዘሃበሻን እንዴት አመሸህ ስል አዳዲስ ዜናዎች ይዞ የጠበቀኝ።

ልቤን ሳብ ያደረገኝ የአላጋጩ የደህሚት የማተብ ወልምታ ነው። ሳቅ በሳቅ ነው የሆንኩት የእውነት ልቤ ፍርጥ እስኪል ድረስ ሳቅኩኝ። ቀልድ አይሉት መቦጫረቅ፤ መቦጫረቅ አይሉት መንጨባረቅ፤ መንጨባራቅ አይሉት መዛቀጥ፤ መዛገጥ አይሉት ማንዳላጥ ቅጥ አንባሩ ግርም ይላል፤ ቡጭቅጭቅ አንባርጭቃ!





  • ·       የላንቁሶ ልግጫ።
  • እንዲህ ይለናል ትራሱን ከፍ አድርጎ  ሲያለግጥ የከረመው ደህሚት ….

„ድርጅታችን ይህ አሁን በአገራችን ወደ ስልጣን የወጣው በዶር አበይ የሚመራው የለወጥ ሃይል የድርጅታችን እና የመላ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ውጤት መሆኑን በማመን በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እዬተወሰዱ ያሉ ለውጦችን በመገምግም አዎንታዊ ድጋፍ ሲሰጥበት ቆይቷል“ ዳጥ የሆነ ጉድ። ውሸቱ አያልቅባቸው ወይንስ ሲፈጠሩ እ ተብለው ሲማጡ ውሸት ይሆን የተቀበላቸው... 


ይህን ድርጅት እንደ ድርጅት አይቼ እራሱን አስችዬ ለመጻፍ ፈጽሞ አስቤው አላውቅም። ሁሎችም አረና ይሁን የዶር አረጋይ በርሄ ስብሰብ ይሁን፤ ወደ አንድነት ተቀላለቀለን የሚሉትም ቢሆኑ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ፖሊሰ ነፍስ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ የታላቋ ትግራይ ምናብ ጋር የተጣበቁ ግን የሥልጣን ቁራኛነት ያባከናቸው ናቸው። 

አብሶ ከአቶ ሞላ አስገዶም ሲመሩት የነበረው ድርጅት ከምን ይመደብ ሊባል እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀው? ሰው እንደ እንደ ምን ለሳቸው ሲነዳ እንደ ነበረ ይገርመኛል … ውልቅልቃቸው የወጣ ውጥንቅጥ ጉድ። 

እንዴት የሰው ልጅ ለደቂቃ መሪዬ ብሎ አብሮ ከሳቸው ጋር እንደሚታደም ብቻ ሳይሆን፤ ስንት የፍጥረት ዓይነት እንዳለ በውል ያስገነዝባል … መሬትነት በዝብርቅርቅነት ... መቼስ ገበርዲን ሱሪም አይችለው የለም።

አቶ ሞላ አስገዶም የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ


የአቶ ሞላ አስገዶም የደህሚት ዓላማውም፤ መላውም፤ ግቡም የማይታወቅም። የውሽማ ሞት የነበረ የጉዶች ክምር ነበር። ኤርትራውያን ከዚህ ያሉት በርካቶች የክት እና የዘወትር ጉዳይ ድርጅቱ እንዳለው ያጫውቱኝ ነበር። ግንስ ምኑም ግጥሜ ስላልነበረ፤ ጠረኑም ክፍሌ ስላልነበረ አጀንዳዬ ብዬ አስቤው አላውቅም ነበር፤ ዛሬም እንዲያው ያላ አቅሙ ወጥቶ ሲንጠራራ፤ ፊጢጥ ሲል ልኩን እንዲያውቅ ሊነገረው ስለሚገባ ነው ብዕሬን ያነሳሁት … 
  • ·       „ወደሽን ቆማጤ ንጉሥ ትመርቂ ነው።“


አሁንማ ጥግ የለም። ከለላ የለም፤ እዛ የነበረው ምሽግ እኮ እንደሚደመረስ እና የወለሌ ገበታ እንደሚሆን የባድም ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታን ማንበብ ነው። ያ ወሳኔ ኔት ላይ መሽገው የባጁትን የፖለቲካ ድርጀቶችን ኤርትራ የመሸጉትን አከርካሪ እንደሚሰብር አሳምሬ ገልጨዋለሁኝ።  

