ልጥፎች

ከኖቬምበር 18, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ጭካኔ ከዘር መል ይነሳ ይሆን? መነሻዬ የBBC ዘገባ ነው። ሳክል እኔ ጭካኔ #ፆታ የለውም የሚልም ሃሳብ አነሳለሁኝ።

ምስል
  #ጭካኔ ከዘር መል ይነሳ ይሆን? መነሻዬ የBBC ዘገባ ነው። ሳክል እኔ ጭካኔ #ፆታ የለውም የሚልም ሃሳብ አነሳለሁኝ።    https://www.bbc.com/amharic/articles/cn7e3rg4302o «በሂትለር ዘረ መል ላይ የተደረገው ጥናት ያስገኘው ውጤት እና የፈጠረው ሙያዊ ውዝግብ» ዝርዝሩ ከሥር ለጥፌወላሁኝ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #ጭካኔን በሚመለከት ሙሉ 15 ዓመት ሆነኝ ...   1) ጭካኔ ከየት መጣ? 2) ጭካኔ መቼ መጣ? 3) ጭካኔ እንዴት መጣ? 4) ጭካኔን ምን ይገታዋል?   በሚሉ ዙሪያ #ተመድን #የአውሮፓ ህብረትን መፍትሄ ነው ባልኩት ጉዳይ ጽፌላቸዋለሁኝ። እነሱም አክብረው መልስ ሰጥተውኛል። #የአዌርነስ የቃላት ፖስተር የምሠራበት ዩቱብ ቻናሌም ላይ ሠርቸበታለሁኝ። በአትኩሮት ማሰብ ስለሚጠይቅ ለተወሰኑ ዓመታት አልሰራሁበትም። ለመነሻ የሚሆን ሃሳቦች አሉበት። መጪው ትውልድ ሊሠራበት ይችላል።   የጸጋዬ ራዲዮ ከተመሰረተ ከ2008 እአአ ጀምሮም በቅንነት ዙሪያ ሠርቸበታለሁኝ። አሁን ሙሉ ለሙሉ ጭካኔ እና ክፋ ሃሳብን የሚታገል የራዲዮ ጣቢያ ሆኗል የጸጋዬ ራዲዮ። ቲክቶኬ በዚህው ዙሪያ ነው የሚሠራው። ስጀምረውም ለዚህ ዓላማ ነው። በአማርኛ የፖለቲካ ሙግት እምሠራበት ሁለተኛው ዩቱብ ቻናሌም አሁናዊ አቋሙ በዚህ #በፍቅር ተፈጥሮ ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኗል።   #ትንሽ ረፈት የሰጠኝ ቸር ዜና።   ሳይንቲስቶች፤ ተመራማሪወች የጭካኔን ምንጩን ለማጥናት ያደረጉትን ጥናት፤ ሙግታቸው ውስጤን ስላገኜሁበት ነው የBBC ዝርዝር መጣጥፍ የለጠፍኩት። ለእኔ በጣም ኢንተርስቲንግ ጉዳይ የሰው ልጅ ከጭካኔ፦ ከክፋ ...

