የተከበረውን አቶ ኦባንግ ሜቶ አስመልክቶ ፀፀት የለብኝም። ይድረስ ለወዳጄ ለአቶ ኦባንግ ሜቶ። ከአለህበት። #ምዕራፍ ፲፬ "የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 

የተከበረውን አቶ ኦባንግ ሜቶ አስመልክቶ ፀፀት የለብኝም።
ይድረስ ለወዳጄ ለአቶ ኦባንግ ሜቶ።
ከአለህበት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
#የአፋልጉኝ #ትሁታዊ #ጥያቄ#ጠይም #ዕንቋችን #እናፈላልግ#አቶ #ኦባንግ #ሜቶ የት ነው ያለው? ምን ገጠመው? ምንስ ሆነ? ታመመን?
 
እጅግ የማከብርህ፤ የምሳሳልህ ወንድሜ አቶ ኦባንግ ሜቶ በቀድሞው አጠራሬ #ኦባንግሻን ዶር ኦባንግ #ኢትዮጵያ በአያሌው እንዴት ባጀህልኝ? ባለቤትህ እንዴት ናቸው? መላ ቤተሰብህ እንደምን ነው? የምታፈቅራት ኢትዮጵያ ጠረኗ እንዴት እና እንዴት እያደረገህ ይሆን? ታድለኃል ልበልህ ይሆን? ጠቀሜታውን እምታውቀው አንተው ነህ።
 
ለመሆኑ ኢትዮጵያ እንዴት ናት? ያቀድከው #ተስፋስ ዕውን ማድረግ ችለህ ይሆን? የአውሮፓ ህብረት ሽልማት ሲያልፍህ በጣም አዘንኩኝ። ብዙ የተጋህ ድንቅ የሰባዕዊ መብት ተሟጋችም ነበርክ። ከመኪና አደጋ ከሞት ተርፈህ፦ ተድረህ፦ አገርህ ገብተህ በተወሰነ ደረጃ ከምታከብረው ህዝብህ ጋር #መሳቅህ ቢያስደስተኝም ለረጅም ጊዜ #ድምጽህ #መጥፋቱ ግን ሰርክ #ይጎሰጉሰኛል
 
የእኛ ውድ #ጠይማችን ዕንቁ አንተን የበላ ጅብ አልጮኽ አለ። አዲስ ዓመት መጥቶ ሲሄድ ድምጽህን መስማት አልቻልኩም። ለነገሩ ክቡር ኮነሬል ጎሹ ወልዴም አገር ሲገቡ ከነበረው ሴሪሞኒ ውጪ የት እንዳሉ፤ በምን ሁኔታ እንደሚገኙ መረጃው የለም። የተከበሩ አንባሳደር ካሳ ከበደም ከብዙ የዝምታ ጊዜ በኋላ በሥጋ መለየታቸውን አዳመጥኩኝ። ፀጥታ፤ ዝምታ። ጥሞና ታቅዶ ከተፈፀመ መልካም ነው። ተጫኝ እና አስገዳጅ ሁኔት ካልኖረ።
 
ታስታውስ እንደ ሆነ #ነሐሴ 2010 እንደ አገራችን አቆጣጠር #ተስፋችን #ተጠልፏል #የመንፈስ #ትጥቅህን አትፍታ ብዬህ ነበር። ለዛውም እኔ ስልክ መደወል አልወድም። ግን ደወልኩልህ። ነገርኩህም። #ፀፀት የለለብኝም ለዚህ ነው። የሚገርመው በነገርኩህ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያ መግባትህን አዳመጥኩኝ። አልከፋኝም ነበር። እኔ ጥንቃቄ ታደርግ ዘንድ፦ እንዳትዘናጋ ነበር ትሁታዊ ማሳሰቢዬ የነበረው። ተስፋ ማድረግ አወንታዊ ነው። የፈጣሪ ክቡር ስጦታም ነው። ሊያስወቅስ አይገባም እንደ ማለት።
 