የግድ ነው ይህ ሊሆን? ማን ቀለብ ቁጭ አድርጎ እንደ ሰንጋ ይቀልባል? ከእንግዲህ … ሞኙን ይፈልግ ደህሚት እርግጥ ነው የልብ አዋቂ ሚስጢር ጠባቂ እንደ ነበር ይታወቃል።

የሆነ ሆኖ ይህ የለውጥ ማዕበል ሲመጣ የነበረው ግራ ቀኝ ጫጫታው ሁካታው ኳኳቴው በዬአቅጣጫው ሲተራመስ ኔቱን ሲያውክ የከራረመው  … በዚህም ክፉኝት ጉዳይ ነው። እንደ ተኮፈሱ፤ እንደ ተለጠጡ፤ ተራራ እንዳከሉ እንደ ባሎን እንደ ተነፉ መቀጠሉ መርዶ ስለነበር።

አይታፈር ደግሞ „የኢትዮጵያ ህዝብ“ ይለናል ደህሚት¡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አስቦ? ከትተክት … ሌላው መለናቆጣዊ ትእይንት ደግም   „የድርጅታችን እና የመላ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ውጤት መሆኑን በማመን“ ከዚህ ላይ ደግሞ ባለ ኮፒ ራይት ሆነ፤ የ እሱ ሰዎች ነበሩ እዛው የሚቀር፤ የገብያ ግርግር እያሉ ሲያላግጡ የነበሩ፤ 

ደግሞ መቼ ነው ወጉ ደርሶት ደህሚት ትግል ሜዳ ተገኝቶ የሚያውቀው፤ ወገቡ ተፈትሾ የሚያውቀው? እፈረተ ቢስ መሳቂያ። ያ ሁሉ ህዝብ ሲያልቅ የት ነበር ይህ ልግጫዊ ትብኢት ፈንድሻ ብተና ... ህም!



ሌላው መሳቂያው ደግሞ መቼስ ነው „አዎንታዊ ድጋፉን ለለውጡ ሲሰጥ“ ይለናል እንዴት ዓይነት ዓይኑን በጥሬጨው ያሸ ጉደኛ ነው? ለነገሩ የተለመደ ነው የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ ከዬትኛው የወረሰውን ያው ነው ዙሮ ተመልሶ ስርቆት፤ ሌብነት ውሸት ዝርፊያ ወረራ። 

„የትግራይ ሰው ተፈናቀለብኝ“ እያለ አልነበረም ሲንጫጫ የነበረው። ተልባ። መሳቂያ …. አይታፈር ደግሞ አሁን አለሁኝ ሲል ከሞቀው ዘፋኝ። ባለፈው ሰሞን አይደል ሁመራ ላይ ሰው ሰርቆ የሄደው። በምን አቅሙ አሳምኖ ታጋይ ያመጣል። ታጋይስ ያወጣል፤ በዘረፋ። ትርትር! የሰውን ልጅ ሰላም እንዲህ እንዳወከ … የመርዝ ብልቂያጥ
  • ·       ኔቢስ ቀረርቶ!

አቤቶ ደህሚት ወኔው፤ ቀበቶው፤ ቃታው ኑሮህ ቢሆንማ ያን የወያኔ ሃርነት ትግራይን በባድማህ ገብተህ አርበትበተህ፤ እርቃኑን ታስቀረው ነበር … ሱሪው ቢኖርህ ቀበቶው ቢኖርህ። አንዲት ቀልሃ ሳትተኩስ፤ የትጥቅ ትግል ቆመ፣ ክክክክከ፤ መሳለቂያ … 

መቼ የታገልከውን? ለመሆኑ መቼ ነው ከማሽላ ቆረጣ የተመለስከው? ለመሆኑ ትጥቅ ትግል ምን እንደሆነ ታወቀዋለህን? እስኪ ንገረን? ስንት መሬት ከወያኔ ሃርነት ትግራይ በራስህ በባዕትህ ትግራይ ላይ አስለቀቅክ። ስንት ድል ደረደርክልት ለዛ ላለምከው የታላቋ ታላቅ የትግራይ ልዕልና እና ኩፍስና?

