#አማራነትን አታሰቃዩት።

 

#አማራነትን አታሰቃዩት።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
አቶ ቴወድሮስ የአብን አመራር ነበሩ። ግልጽና ቀጥተኛም ናቸው። በሙያቸው በተመረቁበት መስክ ተደላድለው መሥራት ሲችሉ የእትብት ችግርን ልጋራ ብለው አብን ተቀላቀሉ። በጣም ደፋር የሆኑ አስተያዬቶችን በግል ሲያቀርቡ አስተውል ነበር። ከታሠሩ ጀምሮ በእሳቸው ዙሪያ የሚተጋ አንድም ቀንጣ ነፍስ አላዬሁም። ከስብስቡ የወል የመታገያ ምስልም የሉም። ለምን?
 
አይዋ አብን "አንድ አማራ ለሁሉም አመራ" ብሎ ሲያስፈነድቅ ምነው ለራሱ መሆን ተሳነው? ፓርላማም፤ ምክር ቤትም ተመርጠው የገቡ ወገኖቹ ለካቴና ሲዳረጉ ዝም። በቃ ዝም። አቶ ካሳ ተሻገርም ጠንካራ ሞጋች ናቸው።
 
አይዋ አብን ለሽ እንዳለ ነው። አሁንማ #መቅኖውን ለብልጽግና ቀላልቦ ዕጣ ነፍሱን እንደቀረ የሰሞናቱ የኢታማጆሩ ቃለ ምልልስ እርቃኑ መሆኑን አስገነዘበን። አያድርስ ነው። ያን ሁሉ አቅም #ሜዳ #አደር አድርጎ #በከንቱነት የቀረ #ጉደኛ። የሆነ ሆኖ የአማራ ፖለቲከኞችን እያደኑ ማሰር ይቁም። 
 
የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነኝ ቢልም አሳር፤ አማራ ነኝ ቢልም ፍዳ። በእሳተ ጎመራ ላርባ የሚገረፍ፤ ቀጭወቹን ሃግ የሚል የጠፋበት ዘመን ነው። ያው ባለ ኮፒራይቱም ወዘተረፈ ስለሆነ በግል ለሚተጉ የእኔን መሰል ባተሌወች ጋዳ ነው። ዝም ስንል ደግሞ እንዲህ የሚረሱ፤ ጨርሶም የማይታወሱ ወገኖች ቁጥር በረከተ።
 
ለመሆኑ እነሱስ ቤተሰቦቻቸውስ በምን ሁኔታ ይገኙ ይሆን? ጤናቸውስ በምን ደረጃ ይገኝ ይሆን። ሙሉ ስድስት አመት በእስር መጋዝ። ምን ይጠና የአማራ ሕዝብ? ምንስ #ከብረት #ቁርጥራጭ #የተሰራ #ጽናት አደለው ፈጣሪ???? 
 
በዬደቂቃው፤ በዬሰከንዱ የሚታገተው፤ የሚታደነው፤ የሚገደለው፤ የሚሰወረው ብዛት የማናውቀውንም፤ ያልሰማነውንም ፍዳ የተሸከመ መከረኛ ምፃተኛ። የብልጽግና ቁንጮ ሹሞች የምን የህልውና አደጋ ሲሉ ሲያላግጡ አደምጣለሁኝ። ሰው ሆነው፤ በአማራ ሁልአቀፍ ተጋድሎ እና ትሩፋት ሙሉ ድምጽ ሥልጣኑ ተገኝቶ መመፃደቅ። ይሉኝታ ያልፈጠረላቸው ሰብዕናቸው።
 
የኦሮሞ ፖለቲካ ለአማራ ሕዝብ #ከፍሎ #የማይጨርሰው #ዕዳ አለበት። #ህሊና ቢኖረው። አዙሮ የሚይ አንገት ቢኖረው ኖሮ። ይህን ያህል የኦሮሞ ፓለቲካ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አውራ ሆኖ ክብር፦ ሞገስ፤ ሹመት እና ሽልማት የተዛቀው #በአማራ #ህዝብ #በጎ #ቸርነት እና #ያልተገደበ #ቅንነት ነበር። 
 