አገር ከገባህ በኋላ የክብር አቀባበሉን በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አዬሁኝ። ብዙም ለዚህ መሰል ሴሪሞኒያል ጉዳይ አድናቂ አይደለሁም እና እንደማንኛውም ሁነት ተመለከትኩት። እኔ የሚመስጠኝ ለአቅም የአቅም ዕውቅና ተሰጥቶት ባለ አቅሙ አቅሙን ኢንቤስት የሚያደርግበት ሁነት ሲመቻችለት ነው እማደንቀው። ልክ እንደ አቶ ሙስጦፌ። የሳቸው የተሳካ ሪኮመንዴሽን ነው ባይም ነኝ። የነገን ባላውቅም። 
 
የሆነ ሆኖ #በአማራ ክልል እና #በጋንቤላ እንዲሁም #በአዲስ አበባ የነበረህን የመድረክ ቆይታም እከታተል ነበር። ልቤን ጥያ ግን አልነበረም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትብትብ ስለሆነ #ቅንነት #በብልህነት ካልተመራ አደጋው ሰፊ ነው እና ስጋት ነበረብኝ። 
 
ይህን አልሸሽግህም። ይህ የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥት ስለሆነ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኦሬንቴሽን ቅንነት እና አዛኝነት የነጠፈበት ስለሆነም ነው።
 
በተለይ በሚዲያ አንተን፤ አቶ ጀዋር እስር ቤት እያለ፤ አቤ ገላውን አስመልክቶ በቀድሞው የጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ #የኢንሳ ተሳትፎ አስመልክቶ የነበራችሁ ሚና በሚዲያ ስሰማ እጅግ ደነገጥኩኝ። እንደምንስ አቶ ጃዋር እስር ቤት እያለ፥ ኦባንግሻ እና አቤ ኢትዮጵያ እያሉ ለምን ይህ ጥልቅ ጥንቃቄ የሚገባው መረጃ ተሰጠ ብዬ ፃፍኩኝ። ጠቃሚም አትራፊም ስላልነበር። ሆድ ብዙ ይችላል እኮ። የዕድሜ ተመክሮስ የት ላይ ይረፍ። 
 
ምክንያቱም እኔም ብሆን በእኔ ላይ ስላሉ ጉዳዮች በአሉታዊ መልኩ ስሰማ፤ የተከደነ ሚስጢር ሲከፈት ያን መታገል ሰብዕናዬ ይፈቅዳል፤ ተፈጥሯዊም ነው። እራስን መከላከል። በእኔ ቢሆን ብዬ ሳስበው ማለት ነው። ከዛ በኋላ #አብዝተህ መዘናጋትህ የተገባ አይመስለኝም ነበር። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በራሱ የመጣን ነገር እንዳሻህ ሁንበት የሚልበት አመክንዮ ስለለ።
 
ለነገሩ ያ መረጃ በእጃቸው የነበረ ወገኖቻችን ከድነው መያዛቸው ለጠ/ሚር አብይ አህመድ እስከ ኖቤል ሽልማት ያበቃውን ክስተት በጽኑ አግዟል ብዬ አስባለሁኝ። የሚሊዮን ፍቅርንም በገፍ እንዲያገኙ ረድቷል። ቀድሞ ቢሰማ ተጽዕኖው ኃይለኛ ነበር። በተለይ ጠንቃቃ ዜጎች ድጋፋቸውን መመጠን ይችሉ ነበር። ስለዚህ ለጠሚ/ር አብይ አህመድ መረጃው ቀድሞ የነበራቸው ወገኖች በአመክንዮው ላይ የጣሉት ማዕቀብ ለጠሚር አብይ አህመድ አሊ ያገዘ፤ የረዳ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነበር። 
 