ያው የቆምከው አክሱማዊትን ኪንግ ደም ለመፍጠር ነው አይደለንም? ስለምን አላሳዬህንም አድዋዊን ሥርዕዎ መንግሥት በአክሱማዊቷ ታላቋ ትግራይ ህልምህን ዕውን አድርገህ … ብትገባም መርዝህን ይዘህ ነው … ያው እንደ ተለመደው … ወገኛ ወግ አይቀርም …

ይህ ድል የጀግናው የቄሮ እና የጀግናው የአማራ ማንነት የህልውና ተጋድሎ ያልተቋረጠ የተከታታይ ዓመት የተካሄደ የተጋድሎ የደም ውጤት ነው። ይህ ትግል ኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ የወለደው መራራ ተጋድሎ ያፈራው ፍሬ ነው። አቋጥሩኝ! … 

አንተማ ማሽለላህን እጨድ ውቃ ንግድህን አጧጡፍ … ሌላም ሌላም … አሳደድ ጨለማን ተገን እዬደረክ፤ እዚህ ያሉ የኤርትራ ወጣቶችን ጠይቅ ከተማ ላይ ያሉህን ምንትሶችህን …



ይሄን እዬው ይህ ተገድሎን ከዚህ ያደረሱ ጀግኖች እነኝህ ናቸው …. ከገባህ … አልቀረብህም ታገልኩ ስትል። ከእነመኖርህ ያስታወቀልህ ኢሳት ነው ሚዲያ ከፍቶ ቀስቅሶልህ። ትራፊ ቢገኝ ተብሎ በቃ … ጥምረት ቢሳካ ተብሎ፤ የነገ ተስፋ ተብለህ ስተቀደስ ስትወደስ፤ አንድም ሰው ከጆሮው ሳያንጠለጥልህ እንደተከዘንክ አሁን ደግሞ በዛገ ዕብለት ተከዘንክ… መጥኒ ለዛች መከረኛ የእትብት መንደራችሁ … አንድ እንኳን ልብ ተከፍቶ የእኔ የሚባል ድርጅት ሳይፈጠረባት ቀን ከሌት ስትብጠለጠል ውላ ስለመታድረው ትግራይ።

እንግዲህ የአዲሱ ምላጭ የአቶ አብርሃም ደስታ/ አቶ ገብሩ አስራት ውርስና ቅርስ፤ የአዛውንቱ የዶር አረጋይ በርሄ፤ የዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ታላቋ ትግራይ ታስተናግድ ይህን ሁሉ መከራ ለ4% ይህ ሁሉ ሽር ጉድ። ተራራ በተራ። ያው ተቀራመቱት እና ያን ፍደኛ ሥም ያው እንደ ፍጥርጥራችሁ ጦሳችሁን ተሸክማችሁ እዛው ….

የሆነ ሆኖ አቤቶ ደህሚት የትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ስለመፈጠረህ አያውቅም፤ ስለመኖርህም አያውቅህም፤ እንዳለህም አይቆጥርህም፤ እስኪ ደጋፊህን ውጪ አገር ካለ ከኢሳት ጋዜጠኞች በስተቀር አንድ ሁለት ብለህ ቁጥርልን … ወግ መጠረቅስ ይታወቃል … ዕድሜ ለኢሳት ጋዜጠኞች በል እድሜ ለግንቦት 7 ጋዜጠኞች በል። ለእነሱ ይልቅ ወርቅ ግዛላቸው …  
ይህ የለውጥ ማዕበል የቄሮ እና የአማራ ይህልውና ተጋድሎ ነው።

እንዳትረሳው! ያርበተበትህ የጎንደር የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ የወልቃይት እና የጠገዴ የአማራ የማንነት አብዮት የወለደው የጀግናው የኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጫካ እንዳተ ጉልበቱን ታቅፎ ሳይተኛ፤ ዓመት ይዞ እስከ አመት ማሽላ እዬያጨደ ሳይኮፈስ፤ ቤቱ ቁጭ ብሎ በጽናት ጠላቱን ደጃፉ ላይ ዘርግቶ ያቀጣጠለው አብዮት ነው።
        የዚህ የምዕት ጀግና ውርስ እና ቅርስ ነው ... 

