አንተ ሞት የማትለመድ ጉት ሥጦታ ለግርባው ብአዴን።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።
ዕለተ ሃሙስ ማዕዶተ አሰጋሪው
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)
· አፍታ።
ነፃጫጭ ባዘቶዎች ከሰማይ ወደ ምደር እዬወረዱ ለአፍታ ቆዩ። ሚያዚያን ሲዊዞች አንደልቡ ይሉታል።
እንፈለገው የሚሆን ይሉታልም። ባይበዛም ብናኝ የባዘቶ ጥጥች አሉ። ትናንት ይብርድ ነበር። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ቅልጥ ያለ ጠሐይ
ሊወጣ ይችላል። ሚዚያ የፈለገውን የሚያደርግ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳም የዶር ዳኛቸው አሰፋ የስለት ልጅ ልክ እንደ ወርሃ ሚዚያ
ባህሬ ናቸው። እንደ ልቡ።
ቅኖቹ እንዴት አደራችሁ?
እናት ኢትዮጵያስ እንደምን እዬሆነች ነው?
ዛሬ አባወራው አሰጋሪው ሃሙስ ነው። ማዕዶተ አሰጋሪው የቅኔው ልዑል የብላቴ ጸጋዬ ዕለት። የዛሬው
የራዲዮ ዝግጅቴ በሞት ላይ ነው። ሞት እንዲኖር እንዲመራ፤ እንዲገዛ፤ እንዲያስተዳደር ተፈቅዶለታል ኢትዮጵያ ላይ። የሞተው ሰውኛው
ሞራል፤ ተስፋ፤ ራዕይ፤ ቅርስ ውርስ፤ ተፈጥሮ፤ ማስብም ሳይቀር ነው። ሙት መሬት ላይ ስላለወ ግርባው ብአዴን ዛሬ ምን ይል ይሆን
የጸጋዬ ራዲዮ? አብራችሁት ትሆኑ ዘንድ በትሁት አክብሩት ይጠይቃችኋል።
Realaudio – Player ግን ይጠይቃል በራዲዮ ሎራ ዕልፍኝ የጸጋዬን መንፈስ አርኬብ ላይ ቀጥሎ ለማድመጥ።
በራሴ ዩቱብ ቻናልም እንዲሁ ከሥርጭቱ በኋላ እለጥፈዋለሁኝ። በቴሌግራም ፔጄ ላይም እንዲሁ። ላይፍ ላይ ሰዓቱ ሲደርስ ከ10 ደቂቃ
ቀደም ብዬ ሼር አደርጋለሁኝ።
· ምርኩዝ።
https://www.lora.ch/sendungen/alle-sendungen?list=Tsegaye
https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg?view_as=subscriber
Sergute
Selassie ሥርጉተ ሥላሴ
· ደመመን የተጫናቸው ዕለታት፤ ዘመን፤ ወራት፤ ወቅታት በኢትዮጵያ።
እኔ የመጋቢት 1 ቀን የሰማይ ታምር የአውሮፕላን አደጋ ሲከሰት በኢትዮጵያ ዶር ለማ መገርሳ
እና ዶር አብይ አህመድ ትቢያ ነስንሰው ሱባኤ ይገቡ ዘንድ በትህትና አሳስቤ ነበር። ያን ዕለት ነበር ባልደራስ ለኢትዮጵያም የተመሰረተው።
ያ የሰማይ መልዕክት ቀላል አልነበረም። ታስታውሱ እንደሆን ዶር አብይ በተመረጡበት ሌሊትም በመቀሌ አቅርቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ
ተከስቶ ነበር። እኔ ያነንም እንደ ወረደ አልተቀበልኩትም ነበር ሰማይ ሊነግረን የፈለገው ነገር እንዳለ ጽፌበት ነበር። በሌላ በኩል
በጉራጌ ዞንም ሦስት ከባባድ ክስተቶች ተከስተው ነበር።
(1)
ተሰምቶ የማያውቅ
ኃይለኛ የሰማይ ድምጽ፤
(2)
መሬትን ከሁለት
የሰነጠቀ የመሬት መንቀጥቀጥ፤
