#ጭካኔ ከዘር መል ይነሳ ይሆን? መነሻዬ የBBC ዘገባ ነው። ሳክል እኔ ጭካኔ #ፆታ የለውም የሚልም ሃሳብ አነሳለሁኝ።
«በሂትለር ዘረ መል ላይ የተደረገው ጥናት ያስገኘው ውጤት እና የፈጠረው ሙያዊ ውዝግብ» ዝርዝሩ ከሥር ለጥፌወላሁኝ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

#ጭካኔን በሚመለከት ሙሉ 15 ዓመት ሆነኝ ...
1) ጭካኔ ከየት መጣ?
2) ጭካኔ መቼ መጣ?
3) ጭካኔ እንዴት መጣ?
4) ጭካኔን ምን ይገታዋል?
በሚሉ ዙሪያ #ተመድን #የአውሮፓ ህብረትን መፍትሄ ነው ባልኩት ጉዳይ ጽፌላቸዋለሁኝ። እነሱም አክብረው መልስ ሰጥተውኛል። #የአዌርነስ የቃላት ፖስተር የምሠራበት ዩቱብ ቻናሌም ላይ ሠርቸበታለሁኝ። በአትኩሮት ማሰብ ስለሚጠይቅ ለተወሰኑ ዓመታት አልሰራሁበትም። ለመነሻ የሚሆን ሃሳቦች አሉበት። መጪው ትውልድ ሊሠራበት ይችላል።
የጸጋዬ ራዲዮ ከተመሰረተ ከ2008 እአአ ጀምሮም በቅንነት ዙሪያ ሠርቸበታለሁኝ። አሁን ሙሉ ለሙሉ ጭካኔ እና ክፋ ሃሳብን የሚታገል የራዲዮ ጣቢያ ሆኗል የጸጋዬ ራዲዮ። ቲክቶኬ በዚህው ዙሪያ ነው የሚሠራው። ስጀምረውም ለዚህ ዓላማ ነው። በአማርኛ የፖለቲካ ሙግት እምሠራበት ሁለተኛው ዩቱብ ቻናሌም አሁናዊ አቋሙ በዚህ #በፍቅር ተፈጥሮ ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኗል።
#ትንሽ ረፈት የሰጠኝ ቸር ዜና።
ሳይንቲስቶች፤ ተመራማሪወች የጭካኔን ምንጩን ለማጥናት ያደረጉትን ጥናት፤ ሙግታቸው ውስጤን ስላገኜሁበት ነው የBBC ዝርዝር መጣጥፍ የለጠፍኩት። ለእኔ በጣም ኢንተርስቲንግ ጉዳይ የሰው ልጅ ከጭካኔ፦ ከክፋ ሃሳብ፤ ከበቀል፤ ከጦርነት የሚላቀቅበት ዘመን የሰው ልጅ የሚድንበት መንገድ ሁሉ መስመሬ ነው።
በውስጥ ጥላቻን ቋጥሮ ጸሐፊነትም፤ ይሁን ጋዜጠኝነት ስውር ነው። የሆነ ሆኖ ከጥናቱ የተወሰነ ዕይታቸው ልጅ እያለሁ #ጭካኔ ያለበት ሰብዕና አይ ነበር። ያ ሰብዕና የዘረ መል ችግር እንዳለበትም አዳምጥ ነበር። በዚህ ዲያሎግ በዘርፋ የቀረበው የጥናት አቅጣጫ የዘረ መል ህውከት ጭካኔን ሊፈጥር ይችል ይሆን አልኩኝ። ከማውቀው ታሪክ ጋር ስለተገናኘ። ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም አንድ ፋክተር የመሆን አቅሙ ግን ሙሉዑ ነው።
#እኔ የጭካኔ ምንጩን በሦስት መደብ ለይቼ አየዋለሁኝ። እንዲህ ………
2) ስንፈጠር ጸድቀን፤ ተመርቀን፤ ጸድተንም ሲሆን ዓለማችን ያን የሚስቀጥል #ተቋም የላትም። ይህ ሁለተኛው ፋክተር ነው። በእርግጠኝነት። ለዚህም ነው የፍቅር ተፈጥሮ የዕውቀት ዘርፍ ሆኖ፤ በመደበኛ ትምህርት ቤት ይሰጥ፤ ኮሌጅ ይኑረው፤ ዩንቨርስቲ ይኑረው፤ ሚዲያ ይኑረው።፦ ሳይንቲስትም ፈላስፋ ይኖረው የምለው። የምርምር ማዕከልም ይኑረው።