 ልባሙ አስተዋዩ ጨዋው ድንቁ የጎንደር ህዝብ የፍቅር ድልድዩን ዛሬ ሳይሆን „የኦሮሞው ደም ደሜ ነው፤ የጋንቤላውም ደሜ ነው፤ ድምጻችን ይሰማ“ ባለው መሠረት፤ ጎጃም ደጀኑ ደሙን ልጆቹን ትዳሩን ኑሮውን ገብሮ 20 ሺህ ወገኞቻችን እስር ቤት ተከዝነው፤ የኦሮሞም ንቅናቄ 30 ሺሕ ወገኖች የካቴና እራት ሆነው ቢሸፈቱ ላይ 600 ወገን ተገብርቦት፤


ባህርዳር ላይ 50 ንጹሃን ተጨፍጭፈውበት፤ አንባ ጊዮርጊስ ላይ 26 ሰማዕት ህጻናት ተገብረውበት የጎንደር የቅርስ መሠረት በትዕቢተኛው አቶ አባይ ወልዱ ሽፍቶች በቤንዚን ተርክፍክፎ ቅዳሜ ገብያ ነዶ፤ ደብረታቦር ጭሶ በዬጥሻው በዬጫካው የጎጃም እና የጎንደር አማራ እዬታደነ የአሞራ እራት ሆኖበት የተገኘ ድል ነው። ይህን ያደመጠው የለማ የገዱ መንፈስ የጽናት መሠረት ያስገኘው ነው። ለነፍስ አንድ የትግራይ ድምጽ ባልተጨመረበት ታሪካዊ ውሳኔ ላይ፤ አለንነበት አታፍሩም? አይሰቀጥጣችሁም? ውሸት ትዳር እና ክብር፤ ወረራ ጌጥ እና ታሪክ፤ መሳቂያ ... መጥኔ ስለ እናንተ ... 


የጎንደር አብዮት  ጣና ኬኛን አብጅቶ አባይ ኬኛን አጰጵሶ አብይ ኬኛን አጨጌይቶ አንተንም ከማሽላ አጫጅነት ገላገለህ … አማራ እንዲህ ነው ሙያ በልብ ነው። ሁሉንም ልኩን የሚያስይዘው በልበ ብርሃንነት፤ በልበ ሙሉነት፤ በሙያ በልብ ነው  ዓለማውን ከግብ አድርሷል፤ የ66ቱን የምክር ሰውር ደባ ከመሰረቱ ነቅሎታል፤፡ አማራ ከበሮ መደለቅ አይደለም ተልዕኮው …. አሁን ሁሉም ልኩን አውቋታል።

የጊዜ ጉዳይ ነው አይምሰለህ ጊዜውን እዬጠበቀ ሃቅ እውነት ይነጥራል። አማራ የምንም እና የማንም ተጠማኝ አይደለም፤ ለዚህ ነው አማራ ተደቁሶ፤ ተሰውሮ ግን አቅሙን ሲያስመጠምጥ የኖረው፤ አሁን ግን  በአቅሙ ልክ ራሱን ወክሎ መሆኑን በተግባር የሚያቀልምበት ዘመን ብትፈራውም አይቀርም …. መንፈሱ እራሱን የቻለ ነው።

ቤቱን አደራጅቶ አሳምሮ እስክርቢቶን ለወግ አብቅቶ ለሥም እና ለዝና ሲያጀግን ያውቅበታል … ከአንተ ቀድሞ ጫካ የገባው እኮ የአርበኛ አበጀ በለው/ የአርበኛ ጄ / ሃይለ መለሰ ሠራዊት ነው ኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን የፈጠረው።  ይህን መቼም አሊ አትለውም … 

አቤቶ ደህሚት ይልቅ አንድ ነገር የብልጦች የጮሌዎች ሰላባ አለመሆንህን አደንቅልህአለሁኝ። ራስህን ከእነ አቧራ የጠጣው ትጥቅህ ጋር ማቆዬትህ ላራስህ ታሪክ ይበጅሃል። ሳትከፈልም ሳትዋጥም፤  የአማራ ተጋድሎ እና የቄሮ አብዮት ለዚህ አብቅቶሃል … ለቀን አድርሶሃል ቀን ወጥቶልሃል ከወድአከር አጨዳ እና ውቂያ … ተማልዶሃል።
            


          የአንተዎቹ ደግሞ እነኝህ ናቸው ...