(3)
እና ታይቶ
የማይታወቅ ዶፍ። ይህ ሁሉ ዘመኑን ያነበበ የሰማይ ታምር ነበር። አድማጭ ግን አላገኜም። የ ዕድምታ ባለሙያም የተሰጠው አላገኜም።
በወቅቱ መልዕክቱን እዬተከታተልኩ በከበቡሽ ብሎግ አቀርቤዋለሁኝ። መከራችን ተጀመረ ልል አልችልም
ዛሬም። የኢትዮጵያ ቀንም ተጸነሰ ማለት አልችልም። ሞት ውስጥ ነው ያለነው። የሞት በሮች የተከፈቱት በሰኔ 16/2010/ በሀምሌ
19/ ነበር። አቅማችን መዳፋችን ባዶ ነው። መዳፋችን ቀርቶበት የሂደት አትኩሮታችንም የሃሳብ ልቅ ሲመዘን ያሳስባል። የለንም።
በዕለታዊ ብቻ ነው አቅም ሲፈስ ሲተንም እማዬው።
በሳል ሊቃናት ከሞት ላይ ተቀምጠው እንኳን ምን እናድርግ የሚለውን እንደ እኔ እንደ ማህይሟ
አጀንዳቸው ሊሆን አልቻለም። ይህ ሃሳብ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስን፤ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትን፤ አቶ ልደቱ አያሌውን፤ አቶ እስክንድር
ነጋን አይመለከተም። እነሱ የቀደመ ሃሳብ አቅርበዋልና። አብሶ አቶ ልደቱ አያሌው ከእነ መፍትሄው ነበር ዝርዝር የመዳን ስጦታ ያቀረቡት።
አንድ ቀን፤ አዎን አንድ ቀን ልደቱ የሚል ትውልድ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁኝ። እኛ እናልፋለን ግን የመፍትሄ አሻራቸው አንድ ቀን
ገናና ሆኖ ይወጣል። እሳቸውን ከመፎካከር ሃሳባቸውን መቀበል ውስጥ ማድረግ ብልህነት ነበር።
· ተስፋ ሲያምጥ።
እምትደክሙበት ነገር ተስፋ የሚበላ ከሆነ ድካሙን ማጠሞን ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። ከ100 የጥገና
ለውጥ የተስፋ ጉጉት ቀናት ውጪ ያሉ ማዕልቶች የኢትዮጵያን ክፉ ቀን አማጮች ነበሩ። እያንዳንዱ ክስተት ለሌለው ውድቀት ነበር።
እያንዳንዱ ኦፕሬሽን የቀጣዩ ዕለታት የሞት አዋጅ ነበር። ሦስት ሰኔዎች፤ ሶስት ጥቅምቶች፤ 11/11 ጨምሮ የሞት ኦፕሬሽኖች ነበሩ።
ይህም ሆኖ ግርባው ብአዴን እንዳይነካብን የሚሉ ሰፊ ድምጽ ያላቸው ነፍሶችም ነበሩ። ተስፋ የጣሉበት።
ኢትዮጵያን ይታደጋል በሚል። ተስፋ ጎዳና ነው። ግን ጎዳናው ማህንዲስም ምህንድስናም ይሻል። ማህንዲስም ምህንድስና ሳይኖር ተስፋ
ሊኖር እንደምን እንደሚቻል ይገርመኛል።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ያው በአማራ ትክሻ ሁሉም ፍላጎት ይከወናል የሚል ተደሞ ጉልህ ነው።
ተስፋ ማድረግ ባይከፋም ተስፋ የተደረገበት ህዝብ እዬአለቀ፤ እየተሳደደ በውጭ አገር መንግሥታትም እንኳን አንድ ድምጹን የሚሰማ
አካል ሳይሆን ብቻውን እዬተፋለመ ያለ የአማራ ህዝብ ወዘተረፈውን የኢትዮጵያ ችግር ይሸከም ተብሎ ብዬን ገመድልነት ነበር። ልክ
የአማራ ታገድሎ ሲነሳ „የነፃነት ሃይል“ ተብሎ ተዘርፎም እንደገናም ኃላፊነት ተወጣ። ? ? ? አማራ የራሱ ጉዳይ አጀንዳው ሆኖ
