ልጥፎች

ከኤፕሪል 15, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አንተ ሞት የማትለመድ ጉት። ሥጦታው ለግራባው ብአዴን እና ለጌታው ለኦነጉ ኦህዴድ ይሁንልኝ። 15.04.2021

ምስል

አንተ ሞት የማትለመድ ጉት ሥጦታ ለግርባው ብአዴን።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሃሙስ ማዕዶተ አሰጋሪው በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·        አ ፍታ። ነፃጫጭ ባዘቶዎች ከሰማይ ወደ ምደር እዬወረዱ ለአፍታ ቆዩ። ሚያዚያን ሲዊዞች አንደልቡ ይሉታል። እንፈለገው የሚሆን ይሉታልም። ባይበዛም ብናኝ የባዘቶ ጥጥች አሉ። ትናንት ይብርድ ነበር። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ቅልጥ ያለ ጠሐይ ሊወጣ ይችላል። ሚዚያ የፈለገውን የሚያደርግ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳም የዶር ዳኛቸው አሰፋ የስለት ልጅ ልክ እንደ ወርሃ ሚዚያ ባህሬ ናቸው። እንደ ልቡ። ቅኖቹ እንዴት አደራችሁ? እናት ኢትዮጵያስ እንደምን እዬሆነች ነው? ዛሬ አባወራው አሰጋሪው ሃሙስ ነው። ማዕዶተ አሰጋሪው የቅኔው ልዑል የብላቴ ጸጋዬ ዕለት። የዛሬው የራዲዮ ዝግጅቴ በሞት ላይ ነው። ሞት እንዲኖር እንዲመራ፤ እንዲገዛ፤ እንዲያስተዳደር ተፈቅዶለታል ኢትዮጵያ ላይ። የሞተው ሰውኛው ሞራል፤ ተስፋ፤ ራዕይ፤ ቅርስ ውርስ፤ ተፈጥሮ፤ ማስብም ሳይቀር ነው። ሙት መሬት ላይ ስላለወ ግርባው ብአዴን ዛሬ ምን ይል ይሆን የጸጋዬ ራዲዮ? አብራችሁት ትሆኑ ዘንድ በትሁት አክብሩት ይጠይቃችኋል። Realaudio – Player ግን  ይጠይቃል በራዲዮ ሎራ ዕልፍኝ የጸጋዬን መንፈስ አርኬብ ላይ ቀጥሎ ለማድመጥ። በራሴ ዩቱብ ቻናልም እንዲሁ ከሥርጭቱ በኋላ እለጥፈዋለሁኝ። በቴሌግራም ፔጄ ላይም እንዲሁ። ላይፍ ላይ ሰዓቱ ሲደርስ ከ10 ደቂቃ ቀደም ብዬ ሼር አደርጋለሁኝ።   ·        ም ርኩዝ። https://www.lora.ch/sendungen/alle-sendunge