ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ሊከፈትለት የሚገባ ገናና ማንነት ነው።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ዘመን ኢትዮጵያዊነትን ይከሳል - ይፈውሳልም! „ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፤ መንገዴን የሚያቃና፤ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ፤ በኮረብቶች የሚያቆመኝ፤ እግዚአብሄር ነው።“ መዝሙር ፲፯ ከቁጥር ፴፪ እስከ ፴፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። መካሻ! · ወግ ቢጤ በሲቃ … እኔዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ዛሬ ወግ ወግ ብሎኛል … እንዲህ … እኔ ውጭ ስወጣ ከገጠመኝ ፈተና አንዱ የኢሠፓ መደበኛ ሠራተኛ መሆኔን እንድደብቅ ነበር ምክሩ እና ዝክሩ። እኔ ደግሞ ምንም የማፍርበት፤ አንገቴንም የሚያስደፋ አንዳችም ጸያፍ ነገር ስላልሰራሁ በአደባባይ የኢሠፓ ቋሚ መደበኛ ሠረተኛ እንደ ነበርኩኝ አወጅኩኝ። የሚገርመው ይህን የሚሉት በዘመነ ኢሠፓ የገበሬ እና የሠራተኛ ልጅ እዬተባሉ፤ ወይንም በራሱ በ ኢሠፓ ለከፍተኛ ትምህርት የተላኩት አውሮፓን ያጥለቀለቁት በስኮላርሽፕ ተልክው የተለያዩ ሙያ ሊቀ - ሊቃውንት የሆኑት ናቸው። የበሉበት እጅ የሚቆረጥሙ … ደርግም እንደ ብአዴን እጁ አመድ አፋሽ ነው … ተጠቃሚው እራሱ አያመሰግነውም እኮ … ተጠቃሚው ስል በገ...