አያውቅም። ወደፊትም ይሆናል ብዬ አላስብም። አቅሙን ይገብራል ለሞቱ ያስርክባል። በተለያዬ ቨርዥን። ማጎዶነት ግን ይፈቀዳል።
ይህን በተለያዬ ጊዜ በትህትና አሳስቤ ነበር። ሚዲያ ላይ መገኜቱ ባይከፋም መሬት ላይ ሥራ መስራቱ
ይበጅ ነበር። ጭራሽ ተበዳዩ ህዝብ በዳይ ሆኖ በዓለም አደባባይ ሲከሰስ፤ ሲወነጀል፤ ሲወገዝ ምን ያህል እኛ ምንም እንደሆን ያሳዬናል።
እያዬን ነው የተጋሩ ልባሞች ዓለምን እንደምን ሪቦሊሽን እያካሄዱበት እንደሆነ። ተጋሩ ግሎባል አብዮት ነው ያካሄዱት። ይህ አይካድም።
እነሱ ብልህነታቸው ፍላጎታቸውን አይቀላቅሉትም ከሌላ አጀንዳ ጋር አይይጡትም። ጥርት ያለ አቋም፤
ጥርት ያለ ዓላማ እና ግብ አላቸው። ብቅ ሲሉ ጠላፊ ከግራ ከቀኝ ሳይመጣ ቀርቶ፤ አማላጅ ሳይላክባቸው ቀርቶ አይደለም። ሁልጊዜ
እንደምለው የቀደመው የግንቦት 7 የሥ/አ/ኮሜት እንዳለ ነው ያለው ውጭ አገር። ኢዜማ ቅርፊት ነው ለግንቦት 7። ኢህዴግ ቅርፊት
ነው ለህወሃት፤ „ብልጽግና“ ቅርፊት ነው ለኦነጋዊው ኦህዴድ።
ግንቦት 7 የተለመደውን ተግባሩን በተረጋጋ መንፈስ እዬከወነ ነው። ስለ አማራ የሚቆረቆሩትን
በቪዥን ኢትዮጵያ በለው በምንም ጠለፍ ያደርግ እና በራሱ ማዕቀፍ ውስጥ ያስገባቸዋል። ጥረቱ ሁሉ ለግብ የማይበቃው ለዚህ ነው።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዓለም ፊቱን ቢያዞርብን የት እንገባለን ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር። ለማከብራቸውም ሊቃናት የሃሳብ አቅጣጫውን ሁሉ
ኮልሜ ልኬያለሁኝ። ምክንያቱም ብቻችን ልንወጣው አልንችልምና። የዓለም ህዝብ ሊያግዘን ይገባ ነበር። አልሆነም። መቅደም ያተርፋል።
ገዢ መሬትንም መቆጣጠር ያስችላል።
የሆነው እዬሆነ ያለውም ያ ነው። መገለል። አንድ ቅንጣት አመክንዮ የማንቅያ ደወል ነበር። ዛሬ
ስለ ሱዳን በጥቂቱ ይገለፃል። በተገባው ልክ ትኩረት ተሰጥቶታል ባልልም። ያው ማንኛውም አቅም አለኝ የሚል አማራን መሬቱንም፤ ርስቱንም
ህዝቡንም ከቀማ ፌድራሉ አይመለከተውም። አማራ የሚፈለገው ለማገዶነት እና ለሸክም፤ ዝክንትሉን ገመና ለመጫን ብቻ ነው።
የሰሞኑ „በሱዳን ተወረርን“ እኔ እንደማስበው ምርጫውን የማራዘሚያ ዋዜማ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ።
የማዛያም። 50% የምርጫ ዝግጅት ብቻ ነው ያለኝ ሲል የገዳ ምርጫ ቦርድ አሁን አሁን እኔ እንደማዬው አገር ውስጥ አስዳደር የቀለጤዋ
የሚኒስተሯ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ መረጃም ተደምጧል። ይቀጥላል የጤና ሚኒስተር … ይቀጥላል „የሰላም“ ሚኒስተር ኦ! የሰላም ከምለው
የቀውስ ሚኒስተር። ገዳ እና ሰላም? በማስገብር፤ በመግደል፤ በመደርመስ፤ በማቃጣል … ሰላም? ቢያንስ ስለምን ይሆን የተደራጀን