ይህን እዬው …. የጀግኖች ውሎ ይሄን ይመስል ነበር … የአንተዎቹ ደግሞ ቤንዚንና ክብሪት ይዘው ቅርስ ሲያቃጥሉ፤ ፈንጅ እና ቦንብ ይዘው እጅ ከፍንጅ ሲያዙ፤ እንዲያም ሲል አፍንድተው ሲፈነዱ፤ ሲዘርፉ፤ ሲቀሙ፤ ሲቀነዘሩ ያን ማተበኛ ህዝብ በረከሱ ኢ-ሰብዓዊ እና ኢ-ተፈጠሯዊ መከራ ሲያሰወቅሱ እና ሲያስነቅሱ ነው …. ማፈሪያ።

መሪም የላትም ልጅም አልወጣላትም ትግራይ። ከአቶ ገብረመድህን አርያ በስተቀር፤ አንድ ሙሁር ወጡ ተባለ እንድ እንደ ወልዴ እዛ አዲስ አባባ አሉ ሲባሉ እሳቸውም የአልጀርሱን ውሳኔ ታች ወርደው አፈጻጸም ላይ ሲዳክሩ ወይ አንቺ ያልታደልሽ ትግራይ እንዲያው ከማን ትጠጊ ይሆን አሰኝቶኛል። 

የዓለም አቀፉ የህግ ባለሙያ ሊቀ ሊቃውን ዶር ያ ዕቆብ ፓለቲካዊ ትንተና … ስለባድመ እና ሁኔታ ቁስ ላይ ብቻ መዳከር … ነበር።

አሁን በዚህ 8ቀን ማን ስለቁስ ያወራል? እሳቸው ግን የተቸገሩበት ሌላ ነበር። ፍቅር ከኖረ እኮ ምንም የሚያናቁር ነገር የለም፤ ድንኳን እኳ ነው የዚህ ምድር ጉዳይ። እሳቸው ግን ያን ያህል የህዝብ ዕምነት የተጣለባቸው የመሆን አባወራ የኖሩ ሊቅ ወደ እሳቸው እትብት ኮተት ሲባል ሾልከው ነው የቀሩት። አሁን ያለው ፍሰሃ ሐሴት ሰናይ የበለጠውን  ለእናንተው እንጂ ሌላውማ ትራፊው ነው የሚደርሰው … ግን የሆነው የተገላበጠ ነው …

የሆነ ሆኖ የፈራችሁት የአማራ አቅም ዘመናችሁን ሁሉ በመንፈስ የተደራጃችሁበት የዘረኝነት መርዝ ታጥሶ በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት አቅሙ ችሎታው ብቃቱ ተደሞው እያያችሁት ነው እንኳንስ ለራሱ ለእናተም እዬተረፈ ነው። አማራ ኢትዮጵያ ብሎ እንጂ እንደ እናንተ ብሄሬን ካለ ማንም ሊገድበው ሊገታው ከቶውንም አይችልም …  ሲነሳ አይታችሁታል … እናንተ የረገጣችሁት የዘራይ ደረስን የጎንደሩን ዘውድ የዐጤ ዮሖንስን ዓርማ ነው ያነሳው … የሆነ ሆኖ እንኳን ለ2011 የማሻላ አጨዳ ዘመን ተገላገላችሁ ሌላማ ምን ሥራ ሲኖራችሁ …

  • ·       ይደረስ ለፕ / ኢሳያስ አፈወርቂ።


ፕ/ አሲሳያስ አፈወርቂም አቶ ዳውድ ይብሳን ከነትጥቁ ልከው የወለጋ ለቀምትን መከራ እንደ ገና እንዲንሠራራ እንደ ተደረገው ሳያደርጉ እምለሳለሁ ወደ አገሬ ለላ የሞገድ የትጥቅ ታጋይ ድርጅት ሁሉ ካለ ትጥቁን ማስረከብ ይኖርባቸዋል። ትጥቅ ማስፈታት ማስፈታት ግድ ይላል ዬትኛውንም የትጥቅ ትግል የአየር ላይ የጉራ ተፋላሚ።