3) የወንጀል መሰረቱ ህግን አለማወቅ ነው። ስለሆነም ህግ የማህበረሰቡ #ዕውቀት ሊሆን ይገባል። ግዴታውን ሳያውቅ ሰው እንደምን ወንጀለኛ ላለመሆን ይችላል??? መብቱን የሚገባውንም እራሱ ከእኔ ጀምሮ ብዙ ሰው አያውቅም። ከህግ ባለሙያወች በስተቀር ህግን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ የሚተረጉም ጽንሰ ሃሳቡን የለም። የህግ ድንጋጌወችን ማንበብ እንጂ መተርጎም አንችልም። ማንበብ የማይችሉ ደግሞ አሉ። ስለዚህ የሁሉም አገር ልጆች የአገራቸውን እና የታህሳስ 10/1948 የሰብአዊ መብት አስከባሪ ድንጋጌወችን ከሥር ጀምሮ ይማሩ ዘንድ ካሪክለም ሊነደፍለት ይገባል ባይ ነኝ። ለሌሎቻችን ደግሞ በሚዲያ ትምህርቱ ሊሰጥ ይገባል።
ኢትዮጵያምም፤ ኢትዮጵኒዝም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የመከራ ቋት #ጭካኔ ነው። ስለሆነም #ጭካኔን ለማስቆም ህሊናን ቧ አድርጎ መክፈት ይገባል። በየትኛውም ሁኔታ የጭካኔ ጭብጦች ላይ የሚሰሩ ጥናቶችን መከታተል ይገባል። ለነገሩ በመልካም ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ቃለ ምልልሶች እንኳን በቂ #አድማጭ የላቸውም። የጭካኔ ዜና ከሆነ ግን አገር ምድሩ ይጥለቀለቃል።
የሆነ ሆኖ ጭካኔን በዚህ ልክ ምርምር ማድረግ ዓለማችን ከፈቀደች ዘንዳ፦ በሥጋ ከተለየው ብቻ ሳይሆን #በጭካኔ #ሪከርድ ከሰበሩ ግን ቁመው ከሚሄዱ በህይወት ካሉትም #ሰብዕናወችም ዘረ መል እየወሰዱ ምርምሩን ቢቀጥሉ ፈቃዴ ነው። ይህ ተብዓትን ብቻ የሚመለከት ሲሆን አንስት ሆኖ ጭካኔ እና ሴቶችስ? ይህ በምርምሩ ላይ እራሴ ያነሳሁት ጥያቄ ነው። በእኛ ታሪክ ዩዲት ጉዲት ጉዳይ ከጭካኔ ጋር ይያዛል።
"የዘር መል አንባገነን ሊሆን እንደማይችል" ሃሳብም ቀርቧል። ከጹሁፋ ሳነብ ያገኜሁት። ሳክልበት ጭካኔ #ፆታ የለውም ባይም ነኝ። ርህርህና በሚጠይቁ ጉዳዮች ሴቶች ዳታ ካበዛን፤ በግፍ የሚፈስ ዕንባን ማበስ ካቃተን ወይንም ዝምታን ከመረጥን። አይዞችሁ ማለትን ካራቅን የጭካኔ ሃሳብን የመጋራት ሊሆን ይችላል።
የሆነ ሆኖ የBBC ሐተታ ከውስጤ ገብቷል። የህይወቴ መስመር ክፋ ሃሳብን፤ ከክፋ ሃሳብ የሚታዘለውን ክፋትን፤ ከክፋት ጋር እቅፍቅፍ የሚለውን ጭካኔ በብዕር መፋለሜ አይቀሬ ነው። የተሟጋቾች ፎቶ እና ጥናት የተደረገበት ዘረ መል የማን እንደሆነ ቢቢሲ ላይ ታገኙታላችሁ። እኔ ከዝች ከምታዮዋት ቁራጭ የተገኜች ጠብታ ናት ምርምር የተደረገባት። እና ቀልቤን ያዝ ያደረገው ፎቶ ይህ ሆነ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/11/2925
/////////////////
#የBBC ዘገባ።
«በአዶልፍ ሂትለር ደም ላይ የተደረገው የዘረ መል (ዲኤንኤ) ትንታኔ ስለ አምባገነኑ የዘር ግንድ እና ሊኖሩ ስለሚችሉ የጤና ሁኔታዎች አንዳንድ ያልተለመዱ ግኝቶች ላይ ደርሷል።»
«የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን የተደረገው አስደናቂ ሳይንሳዊ ሙከራ ሂትለር የአይሁዶች የዘር ግንድ ነበረው የሚለውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ የመራቢያ አካል እድገት የሚጎዳ የዘረመል መታወክ እንደነበረበትም አሳይቷል። ይህን ሁሉ ምርመራ ማድረግ የተቻለው በአንዲት እራፊ ጨርቅ ላይ ፈስሶ ከተገኘው ደም ላይ ከተወሰደ ናሙና ነው።"
"ትኩረት ለመሳብ የሚሞክሩ ዜና ርዕሶች የናዚው አምባገነን በጣም አነስተኛ ብልት እና አንድ የወንድ የዘር ፍሬ ብቻ ነበረው የሚል ላይ ያተኮሩ ቢሆንም፣ የእርሱ ዲኤንኤ "በጣም ከፍተኛ" ውጤት ያሳየበት ከአንድ በመቶ በላይ ለኦቲዝም፣ ለስኪዞፍሪኒያ እና ለባይፖላር ዲስኦርደር ተጋላጭ እንደነበር ያሳያል።» ይህ ማለት እነዚህ የነርቭ በሽታዎች ነበሩት ማለት ነው?»
"በፍጹም አይደለም" ይላሉ ባለሙያዎቹ፤ ይህ የጤና ምርመራ አይደለም። ሆኖም ግን፣ ስለ መገለል እና ጥናቱ ምን ያህል ሥነ ምግባራዊ ነበር የሚል ጥያቄ አስነስቷል፤ ይህም ጥናቱ መደረግ ነበረበት? የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ፕሮፌሰር ቱሪ ኪንግ በቻናል 4 ላይ በቀረበው ዘጋቢ ፊልም ላይ "በውሳኔው በጣም ተጨነቅኩ" ብለዋል።
«የዘረ መል ባለሙያ የሆኑት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከበርካታ ዓመታት በፊት በፕሮጀክቱ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት ወቅት እንደ አዶልፍ ሂትለር ያለ ሰውን ዲኤንኤ በማጥናት ላይ ሊኖረው የሚችለውን አንድምታ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር።»
"እኔ ነገሮችን የማራገብ ፍላጎት የለኝም።" «ነገር ግን በአንድ ወቅት በሆነ ሰው ሊሠራ እንደሚችል ይናገራሉ። እና ቢያንስ በእርሳቸው ክትትል ሥር ጥናቱ የተደረገው ጥብቅ በሆነ መስፈርት፣ በሁሉም "ማስጠንቀቂያዎች እና መከላከያ መንገዶች ተቀምጠው" መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።"
«ፕሮፌሰር ኪንግ ከፍተኛ ስም ላላቸው እና ትኩረትን በቀላሉ ለሚስቡ ፕሮጀክቶች እንግዳ አይደሉም። በአውሮፓውያኑ 2012 በሌስተር የመኪና ማቆሚያ ሥር ተቀብሮ የተገኘው የሪቻርድ ሳልሳዊ አጽም ማንነት ከተረጋገጠ በኋላ የዘረ መል ምርመራውን መርተዋል። ደም ነካው ጨርቅ አሁን 80 ዓመት ሞልቶታል፣ በሂትለር የመሬት ውስጥ መኖሪያ ውስጥ ካለው ሶፋ ተቆርጦ የተወሰደ ነው።»
«ይህ ሶፋ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ የኅብረቱ ኃይሎች ወደ በርሊን ሲቃረቡ ራሱን ያጠፋበት ነው። የአሜሪካ ጦር ኮሎኔል ሮዝዌል ፒ ሮዘንግሬን ከመሬት በታች የተገነባውን ዋሻ ሲፈተሹ ልዩ ወታደራዊ ሽልማት የማግኘት ያህል ስለቆጠሩት ጨርቁን ወሰዱት። አሁን በመስታወት ተደርጎ በአሜሪካ በሚገኘው በጌቲስበርግ የታሪክ ሙዚየም ውስጥ ለዕይታ በቅቷል።»