የኦነግ ፖለቲካ የት ያምጣው ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ፤ ኢትዮጵያዊ ጠረን፤ ኢትዮጵያዊ ማዕዛ፤ ኢትዮጵያዊ ቃና፤ ኢትዮጵያዊ ለዛ፤ ኢትዮጵያዊ ውበት፤ ኢትዮጵያዊ ሳቢነት? እሷን ተፃሮ ቁሞ። #ጥብቆ። የአማራ ሲቢላይዜሽን ሁለመና ነው። ካላማራ ሲቢላይዜሽን ቅንጣት መንቀሳቀስ አይቻልም።
 
ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል ይላሉ ልባሞቹ ጎንደሬወች ……… 
 
ሰሞኑን ሰይፋሻ የኦሮሚያ ቱሪዝም ሲል ቃለ ምልልስ ያደረገች ደመ ግቡ ወጣት ነበረች። የኢትዮጵያ ለምን አላለውም። ሸማው የማን ነው? የኢትዮጵያ አይደለምን? የገረመኝን አንድ ነገር አያይዤ ላንሳ አማራም ውብ ተመርጣ ነበር በዘመነ እናትዋ ጎንደር የአስቶርዬ እሷን አላናገረም። ለእሷ ዕውቅና አልሰጠም።
 
ባለገሩ ሦስት ዓመት ተኩል ብዙ ደክሞ ያስመረቃቸውንም ቃለ ምልልስ አላደረገም። ነጥሎ ሦስተኛ የወጣውን ስሚዝን ብቻ ቃለ ምልልስ አደረገ። እሱ #ታብዮ ሽልማቱን አልቀበልም ያለ ወጣት ነበር። በትህትና አክብረው ሽልማቱን የተቀበሉትን ግን ዕውቅና ሰጥቶ አላነጋገረም። ይህም ብቻ ሳይሆን የባላገሩ ጥረት ውጭ አገር እንኳን ያልታዬ ድንቅ ትጋት ነበር። ባላአገሩ በሰይፋ ሸው ሊጠዬቅ ይገባ ነበር። 
 
አሁን አሁን ሳዬው ሰይፋሻ ሾው ወደ ፖለቲካዊ ጉዳዮች #መመሰጥን አስተውላለሁ። ሪኮመንዴሽኑም ከዛ የሚመጣ ይመስለኛል በተለይ ከጠቅላይ ሚር ቢሮ እና ከከንቲባ ጽህፈት ቤት። ተወዳጅነት፤ ክብር እና ሞገስን በጥንቃቄ መያዝ ይገባል። የአማራ ክልል #ሚስ #ቱሪዝምን ሳያደንቅ፤ ዕውቅና ሳይሰጥ ከሁለት ዓመት በኋላ በፋክክር ለተከወነ ጉዳይ አትኩሮት መስጠት #ትውልድን #ማበላለጥ#ማግለልም ነው። የባህሉ መሠረትም #ዝበት ሊፈጠርበት አይገባም።
 
#ተጨቆነ፤ #ጫና ነበረበት የተባለውን ተፈጥሯዊ አለባበስ ይዞ መቅረብ እና ዕውቅና ማሰጠት ነው ልቡ ከኖረ። ሸማማ ባለቤት አለው። የቀደመ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅናም አለው። 
 
ይህም ሆኖ በአማራ ባህል፤ ትውፊት እና ትሩፋት እዬተቀማጠሉ፤ በደጋግ ኢትዮጵውዪን በተገነባች አገር አማራን ነጥሎ መቆሚያ፤ መቀመጫ መንሳት ከወንጀል አልፎ ማህበረ ኦነግ ሃይማኖት ካለው ኃጢያትም ነው። ዝምታው የሚያስተምር ነገር ከኖረው ተብሎ ነው። ሙግት ሲታገስ በተሻለ ፍጥነት ጎባጣን አቃንቶ፤ መታበይን ቀናንሶ በልክ በመሆን እራስን መግራት ያስፈልጋል።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/10/2024
አማራነትን አታሰቃዩት።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።