በስተቀር የፕ/ አሳያስ አፈወርቂ ካቢኔ ከልቡ አይደለም „ኢሳያስ ትናንትም ኢሳያስ ዛሬም ኢሳያስ“ ለሚሉት የመንፈስ ስንቅ አቀባይ ብቻ ሳይሆን ይህን ከእዮር የተላከለትን የመግቢያ በር ይከረቸማል። የቀረበት ብዙ ነገር እንደነበረ ራሱ ያውቀዋል። ደስታው ለ ኤርትራ ዱባይ፤ ሳውዲ፤ ግብጽ አልነበረም ቅደስተ ቅዱሳን ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

ህዝብ መለያዬቱን አልወደደውም … ለዚህ ነው ንጹህ ፍቅሩን እዬሰጠ ያለው … ስሊዘህ የመጀመሪያው የፕ/ ኢሳያስ ካቢኔ ሊያደርግ የሚገባው ያስታጠቃቸውን ሃይሎች ትጥቅ በሙሉ ማስፈታት ነው። የጠ/ ሚር አብይ አህምድ መንግሥትም ይህን መሰረታዊ ጉዳይ መስመር ማስያዝ ይኖርበታል። በዚህ ጉዳይ ተላላ መሆን በፍጹም አይገባውም።

ኢትዮጵያ ውስጥ አስከ አፍንጫው የታጠቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሠራዊት ከበቂ በላይ ነው። ያ መቼም ለዘመናት ዬተከለ ነቀርሳዊ ጉዳይ ነው። … የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶን መንፈስ የታጠቀው ደህነንቱ ቢሮ ከበቂ በላይ ነው ይህም ሌላው ኤድስ ነው።

 በዬቢሮው 27 ዓመት ሙሉ አገር ምድሩ የተጥለቀለቀው የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ አቀንቃኝ መንፈስ ከበቂ በላይ የመርዝ ብልቂያጥ ነው …
የውስጡ መርዝ ሳይነቀል፤ ወይ ወደ ሰዋዊ መንፈስ ገና ሳይገራ ሌላ የ20 ሺህ መርዝ ደግሞ ከእነ ሙሉ ትጥቁ እረከባለሁ ቢል ኦሮሞ እና አማራ ነው መጀመሪያ ድውለት የሚሆነው። በዚህ ጉዳይ ዶር ለማ መገርሳ ሆኖ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሙሉ መንፈሳቸውን በዚህ ላይ ማሳረፍ ይገባቸዋል።

 … ይህ በመርህ ደረጃ ውል ሊይዝ፤ ልክ ሊይዝ፤ ሊታሰብበት የሚገባ ክፍት ቦታ ነው። በምንም መሥፈርት እና ሁኔታ ከነትጠቁ የሚገባ፤ ከነትጥቁ ምህረት የሚጠይቅ የመርዝ አንቀልባ መሆን የለበትም የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ። በዚህ ዙሪያ ያን የመሰለ ክብር እና ልዕልና ለሰጠ ህዝብም የተሰወረ የጥቃት ቅኝትን አመቻችቶ መላክም በሰማይም በምድርም ገሃነም የሚልክ ይሆናል።

 ይህ ሃላፊነት እና ቁርጠኝነት ከሁለቱም መሪዎች ከኢትዮጵያ መንግሥት አና ከኤርትራ መንግሥት ያስፈልጋል። ሌላው ታጠቂው ለግብር ይውጣ ነው የታጠቀው፤ ደምሂት ግን ሙሉ ትጥቅና ሙሉ ብቃት ያለው ነው። ስለዚህ የጠ/ ሚረ አብይ ካቢኔ ሌላ ጦርነት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያሳውጅ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። መንፈሱ መርዝ ነው …

እንዲሁ የሚቀላቀል አይደለም። ይሄው ተሸንፈው እንኳን ያቅራራሉ … ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም መልሰው የኤርትራን ህዝብ የ የኢትዮጵያን ህዝብ ላለመበድል ብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርጉበት ይገባል። የመንፈስ ካሳ የምንፈልገው በዚህ መልክ ነው። ዛሬ የ አሰብን የድጋፍ ሰልፍ ሳይ ነበር። ትናንት የ አዋሳን አዬሁኝ። አሰብ እንዲያ አቧራ ለብሳ ወደብ ያላት ማለት ነው፤ አዋሳ ደግሞ ያን ያህል የ አባባ ወርቅ ይዘንብባታል፤ የህዝቡ ጸዳል እና ውበት፤ የ አዬሩ ለዛ እና ማዕዛ ማገናኘት አይቻልም። መመዘነም። ሰሊዘህ መለዬቱ ያተረፈው ነገር ቢኖር ኤርትራ የ እኔ የምትለው ሰንደቅ ዓላማ ያላት መሆኑ ነው። በቃ …
  • ·       ውስጤ ያዘንኩበት።