ነገር የሚያውድመው ገዳ? ለነገሩ ግንቦት 7 የበቀለ ማዬት በሽታው ነው። እሱም እኮ አንድ ኦርጅናሉ ገዳ ነው።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ በሰኔ 16/2011 የአማራ ሊሂቃን ርሸና፤ የአማራ ልዩ ሃይል ርሸና
ጊዜ እርዳታ ከጎረቤት አገር ተጠይቀን ነበር ተብሎ ተነግሮናል። እኛ እንቋቋመዋለን ብለን ነው እንጂ ሲሉ ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር
አብይ አህመድ ነግረውናል። አስቀድመው የግንቦት 7 ቁንጮ እና ዛሬ የተነኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ግንቦት ወር ላይ ወደ ዲሲ ተልከው
ነበር። ጠቅላዩም አቶ ንግሡም በቢኦኤ የአማርኛው ክፍለ ጊዜ ቃለ
ምልልስ ነበራቸው። እኔ በዩቱብ ቻናሌ በስፋት ሰርቸበታለሁኝ።
ለሰኔው የአማራ ክልል ኦፕሬሽን ጉዝጓዝ ለመስራት ነበር የ ኦህዴድ እና የግንቦት 7 የወልዮሽ
ጉዞ የነበረው። ሰኔ ላይ ያ ግፍ ሲፈጸም አቶ ገዱ ወደ ጀርመን አቶ ደመቀ ወደ ዲሲ አቅንተውም ነበር። ለአንባሳደር ኸርማን ኮኽንም
የአማራ ጽንፈኛ ዳግም ሊገዛ ሞክሮ ከሸፈ የሚል መረጃ ተሰጥቶ ምን ያህል ፖለቲካዊ ትርፍ በግንቦት7ወኦህዴድ እንደተገኜበት ይታወቃል።
ያን ጊዜ የአማራ ሊቃናት ለሽታ ላይ ነበሩ።
ያ ታላቅ ደወል ነበር። የአማራ ሊቃናት ግን ማን ገዳይ፤ ማን አስገዳይ ሆነ በሚል በብጄ አሳምነው
ጽጌ እና በዶር አንባቸው መኮነን ሁለት ረድፍ ተከፍሎ ቦክሱ ቀጠለ። ያን ጊዜ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ይጠይቅ ነበር። ልክ ዛሬ ልባም
የተጋሩ ልጆች እንዲሚያደርጉት ሁሉ። እኔ አይጸጽተኝም። የምችለውን ያህል ሞክሬያለሁኝ። መረጃውም ከእጄ አለ። ያን ጊዜ ነው እኔ
የአማራ ጆኖሳይድ በይፋ ተጀመረ ብዬ ነበር የጻፍኩት።
አቅም አልግባብ ፈሰሰ - ለግደሉኝ። ውጭም ያለው አቅም ደነዘዘ። ፈዘዘ። የዛሬው የጸጋዬ ራዲዮ
መሰናዶዬ „አንተ ሞት የማትለመድ ጉት“ የሚል ሥነ - ግጥም ይሆናል። ከ10 ዓመት በፊት በተፃፈው የአዋቂወች የተስፋ የግጥም መድብል
ለህትምት ከበቃው መጸሐፌ ውስጥ ከገጽ 100 እስከ 108 በተለያዬ ቀናት የተጻፈው ግጥሜን ከግርባው ብአዴን የወቅቱ ፕሬዚዳንት
መገለባበጥ ከማይሰለቻቸው አቶ አገኜሁ ተሻገር እና እና ከቲማቸው ጋር እያንዳንዱ ስንኝ በውል የውስጥ ሆድ ዕቃቸውን ስለገለጸልኝ
ይቀርባል። ሰው አንጎል ብቻ ከኖረው እንዲህም አለና።
ግርባው ብአዴን ኢትዮጵያን በማፍረስ በማስፈረስ፤ አማራን በመጨፍጨፍ እና በማስጨፍጨፍ እራሱ
በሰጠው ድምጽ፤ ራሱ ለገዳ ኢንፓዬር፤ ለፕሮቴስታንት ኢንፓዬር በሚሰጠው ሙሉ ድጋፍ መቃብር ናፋቂ ከንቱ ድርጅት ነው። ለዬነታዋ የተዋህዶ ሰቆቃም ተጠያቂው ግርባው ብአዴን ነው።
ለአዲስ አበባ ሽኝትም።
ግርባው ብአዴን „ጭምት“ ሳይሆን ጨፍጫፊ አስጨፍጫፊ እርቃን ድርጅት ነው። የቅራኔ አያያዝ፤
የተቃርኖ አመክንዮ አደረጃጀት ፈጽሞ የማያውቅ ዕድሜው ግዙፍ ግን እጭ ላይ ያለ ጮርቃ፤ ከዝለቱ የማይማር፤ ግርድ እና ግርድና የማይሰለቸው