Danke, Schöpfer. Krieg ist das Bermuda-Dreieck. ተመስገን ፈጣሪ። ጦርነት ቤርሙዳ ትርያንግል ነው።

ምስል
  Danke, Schöpfer. Krieg ist das Bermuda-Dreieck. ተመስገን ፈጣሪ። ጦርነት ቤርሙዳ ትርያንግል ነው።…  ጦርነት ይቁም። ለምን? ሥልጣኔን ሥልጣኔ ሊያወድመው ስለማይገባ። (Der Krieg muss aufhören. Warum? Weil die Zivilisation des Friedens nicht durch die Zivilisation des Krieges zerstört werden darf.)   • ለሰው ልጆች ሁሉ፥ ለፍጥረታት ሁሉ፤ እንዲሁም ለተፈጥሮ እና ለስልጣኔም ለሁሉም የሰላም ነፃነት ሊሰጣቸው ይገባል። Allen Menschen, allen Geschöpfen, der Natur und der Zivilisation muss die Freiheit des Friedens gewährt werden.   « የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።» (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፲፱)       የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛን እና የእስራኤልን ጦርነት በዘላቂ ሰላም ለመቋጨት የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ ያቀረቡት ባለ 20 አንቀጽ ድንጋጌ በተመድ ዕውቅና ማግኜቱ እኔ እግዚአብሄርን አመስግኜበታለሁኝ።   በረከቱም ለራሺያ እና ለዩክሬን፤ ለሱዳን፣ ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ ላለው የአፍሪካ ቀንድ፥ እንዲሁም ለእናት ኢትዮጵያ ይደርስ ዘንድ ምኞቴ ነው። ሥልጣኔን ሥልጣኔ ሊያጠፋው አይገባም። ሰላም ለው ልጆች ሁሉ። ሰላም ለተፈጥሮ።   Sergute©Selassie 18.11.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። -----------------------------------------------------   BBC   https://www.bbc.com/amharic/article...

እንደምን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ዲያሪክተር ዶር ቢኒያም አሥራት #ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ? (ዘገባው የዋዜማ ነው።) ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር ለክብርት ዶር. #መቅደስ ዳባ።

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር ለክብርት ዶር. #መቅደስ ዳባ።    "አቤቱ አምላኬ ሆይ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   አዲስ አበባ።       ክብርት ሆይ!     አሳዛኝ ዜና ሰማሁኝ። መረጃ ያገኜሁበትን ፔጅ ከሥር ለጥፌያለሁኝ። በመከራችን ሁሉ በአንድነት ሊያቆመን የማይችለው በታኝ ጉዳይ ይህን መሰል #የጓጎለ ውሳኔ ነው። እንደምን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ዲያሪክተር ዶር ቢኒያም አሥራት #ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ? በዚህ ወቅት? በዚህ ጊዜ? ሳይለንት ማጆሪቲው ሆድ እንዲብሰው የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ሞጥሮ እየሰራበት ነው።   የጤና ሚር አይደለም ለሰው ልጅ ለኢትዮጵያ ሃኪሟ ሊሆን ይገባዋል፤ በድርጊቱ፤ በሞራሉ፤ በኤቲክሱ አብነታዊ ተግባር መፈጸም ከቻለ። ግን እየተሳነው ነው። አዌርኔሱ ሌላ የአፍሪካ አገሮች ያላገኙት እጅግ ፈጣን ውስጣዊ እርምጃ WHO እንዲያገኝ አድርጎታል። አትኩሮቱ የተቋሙ ልዩ ሥጦታ ነው። ይህን ዕድሉን በክብር ማስቀጠል ሲገባ የኢትዮጵያ ጤና ሚር #ማፍሰስ የእርግማን ነው። አቶ ጎዳና ያዕቆብ የሚሉት ነበራቸው ቢያንስ አስተካክለው ቢሳሳቱ ይሉታል የብልጽግናን እርምጃ። በዚህ ወቅት ህዝብ የሚያስከፋ ተግባር እንደምን ይፈጸማል? ማንን ለማስደሰት? ማንንስ ለመጥቀም???    1) የሰውልጅ ከሰው ሰራሽ #ፖለቲካ በላይ ነው። 2) ተፈጥሯዊነትም #ከዳንቴሉ ፖለቲካ በላይ ነው።   ለዛው ጥሪውም፤ አፈጣጠሩም፤ ተልዕኮውም ለሰብዕዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት ለሆነው የጤና ተቋማት እንዲህ ያለ ያልሰከነ #ትርምስ ፤ #ለመግደፍ መባተል ምን ይባል? እጅግ አዝኛለሁኝ። የተከበሩ የጂንካ ሆስፒታል ዴያሪክተር ሞታቸው ይፈለግ ነበርን? ለምን በህይወት ተረፋ ነው...

ኢትዮጵያ ያላችሁ ወገኖቼ ጥንቃቄ አድርጉ አደራ። ወደ ኢትዮጵያ የምትጓዙም እንዲሁ።

ምስል
  ማህበረ - ቅንነት ደህና እደሩልኝ። አሜን።