ስለሆነም ይህን ላደረጉ ወገኖች ምስጋና እንጂ ሌላ ነገር ባይታሰብባቸው ፈቃዴ ነው። ትልቅ ኢሹ መንፈስን የሚሰነጣጥቅ ጥብቅ መረጃ በጥንቃቄ መያዙ ለኦሮሞ ፖለቲከኞች አትራፊ እና ጠቀም ነበር። ለሥልጣን ይሁንታ ካሰጡ በኽረ ጉዳዮችም በዚህ ጉዳይ ላይ ያልተገደበ ድጋፍ ባደረጉ ወገኖችም ነበር።
 
የሆነ ሆኖ ቅኑ ወንድሜ ኦባንግሻ የት ነው ያለኽው? አመመህ ይሆን? አሞህ ከሆነ እግዚአብሄር ይማርህ። አሜን። ብቻ፦ አወን ብቻ የሚሊዮን ፍቅርህን "ለውጥ፦ መደመር" ለሚባል ፖለቲካ በገፍ ሳትሰስት ያስረከብክ ደግመንም ልናገኝህ የማንችል ቀለማችን፤ ህብራችን፦ ልዩአችን ነህ እና ቸርኽን ያሰማኝ። ቸር አስቤ፤ ቸርነት ተስፋ አድርጌ፦ ቸሩ መዳህኒተዓለም የምሥራቹን ያሰማን ዘንድ እማጠነዋለሁኝ።
 
እኔ እንዲያውም ምኞቴ የነበረው በአንድ ዓለም ዓቀፍ ተቋም ኢትዮጵያን ወክለህ ስትደምቅ፤ ስታበራ፤ ስትፍለቀለቅ ማዬት በእጅጉ ናፍቆኝ ነበር። ግን አልሆነም። ያ ቀርቶ ትርታህ ከሰነበተ መልካም ነው። ለኢትዮጵያ ዋቢዋ፤ ዋሷ፦ ተሟጋቿ ኦቦግሻ ደህና ሰንብት። ደህናም አምላካችን ያድርግህ። አሜን። ኑርልን። አሜን። 
 
ኦባንግሻ አገር ከገባ በኋላ ካናዳ ወይንም አሜሪካ እንዳለ ዜጋ ሃሳቡን በነፃነት ይገልጽ ነበር። ሥርዓቱ ሳይዘረጋ ይህን መሰል መጠነ ሰፊ የአሰተሳሰብ ነፃነት ኢትዮጵያ ምድር ማሰብ እራስን ለማገዶ ከማቅረብ ውጪ ትርፋማ አይሆንም። አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ተቋማቸው ጎልተው ለወጡ ተጽዕኖ ፈጣሪወች መብት ሲዳጥ ይሞግታሉ፤ ግን በበዛ ጥንቃቄ ነው። እስከ አሁን ደህና የሆኑትም ለዛ ይመስለኛል።
 
የኢትዮጵያ የፖለቲካ መስመር ሊሂቃኑ የተቀረፁብት መሠረት የሶሻሊስቱ ነው። ያ ደግሞ ለሃሳብ ነፃነት ቦታ የለውም። ያለው መጠነ ሰፊ ቦታ ለዲሞክራሲ ማዕከላዊነት ነው። ጠሚ/ ሩ "አቶ - ፈ" ይሁን አቶ "ዘ" ይሁን "ቸ" ይሁን አቶ "ዠ" ይሁን ታክቲኩ ይለዋወጥ እንጂ ኦረንቴሽኑ ወጥ ነው። ለዚህ ነው እኔ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን ያስተሳሰብ ለውጥም ያስፈልገናል የምለው። 
 
አሁንም ተግተን በስክነት ልንሰራበት የሚገባው ጉዳይ ግለሰባዊ ርዕዮት ላይ ሳይሆን ተቋማዊ ሥርዓት መገንባቱ ላይ ነው። ይህ በእኛ ዘመን ሊሆን ባይችልም ግን ሥራወች መጀመር አለባቸው። አሁንም የተነጠለ፤ የተበታተነ፤ የተቆራረጠ፤ የሸነሸነ እና የተሸበሸበ ተሳትፎ ነው እማስተውለው። ጥረትም ነው እማስተውለው። የአንድ ሰው አቅም ብዙ ነው። ቅንነቱ እና ተፈጥሯዊነቱ ከዘለቀው። አይደለም የስብስብ። 
 
