ተፈጥሮን ያዘመነው የማሰብ ፍልስፍና ልቀት ነው።
መሆንን በማሰብ፤ መሆንን በመቻል፤ መሆንን በመሆን። „ይህ ህዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤“ የማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 28.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። v መ ቅድም። መሆን በመሆን ቢጣፋ? መሆን በመሆን ቢባዛ፤ መሆን በመሆን ቢቀመር በመሆን ውስጥ መኖርን ያጠይቃል። መሆንን ማሰብ፤ መሆን በመቻል ማቻቻል፤ መሆንን በመሆን ማትጋት ሁሎችም የተፈጥሮ መብቶች ናቸው። ልዑል እግዚአብሄር የሰጠን። እርግጥ ነው መሆንን ማሰብ ገደብ የለውም። መሆንን መቻል ግን የሚከብዱ ነገሮች ይኖራሉ። መሆንን በመሆን ዕውን ለማድረግም እንዲሁ።አንደኛው ለምሳሌ ሊሆኑ የፈለጉትን አለማግኘት ነው። v መ ሆንን ማሰብ። መሆንን ማሰብ የሚነሳው ከራስ ብቻ አይደለም ከቤተብም ከአካባቢም ሊሆን ይችላል። ብቻ መሆን ማሰብ እስከ ዕድሜ ልክ አብሮ አድጎ እስከ ገሃዱ ዓለም ሥጋዊ ስንብት ድረስ አኗኗሪ ነው። በዚህ ውስጥ ማሰብ ራሱን የቻለ መክሊትም አለው። ከአካባቢ ወጣ ያለ ምናባዊ፤ ፍልስፍናዊ እሳቤም ይኖራል። ማሰብ ድንበር የለውም እንደ ተፈጥሮ ጸጋ ለሚያዩ አካላት። መኖር የተፈጠረው በማሰብ ሃሳብ ውስጥ ነው። ማናቸውም የመኖር ሁለመና መሰረቱ በማሰብ ልቅና የተገኘ ነው። ከማስብ ልቅና፤ ከማሰብ ብልጽግና ውጪ የሚፈጠሩ የፈጣሪ ፍጡራን እና ተፈጥሮ ብቻ ነው። ተፈጥሮን አሰልጥኖ፤ ተፈጥሮን ዘመናይ ያደረገው የማሰብ ፍልስፍና ልቀት ነው። v መ ሆንን በመቻል ማቻቻል። ሊሆኑ የፈለጉትን ቢያገኙትም በመሆን ውስጥ ካልተከተበ ብላሽ ነው መሆንን ማሰቡም ሆነ መሆንን በመቻ...