«ሳይንቲስቶቹ የሂትለር ደም መሆኑን እርግጠኞች ናቸው። ምክንያቱም ከአስር ዓመታት በፊት ከተሰበሰበው የወንድ ዘመድ ከተወሰደውን የ‹ዋይ-ክሮሞዞም› የዲኤንኤ ናሙና ጋር በትክክል ማዛመድ ችለዋል። አሁን በሌሎች ባለሙያዎች እየተደረገ ባለው ግምገማ በእርግጥም አስደናቂ ነው።»
«የሂትለር ዲኤንኤ ሲታወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በአራት ዓመታት ውስጥ ሳይንቲስቶች በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ዘግናኝ አምባገነኖች አንዱ የሆነውን ግለሰብ የዘረመል ስሪት ለማየት ችለዋል። ከአውሮፓውያኑ 1920ዎቹ ጀምሮ ሲሠራጭ እንደ ነበረው መረጃ ሂትለር የአይሁድ የዘር ግንድ ነበረው የሚለው ያልተረጋገጠ ሐሰተኛ ወሬ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።»
«ሌላው ቁልፍ ግኝት ካልማን ሲንድሮም የተባለ በጉርምስና እና በመራቢያ አካላት እድገት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው የዘረ መል መታወክ ነበረበት። ይህ የዘረ መል መታወክ በጣም አነስተኛ የብልት መጠን እንዲኖር እና የዘር ፍሬ ከረጢቱ ባዶ እንዲሆን ወይም ወደ ውስጥ የገባው የዘር ፍሬው እንዳይወርድ ያደርጋል።»
«ይህም በብሪታኒያ ጦር ዘንድ በወቅቱ በሰፊው የሚወራ ነበር። የካልማን ሲንድረም የወሲብ ፍላጎትን ሊጎዳ ይችላል፤ ይህም በተለይ ትኩረት የሚስብ ነው ሲሉ የታሪክ ምሁሩ እና የፖትስዳም ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር አሌክስ ኬይ በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ተናግረዋል።»
"ስለግል ሕይወቱ ብዙ ይነግረናል፤ ወይም በትክክል የግል ሕይወት እንዳልነበረው ያሳየናል" ሲሉ ያስረዳሉ። ሂትለር ሙሉ በሙሉ ሕይወቱን ለምን ለፖለቲካ ሰጠ የሚለው የየታሪክ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ ሲከራከሩበት ኖረዋል።»
"ከምንም በላይ ከማንኛውም ዓይነት የግል ሕይወት ራሱን አግልሎ ኖሯል" እና ይህ ደግሞ ለዚያ ማስረጃ በመሆን ያገለግላል። ባለሙያዎቹ እንደዚህ ዓይነት ግኝቶች ናቸው ማራኪ እና ጠቃሚ የሚያደርጉት ይላሉ። ፕሮፌሰር ኪንግ እንዳሉት "የታሪክ እና የዘረ መል ጋብቻ።"
«በጣም የተወሳሰቡ እና አወዛጋቢ የሆኑ ግኝቶች ሂትለር አንድ ወይም ከዚያ በላይ የነርቭ ወይም የአእምሮ ጤንነት ችግሮች ሊኖሩበት እንደሚችል የሚጠቁሙ ናቸው።»
«የእሱን ዘረ መል እና ሌሎች የተፈጥሮ መረጃ ውጤቶችን በማነፃፀር ሂትለር ለተለያዩ የእድገት ውስንነቶች እና ለአእምሮ ጤና ችግሮች የመጋለጥ ከፍተኛ አዝማሚያ እንደነበረው ደርሰውበታል። ሳይንስ ውስብስብ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው።»