ዛሬ ጥዋት አዲስ ቢዲዮ ሳይ ነበር፤ ከበረንቱ፤ ከአሰብ፤  ከተላያዩ የ ኤርትራ ከተሞች ህዝባዊ ድጋፎችን፤ ህዝቡ ራሱ ወጣት የለበትም። ወጣት ከተባለ ሴቶች ናቸው። ሌላው አዛውንታት እና እናቶች ናቸው በቃ። በብዙ ሁኔታ መንፈሳዊውን ህይወት የትወልድ ውርርስ ሲታሰብ ያልተገባ የፖለቲካ ትርምሶች የበደለው ህዝብን እና ትውልድን ነው።

ከዚህች ጊዜ በኋዋላ ከእንግዲህ ቢከፋኝ ብመለስ የሚሆን አይሆንም። ዕድሜውም እያለቀ ነው … ስለዚህ ፍቅርን ለማውረስ ጠላትን አስታጥቆ ከነትጥቁ ተፋለጥ ብሎ በጎረቤት አገር መሸኘት መሆን አይገባውም፤ … ደህሚት ከምንም ነገር ጋር የሚገጥም አይደለም። አሁን ግንቦት 7 ከነማሳሪያው መሆንን አይፈልገውም። 

መተኮስ ስለማይችልበት፤ ማቀባባል ስለማይሆንለት፤ ጎንደሬዎችን በተናጠል በቀያቸው እዬላከ ነው ሲፎክር የካራረመው፤ ጥሎበት ፈርዶበት እንጂ መሳሪያውን ሲያው ሲቀባባል ሲንቃጫቀጭ ይርዳል … የተጋድሎው ባለቤቱም ጎንደር ነው።

ስለዚህ እንኳን ከዚህ ጉድ አወጣህኝ ባይ ነው። ስለትም ያስገባል። የውሽማ ሞት ሆኖ የከረመው ጉድ 50 ዓመት ዕድሜ ቢጨመርለት ከተለመደው ቧልት ውጪ ለታዳሚው የሚቀርበው የ እውነት ቅርጥምጣሚ አልነበረውም። ያልተፈጠረበት ነበር እና ትጥቅ ትግል። ወኔው በትውስት የተኮፈጠነ ስለነበረ። ሌላው ሚስጢር ግንቦት 7 እኮ በትጥቅ ትግሉ ሆነ በዴያስፖራው የተኮፈሰው በአማራ ነበር። 

አማራ ወደ ቤቱ ሲገባማ ታዬ እኮ። በቃ … እርሾ ነው ያጠው ለዚህ ነው። አሁን ሰማያዊን በይፋ በስውር ደግሞ አብን መንፈስ ላይ ተንጠልጥሎ ያለውም ለዚህ ነው። ማን ቀንበር ይሸከማል ለዬዘመኑ የምርክሲስት ሌሊኒስት አየዝና አርበኞች ካለ አማራ በስተቀር። … 

አብን ነገ ድምጽ ላይ የግንቦት 7 ጃንጥላ ያዥ ነው የሚሆነው። ከዚህ ድስት ስታጥብ እንደነበረቸው የ አማራ ልጅ አሁንም ያረግርግ አማራ በአብን ሥም …

ምክንያቱም ከለ አማራ ነፍስ ቁማ አትሄድም እና የ አንዲት የፖለቲካ ድርጅት ሩህ። … አማራ መድህን ነው። ደግሞ የተጋድሎውን ነፍስ ያደመጠው የገዱ መንፈስ እንጂ የሰማያዊ ቅኝቱ አብን አይደለም። 

አማራ ተገድሎውን ታሪክ እልባ ሆኖ እንዲቀር ከፈለገ አሁንም ክብሩን ደፍቶ ከአብ ጋር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ቀለበት ጋር ይስር። ከዛ ያገኛለታል። እንደ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ሥሙ ከስሞ፤ ተጋድሎ ተቀብሮ ይቀርለታል። 

ምርጫው የእሱ ነው … ደግሞ የሰማሁት ጎንደር ላይ ጉባኤ እንደተካሄደ ነው ወይ ማለገጥ … የተለመደ እኮ ነው ግንቦት 7 አንገቱን ደፍቶ ይሄም ያነም የ እኔ አይደለም ይልና እግር ሲያወጣ የእኔ ነው ብሎ ዘራፉን ተኖረበት ….

