ልጥፎች

ከጃንዋሪ 6, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጥሞና በማስተዋል ከቀለመ የህሊና ብርኃን ነው።

ምስል
      ጥሞና በማስተዋል ከቀለመ የህሊና ብርኃን ነው።  መኖርን እና ተስፋን ለስኬትም ያበቃል።  አደብ የገዙ ፖለቲከኞች ይመስጡኛ።  አደብ ብቻ ትውልድ እና አገርን ያድናልና።  ዝምታም የፖለቲካ ጎዳናነቱ ቫልዩ አለው እያልኩ ነው። ኑሩልኝ የኔወቹ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ 2024/01/5 ጊዜ ቅኔ ነው።

የማድመጥ ክህሎት የማስተዋል ዊዝደም ነው።

ምስል
 የማድመጥ ክህሎት የማስተዋል ዊዝደም ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

መሪነት ያለተመስጦ?

ምስል
       መሪነት ያለተመስጦ?  መሪነት ያለጥሞና?  መሪነት ያለተደሞ?  መሪነት ያለዊዝደም የእንቧይ ካብ። ሥርጉትሻ 24/05/01

የኔታወቼ ማህበረ ቅንነት ክብረቶቼ እንኳን አደረሰን።

ምስል
  የ ኔታወቼ ማህበረ ቅንነት ክብረቶቼ እንኳን አደረሰን።        መድረስ አልቀረብንም እንሆ ለብርኃነ ልደቱ ደረስን። ተመስገን ሲያንስበት። ሰማዕቶቻችን እያሰብን፤ የፈቃድ ዘብ አደሮቻችን እያስታወስን አቅማችን በክብር እዬለገሰን ክብሩን በክብር እናክብር።   አብረን ለመዝለቅ ቅንነት በትህትና ያስፈልጋል። ግልጽነት በፍፁም ታማኝነት ይሻል፤ ሰዋዊነት በተፈጥሯዊነት ይጠይቃል። ወዶ ገብነታዊ ዲስፕሊን ልንለው እንችላለን።   ከዕንባ ጋር መቆም ውስጥን ይጎዳል፤ ጤናን ያጓድላል። ከቤተሰብም ሊለይ ይችላል። ብቸኝነትን ሊሸልም ይችላል። መኖርን ማኖር ባልፈቅድነው ልክ የቤተሰቦቻችን ጊዜ ይሻማልና። ቻሌንጁ ከባድ ነው።    በሌላ በኩል ደግሞ የምንታገለውን ጭካኔ እና ጥላቻ በአድማ ተነስተው መኖራችን ያዋክቡታል። መታመንን የሸጡ ሰብዕናወች አደጋምይደንቃሉ። ግን አለን። ትርታችን በሱ ቸርነት ቀጥሏል። ተመስገን።   ስንብታችን ቢታቀድም የፈጣሪን ጥሪ ሳያሸንፍ እንሆ ልደትንም አዬን። ለዛውም የምድር እና የሰማዩን ንጉሠ ክርስትስ። ምስጋና ለአማኑኤል።   አለሁኝ። አወን አለሁኝ። የነጮችን አዲስዓመትም፤ የውስጤን ማተባዊ ብርኃነ ልደትንም አዶናይ አሳዬኝ። አለሁኝ! ኑሩልኝ ከእኔ ጋር የዘለቃችሁ ውስጦቼ ጽናቶቼ። እንኳን አደረሳችሁ። አሜን።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ" ሥርጉትሻ 24/06/01