«ፖሊጄኒክ የውጤት መለያ ከአንድ ሰው ዲኤንኤ ጋር ይያያዛል እናም ግለሰቡ ምን ያህል ለበሽታ ሊጋለጥ እንደሚችል ያሰላል። ግለሰቡ እንደ የልብ ሕመም እና የተለመዱ ካንሰሮች የመጋለጥ አዝማሚያ ለማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የእሱን ዲኤንኤ ከብዙ ሰዎች ናሙና ጋር ማወዳደር ይጠይቃል። እና ስለዚህ ግኝቶቹ ወደ ግለሰብ ሲወርዱ በጣም ያነሰ እርግጠኝነት ሊኖራቸው ይችላል።»
«ቢቢሲ በተመለከተው ዘጋቢ ፊልም ላይ ባለሙያዎቹ የዲኤንኤ ትንታኔው የበሽታ ምርመራ ሳይሆን የተጋላጭነት አዝማሚያ አመላካች ነው በማለት ተናግረዋል። ይህም ሂትለር እነዚህ የጤና እክሎች አሉበት ማለት አይደለም።»
«ነገር ግን አንዳንድ የዘረ መል ሳይንቲስቶች ግኝቶቹን ከመጠን በላይ አቅልሎ ማቅረብ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። በለንደን በኪንግስ ኮሌጅ የፎረንሲክ ዘረ መል ፕሮፌሰር የሆኑት ዴኒስ ሲንደርኮምቤ ኮርት "በግምታቸው በጣም ርቀው እንደሄዱ" ይሰማቸዋል።»
«በአውሮፓውያኑ 2018 ተመሳሳይ የደም ናሙና ላይ ምርምር ያደረጉት ፕሮፌሰር ኮርት "በጠባይም ሆነ በባህሪ፣ ያ ምንም ፋይዳ እንደሌለው አስቤ ነበር" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።»
«አንድ ሰው ከውጤቶቹ በመነሳት የተለየ ሁኔታ አለበት በሚል ምንም ዓይነት ትንበያ መስጠት እንደማይፈልጉ በመናገር ምክንያታቸውን ሲያስረዱ "ያልተሟላ የዘረመል ጥናት ነው" ብለዋል።»
«ሌላዋ የዘረመል ሳይንቲስት ዶ/ር ሳንዲያ ራማን ደግሞ በቀላል አነጋገር "በዲኤንኤ ውስጥ የሆነ ነገር ስላለህ ብቻ ትገልፀዋለህ ማለት አይደለም" ይላሉ።»
«በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የኦቲዝም ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሲሞን ባሮን ኮኸን "ከባዮሎጂ ወደ ባህሪ መሄድ ትልቅ እመርታ ነው" ሲሉ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ ተናግረዋል።»
"እንደዚህ ዓይነት የዘረ መል ውጤቶችን በመመልከት የመገለል አደጋ አለ። በተለያዩ የዓለም ክፍል ያሉ ሰዎች ምርመራዬ 'እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ነገሮችን ካደረገ ሰው ጋር የተያያዘ ይሆን?' ብለው ያስቡ ይሆናል።"
«ሌሎች ሊታሰብባቸው የሚገቡ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸውን በመጥቀስ "አደጋው ሁሉንም ነገር ወደ ዘረ መል የሚያውረድ ነው" ብለዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ኦቲስቲክ ማኅበር ምላሽ ለመስጠት ፈጣን የነበረ ሲሆን፣ ግኝቶቹን "ርካሽ ዋጋ" ያላቸው ሲል በይኖታል።»