የሆነ ሆኖ ወደ ኤርትራ ስላስታጠቀቻቸው የሞገድ፤ የኔት አርበኞቹ ትጥቅ ጉዳይ  … ሁሉም ቦታ እኩል እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። አንድ ሰሞን  የአዲሱ ለውጥ አበባ መፈንደቅ ሲጀመር ህብርን ተንተርሶ ሲያቅራራ የከራረመው የአማራ ታጣቂ ነኝ ባይም ቢሆን ማንኛቸውም ድርጅት ከነትጥቅ ከኤርትራ፤ ከሱዳን፤ ከኬንያ፤ ከሱማሌ፤ ከሱዳን፤ መግባት መታገድ ይኖርበታል …

ይህ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ሊሰጠው ይሚገባ ጉዳይ ነው …  የአብዩ ካቢኔ ከሱዳን፤ ከኬንያ፤ ከጁቡቲ፤ ከሱማሌ፤ ከኤርትራ ጋር ቋሚ የሆነ ውል መዋዋል ይኖርበታል። አብሶ ኤርትራ ወደ ሱዳን፤ ወደ ኬንያ ወደ ሱማሌ ከነትጥቅ የምትሸኘውን ያስታጠቀችውን የሞገድ የኔት የስልክ አርበኛ ትጥቅ አስያዛ የምትሸኝ ከሆነ ታጥቦ ጭቃ ነው የሚኮነው።

የኤርትራ ህዝብም ፍቅሩን መንከባከብ መቆጣጠር የሚጋበው መንግሥቱን ይህን መሰል እርምጃ እንዲወስድ ሲያስገድድ ብቻ ይሆናል። የኢትዮጵያ እናቶች ከእንግዲህ ለአክተሮች የሥልጣን እና የዝና መስተዋደድ ስንቅ፤ ብርንዶ የሰው ልኳንዳ ቤት እንዲከፍቱ ሊገደዱ አይገባቸውም በፍጹም በፍጹም …. በጠረፍ የሚገኙ አካባቢዎችም ከአብዩ የተሻለ ምንም ዓይነት መሪ መድር ልትፈጥር ስለማትችል መንፈሳቸውን መጠበቅ ግድ ይላቸዋል።

 ጸጉረ ልውጠችን በማናቸውም ሁኔታ ማጋለጥ እና የ እዮርን ሥጦታ የለማ የገዱ የ አብይን መንፈስ መጠበቅ መንከባከብ፤ ከጥቃት መታደግ ግድ ይሆናል። እብሶ የኤርትራ መንግሥት ያስታጠቀውን የደህሚት ሠራዊት ወደ ሱዳን ሸኝቶ ሰቲት ላይ አሰፍራለሁ ካለ ጠቡ የዘለላም ይሆናል። 
ሄሮድስ መለስ ዜናዊ የተከለው ነቀርሳ ይበቃናል።

Freedom! ነፃነት! 05.22.2018


አውጊ አደራው ደምሂት ይህን መርዶ ተመልከተው … ስንቱ ሰው ለማዬት እንኳን እንደሚያቅለሸልሸው ከልብህ ሆነህ እሰበው … አይበቃም የ27 ዓመቱ መከራ … አንዲት በሰላም እጦት ሳትታውክ ባዕትህ በሚሊዮን ግብር አለሁበት አትበል፤  ማፈሪያ!
የኔዎቹ ይሄው ነው ለነገሩ ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው ተማሩም፤ ተመራመሩም፤ አዋቁም፤ ነቁም፤ አንባሳደር ሆኑም ያው አራት ማዕዘን ሳጥን … በቃ ….






ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ቅኖቹ ልባሞቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።