የአማራ ህዝብ ከቶ ወደ #ማርስ ይምጠቅላችሁን?????? ሞፈር ቀንበርን ለምን #ታነዱታላችሁ??? የአማራን #ገበሬ ለምን #በድሮን ታነዱታላችሁ? መሬቷንስ ለምን #በቦንብ መርዝ ታነዟታላችሁ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።"
የአማራ ህዝብ ከቶ ወደ #ማርስ ይምጠቅላችሁን?????? ሞፈር ቀንበርን ለምን #ታነዱታላችሁ ??? የአማራን #ገበሬ ለምን #በድሮን ታነዱታላችሁ? መሬቷንስ ለምን #በቦንብ መርዝ ታነዟታላችሁ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እህል አልባ መኖር አለን? ዘር አልባ የሰው ልጅ ይቀጥላልን? ውኃስ አልባ መተንፈስ ይቻል ይሆን? የኦነግ ጠረን የተላበሰው የኦህዴድ ወራሽ ብልጽግና የአማራ መሬት ይመረዝ ዘንድ ተግቶ እዬሰራ ነው። ለትውልድ እንዳይደርስ አርቆ በማሰብ ጠፍ የማድረግ ብቻ ሳይሆን በተመረዘ መሬት የሚበቅል አዝዕርት ለትውልድ የአካል አፈጣጠር እክል ይሆናል። #ገበሬን በቦንም? ገበሬን በአውሮፕላን #መጨፍጨፍ ? ምን ይባል። በአማራ ህዝብ ተገድሎም፤ ተዘርፎም፤ ተገሎም፤ ታስሮም፤ ተሰውሮም፤፦በገፍ በዬተገኘበት ተጨፍጭፎም የተረፈው በራህብ ያልቅ ዘንድ የጠቅላይ ሚር አብይ መንግሥት ተግቶ እዬሠራበት ይገኛል። የምርት ሰዓት፤ የእርሻ ወቅት ጠብቆ ይቀጣል ያሳዳል። ሲያሻውም ሰብሉን መስክ ላይ የዶግ አመድ ያስደርጋል። የአገር ልጅነቱን ፍቆ የውጭ ወራሪ ነው የሚመስለው። መሃከነ። የሚገርመኝ አብረው የሚሠሩት የአማራ ግዑዛን ናቸው። ህሊና የሚባል ያልሠራላቸው #ገደላገደሎች ። እኔ የገበሬ አደራጅ ነበርኩኝ። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን መሪ በአካል አግኝቼ ነበር። እናም መልሼ ላላገኝሽ እችላለሁ እና ምን ላድርግልሽ ሲሉ በትህትና ጠየቁኝ። ጎበዝ ተማሪ ነኝ። ውጭ አገር ለትምህርት ላኩኝ አላልኩም። ወይንም አዲስ አበባ የተሻለ ሥራ ይሰጠኝ አላልኩም። ወይንም እዚህ ሥራ ይሰጠኝ አላልኩም። የጠዬቅኩት ገበሬ መንደር ሄጄ ገበሬ ማደራጀት ነው እም...