"የጥናት እና ምርምር ክፍል ረዳት ዳይሬክተር የሆኑት ቲም ኒኮልስ "ከአስደናቂው ሳይንስ የባሰ [በዘጋቢ ፊልሙ] ለኦቲስቲክ ሰዎች ስሜት የታየው ግድየለሽነት በጣም ያስደንግጠናል" ሲሉ ጠንከር ያለ መግለጫ ሰጥተዋል።"
"ቢቢሲ የማኅበሩን ስጋት ዘጋቢ ፊልሙን ለሠራው ቻናል 4 እና ብሊንክ ፊልምስ አቅርቧል። በመግለጫ በሰጡት ምላሽ እንደ ፕሮፌሰር ባሮን-ኮኸን ያሉ ባለሙያዎች "የሰው ልጅ ባህሪ በዘረ መል ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀረጽ መሆኑን ያብራራሉ። ይህም አካባቢ፣ የልጅነት ገጠመኞች፣ አስተዳደግ፣ ለትምህርት ያለው ተጋልጦ እና በዙሪያው ባለው የባህል ተጽዕኖ የተፈጠረ መሆኑን ያስረዳሉ።"
"ፕሮግራሙ አፅንዖት የሚሰጠው በፊልሞቹ ላይ የተገለጹት የዘረ መል ምልከታዎች በሂትለር ላይ ብርሃን እንደሚፈነጥቁ ነው፤ ነገር ግን እሱ በተለየ መንገድ ባህሪ እንዲኖረው በሥነ ሕይወት አስቀድሞ ተወስኖ እንደነበር አይነግሩንም።"
"ሰዎች የዘጋቢ ፊልሙን ርዕስ ገና ሲመለከቱ መጠየቅ ይጀምራሉ። በተለይ ሁለተኛው ክፍል 'ብሉፕሪንት ኦፍ ኤ ዲክታተር' የሚለው ለሁሉም ግርምትን የፈጠረ ነው።"
"ፕሮፌሰር ኪንግ የሚመርጡት ርዕስ አለመሆኑን ሲናገሩ በፊልሙ ላይ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ቶማስ ዌበር ደግሞ "አምባገነን ዘረ መል የለም" ሲሉ በመግለጻቸው ርዕሱ እንዳስገረማቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።"
"ለቢቢሲ ቃለ መጠይቅ ከመስጠታች በፊት ዘጋቢ ፊልሙን ያላዩት ፕሮፌሰሩ የዲኤንኤ ትንታኔውን ትኩረት የሚስብ እና አሳሳቢ ሆኖ አግኝተውታል።"
"አስገራሚ ነው፤ ምክንያቱም በሂትለር ላይ የጠረጠርኳቸውን ብዙ ነገሮችን ስላረጋገጠኝ. . .ነገር ግን ሰዎች 'ክፉውን ዘረመል' ለማግኘት በመሞከር ስለ ዘረ መል ብዙ ማንበብ ይችሉ እንደሆነ ስጋት ነበረኝ።"
"በተለይም በፕሮግራሙ ውስጥ ለተጠቀሱት ኦቲዝም እና ሌሎች የጤና አክሎች ያለባቸው ሰዎች እንዴት እንደሚቀበሉት አሳስቧቸው እንደነበርም ተናግረዋል።"
"ስለ ውስብስብ ሳይንስ ለሠፊው ሕዝብ ትክክለኛ ፕሮግራም ለመሥራት ስትሞክር ብዙ ችግሮች እና ውድቀቶች አሉት።"
"እንደ ሳይንቲስት ኃላፊነታቸውን ከሚዲያ እውነታዎች ጋር በማመጣጠን ብዙ ልምድ ያላቸው ፕሮፌሰር ኪንግ "ቴሌቪዥን ነው - አልፎ አልፎ ቀለል ይላል" ብለዋል።
"እነሱ [ዘጋቢ ፊልሙን የሰሩት] የተለየ መንገድ ወስደዋል እና በጣም ስሜት ቀስቃሽ ሊሆኑ ይችሉ ነበር፤ ነገር ግን አላደረጉም፤ አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮችን ለመያዝ ሞክረዋል. . . እና መከላከያዎ ግንቦችን አስገብተናል።"
ቻናል 4 "ዲኤንኤ የሚለው 'የሕይወት መዝገብ' በመባል ይታወቃል" በማለት ለዝግጅቱ የተሰጠውን ስም ትክክለኛነት አብራርቷል።