ሌላው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ውራጅ ርዮት አያስፈልገውም። በፍፁም። ኢትዮጵያኒዝም በቂ ነው። ጥልቅም ነው ፍልስፍናው። እንኳንስ እኛን የዓለም ህዝብን አሰባሳቢ እናት ሊሆን የሚችል ቀደምት ንጥር ነው። ወደ ተፈጥሯችን በቅንነት እንመለስ ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን። አሜን። 
 
አንድ ደፋር ፖለቲካ ፈጣጣ ሃሳብ በአንከር ሚዲያ አቅርበው ነበር። "ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ ካልተመቸን መቀዬር እንችላለን" አሉ። ሰውነቴ ነው የተንዘፈዘፈው። እኛ በህይወት እያለን??? "ምን ብቀጥን ጠጅ ነኝ "ይላሉ ጎንደሬወች ሲቃኙ። አቅም አለን። ለጭብጨባ የማያሸበሽብ። የሆነ ሆኖ የድፍረትም ልክ አለው።
 
ሰሞኑን" ጀግና" ተብለው በአንድ ሚዲያም ሲወደሱ ነበር። ኧረ እባካችሁ እያጣራን እንጓዝ። ውድቀታችን እኮ ይኽው ነው። የሰብዕና ግንባታ እና ጥንቁቅነት አለመደጋገፍ ያመጣው የፖለቲካ ኪሳራ ነው የሚያሳፍሰን። ፈሰናል እኮ። የተደከመለት ሊሂቅ ሁሉ እኮ ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው አየነው። የሆነ ሆኖ ለፓን አፍሪካኒዝም፤ ለቡኒ ጠይም ግሎባሊዝም ዕንቁዊነት ኢትዮጵያኒዝም ጉልላት ነው። "በቅርብ ያለ መዋት የቹቻ መንከሪያ ይሆናል" ይላሉ ባለ ቅኔወቹ ጎንደሮች። 
 
ውዶቼ እንዴት አደራችሁ? #ኦባንግሻን #አፈላልጉኝ። ኦባንግሻ የኢትዮጵያኒዝም ጣዝማ ነው። ቅንም ይመስለኛል። ጠቅላይ ሚ/ር አብይን ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተሬ ያለም ነበር። በዛ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅናው በግርማ ያበራ በነበረበት ዘመን። ትልቅ የህይወት ውሳኔ ነበር።
ኦባንግሻ በዲያስፖራም ቸገረኝ ላለ ሁሉ አጽናኝ፤ አይዟችሁ የሚል ነበር። በአካል ተገኝቶ ችግርን የሚጋራ ሊቀ - ትጉኃን ነበር። 
 
የውጭ አገር የሚሊዮኖች ድምጽ አንባሳደርም ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አቅም ቢኖረው ቻሌንጁን ሆኖ በመገኜት ማሸነፍ ይችልም ነበር። ባለሥልጣኑ አዛዡ ነዛዡ እሱው ስለሆነ። ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የእኔን መሰል ከዬትኛውም ስብስብ፤ ይሁን ተናጠላዊ ግንኙነት እራስን ያገለለ ለሰው ስዋሰዋዊነት የሚታገል ሥልጣንም፤ ቻቻታም፤ ውዳሴም የማይናፍቀው የግንባር ሥጋ ያስፈልጋል። ልምዱ፤ ተመክሮው ዕውቅናው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ህብራዊነት ፍቱን ነውና። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
00/10/2024
 
#እንፈላለግ!
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ውዶቼ እንዴት አደራችሁ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።