በተጨማሪም ኃላፊነቱ "ለሰፊ ታዳሚ የሚደርሱ ፕሮግራሞችን መሥራት እና ውስብስብ ሳይንሳዊ ሀሳቦችን እና ታሪካዊ ምርምሮችን ለሁሉም ተመልካቾች ተደራሽ ማድረግ ነው።"
"በፕሮጀክቱ ሥነ ምግባር ላይ የተነሱ ብዙ ጥያቄዎች አሉ። የሂትለር ዲኤንኤ እርሱ ወይንም ፈቃድ መስጠት የሚችል ቀጥተኛ ዝምድና ያለው ሰው ሳይገኝ መመርመር ነበረበት? እና ይህ በታሪክ ውስጥ ከፈጸመው አስከፊ ጭካኔዎች ለአንዱ ተጠያቂ መሆኑን እንዴት ይገለጻል? ያ የግላዊነት መብቱን ይጥሳል?"
"ይህ ሂትለር ነው፤ እሱ ማንም ሰው የዲኤንኤ ምርምር ሊያደርግበት የማይችል አንድ ተዓምራዊ ገጸ ባህሪ አይደለም። ይህን ውሳኔ የሚያደርገው ማን ነው?" በማለት ፕሮፌሰር ኪንግ ይከራከራሉ። የታሪክ ምሁሩ ሱብሃድራ ዳስ በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ።"
"ሳይንቲስቶች የሚያደርጉት ይህ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሞቱ ረዥም ጊዜ የሆናቸው ሰዎች ዲኤንኤያቸው የተወሰዱ ሰዎች አሉ። በሳይንስ እና በአርኪኦሎጂ ውስጥ ይህ የተለመደ ተግባር ነው፤ ችግር የሚጀምረው እንዴት እናነበዋለን የሚለው ላይ ነው።"
"የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ኬይ "እውነታው እስካለ ድረስ እና ሁሉም ነገር በሚገባ መረጋገጡን እስካረጋገጥን ድረስ" ሥነ ምግባር እንደማያስባቸው ተናግረዋል።"
"እና የሂትለር ዲኤንኤ መነካት ነበረበት ወይ ለሚለው "ሂትለር ለ80 ዓመታት ሞቷል። ቀጥተኛ ዘሮች የሉትም፤ ልጅም አልነበረውም። ላልተነገረ ስቃይ ተጠያቂ ነው፤ ያንን ዲኤንኤውን ከመተንተን የሥነ ምግባር መርሆዎች ጋር መመዘን አለብን።"
"የሚገርመው በአውሮፓ ውስጥ ያሉ በርካታ ቤተ ሙከራዎች የፕሮጀክቱ አካል መሆን አልፈለጉም። እና ሙከራውን ያደረገው በአሜሪካ የሚገኝ ተቋም ነው።"
"ዘጋቢ ፊልሙን የሠሩት ድርጅቶች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥናቱ "ለአካዳሚክ ሥራ አስፈላጊ የሆነውን መደበኛ የሥነ ምግባር ግምገማ ሂደት አልፏል" ይህም በሁለት አገራት የተደረጉ ግምገማዎችን ያካትታል።"
"ታዲያ ይህ ጥናት መካሄድ ነበረበት? ቢቢሲ የተለያዩ የዘረመል ሳይንቲስቶችን እና የታሪክ ተመራማሪዎችን አነጋግሯል። እና መልሱ ጥያቄውን በሚያነሳው አካል ላይ እንደሚወሰን ምላሽ አግኝቷል።"
"በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ያሉት ያለማወላወል አዎ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሂትለርን ማንነት ያለማወላወል ለማሳየት ይረዳል፤ እርሱ የሚያስፈራም የሚያስደንቅም ሰው ነው ይላሉ።"
"ያለፈውን ጽንፍ ለመረዳት የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን" ሲሉ ፕሮፌሰር ዌበር ያምናሉ።"
"ዶ/ር ኬይ "እውነት እንነጋገር ከተባለ፣ እነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ቀደም ብለው እዚያ ነበሩ… ይህንን ሀሳብ በድንገት በሰዎች አእምሮ ውስጥ አልተከልነውም። ሰዎች ሂትለር አንዳንድ ችግሮች ነበሩት ብለው ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሲገምቱ ቆይተዋል።"
"ሁሉም የታሪክ ምሁራን ግን በዚህ አይስማሙም። በዩትሬች ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ታሪክ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ኢቫ ቩኩሲች "የሂትለርን ድርጊት ያነሳሳውን ለማብራራት መሞከር በጣም አጠራጣሪ መንገድ ይመስለኛል" ብለዋል።"
"በጅምላ ግጭቶች ላይ ምርምሮቻቸውን የሠሩት ዶ/ር ቩኩሲች ሰዎች ለምን ፍላጎት እንደሚያድርባቸው መረዳት እንደሚችሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን "የምንፈልገው የትኛውም መልስ በዲኤንኤ ምርመራ አይገኝም" ብለዋል።"
"እና ጥናቱ አስደሳች ቢሆንም፣ የታሪክን እውነተኛ ትምህርቶችን የመደበቅ አደጋን ይፈጥራል ሲሉ በአምስተርዳም የኤንአይዲ ኢንስቲትዩት የታሪክ ምሁር የሆኑት አን ቫን ሞሪክ ይናገራሉ።"
"ያ ትምህርት "በተወሰኑ አውዶች ውስጥ ያሉ መደበኛ ሰዎች ዘግናኝ ጥቃት ሊፈጽሙ፣ ሊያነሳሱ ወይም ሊቀበሉ ይችላሉ" የሚል ነው። በሂትለር አነስተኛ የብልት መጠን ላይ ማተኮር፣ የጅምላ ጥቃት እና የዘር ማጥፋት እንዴት እንደሚፈጸም እና ለምን እንደሚከሰት ምንም አያስተምረንም ብለዋል።"
"ጥናቱ ሲጠናቀቅ እና በሌሎች ባለሙያዎች ግምገማ እየተደረገበት፣ የሆነ ጊዜ ሙሉ ግኝቶቹ ይፋ ይደረጋሉ። ፕሮፌሰር ዌበር "በጣም በጥንቃቄ እና በስክነት" ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው ይላሉ። ነገር ግን በሆነ መንገድ ጠቃሚ እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋሉ።"
"የምርምር ውጤቶች ጥሩ ጎናቸው እርሱ ነው። በአምስት፣150፣ 500 ዓመታት ውስጥ ሊከሰት ይችላል። ይህ ምርምር ለትውልድ የሚያገለግል ነው፤ እናም ለወደፊቱ ብልህ ሰዎች እንደሚጠቀሙባቸው እርግጠኛ ነኝ።"
"ግን እነዚህን ውጤቶች እንዴት እንደምንጠቀም ሁላችንም ኃላፊነት አለብን። ዶክተር ኬይ ሁሉም ሰው "ሳይንስን መከተል" እና የምናውቀውን እና የማናውቀውን ግልጽ ማድረግ አለበት ይላሉ። ይህ ደግሞ መገናኛ ብዙኃን እንዴት እንደሚዘግቡት ያካትታል።"
"ይህን ዘጋቢ ፊልም የሚመለከት ማንኛውም ሰው ለመገለል አስተዋፅኦ አለማድረጉን ለማረጋገጥ በትክክል የመፃፍ ኃላፊነት አለበት። እንዲህ ያለ ዘጋቢ ፊልም ዝም ብሎ ከባዶ ተነስቶ አይሠራም።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