ድርጅት ነው። ሰው ሞትን እንደምን ደግፎ ይፎክራል? እንዴትስ ያቅራራል? እራሱ እኮ ቀኑን የሚጠበቅ ድርጅት ነው። ቀኑ ሲደርስ
የኦህዴድ ገዳ እዬለቀመ ልኩን ያስታጥቀዋል። ግንቦት 7 የሚጠበቀው ይህንኑ ነው።
በገዳ ወረራ፤ በገዳ መስፋፋት፤ በገዳ አስምሊሽን፤ በጋዳ ዲስክርምኔሽን የሚተርፍ እንድም ኢትዮጵያዊ
ተወላጅ፤ ቅርስ፤ ትሩፋት፤ ሃይማኖት፤ የተፈጥሮ ኃብት የለም። ገዳ እፉኝት ነው። ሲረገዝ አባቱን፤ ሲወለድ እናቱን የሚገድል። እዬገደለ
የሚራባ። ለራሱ ለኦሮሞ ህዝብ በተለይ ለተዋህዶ፤ ለክርስትና እምነትም፤
ለኢትዮጵያዊው እስልምናም የመቃብር ሥፍራ ነው። „የገዳ ብልጽግና ተዋህዶን፤ እስልምናን ካቶልክን“ እንደሚያከስም በሰነዱ ጽፎታል።
በግልጥ ነው እዬሠራ የሚገኜው።
ለዚህ ነው ደፋሩ የዕውነት ዓራት ዓይናማ ሊቀ - ሊቃውንት የኔታ ጎዳና ያዕቆብ ፊት ለፊት እስከ
ቤተሰባቸው ወጥተው „አትግደሉን!“ ሲሉ በይፋ በአደባባይ በተግባር የሰውነታቸውን ልቅና በልዕልና ያወጁት። „እኔን አይወክለኝም
ይህ ጭካኔ፤ ለጭካኔ ትውፊቴን ቢሆን አክብሮ የሰውን ልጅ መነሳት አርስዎ ለማለት አልችልም ገዳይን ጨፍጫፊን“ ሲሉ በሚመሰጥ አኳሆን
በተከታታይ በዬቀረቡበት ሚዲያ የገለጹት።
ይቅርታም ጠይቀዋል። እሳቸው ገና ያልተገለጡ፤ ያልተነበቡ የተከደነ ሲሳያችን ስጦታችን ናቸው።
አዲስ ምዕራፍ። ብሩህ ክስተት። ምስባክም ናቸው። እራሱን ያሸነፈ ነው ለእኔ ጀግና። አዎን እኒህ ሰው ፈጣሪ ይጨርስላቸው እንጂ
እራሳቸውን ያሸነፉ ጀግና ናቸው። አርቲፊሻል ያልሆኑ የትውልድ አብነት። „ይቅርታ“ ሲሉ እኔ ቃሉን ስሰማ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም።
እኔ አልችልም ሆደ ባሻ ነኝ። ኢትዮጵያም ታሳዝነኛለች።
https://www.youtube.com/watch?v=_xXeyMiNeWo
“ሰዎቹ” ወደ ግባቸው እየተምዘገዘጉ ነው . . . “የዘጠኝ ወር ድርስ ነፍሰ ጡሯን ሆዷን በሳንጃ ሸልቅቆ አውጥቶ ልጁን እንች አላት”
13,848 views
•Streamed live on Apr 13, 2021
1.2K29SHARESAVE
Apr 13, 2021 የጽዋ
ዝግጅት „የወል የሃዘን ቀን“ ነበር ልበለው። ሙሉውን ለማዳመጥ አቅም ባይኖረኝም። እያቆራረጥኩ በሰማሁት ሁኔታ ግን ያ መሰናዶው
„የትውልድ“ ብለው ይሻለኛል። ትውልድ እሚድነው በዚህ መልክ ነው። በዛ በጨለማ ዘመን የህወሃት የፈንድሼ ፌስታ የከበሮ ዘመን የቆረጡ
የተጋሩ ልጆች እንደዛ በጥዋቱ እንደ አቶ ጎዳና ያቆብ ደፈር ብለው ወጥተው ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል መጨካከን ባልኖረ ነበር። አልነበሩም
እያልኩ አይደለም። ሁለት ፍሬ ነበሩ። ጋዜጠኛ አብርኃም በላይ እና አቶ ገብረምድህን አርያ።
ግን ጉልበታም ንቅናቄ አልፈጠሩበትም። አቶ ጎዳና ግን አዲስ ብሄራዊ፤ ሉላዊ የሰውነት ማህበራዊ
አብዮት ላይ ናቸው። መሪነት በዚህ መልክ ሲፈልቅ፤ መማር በዚህ ልክ በልዕልና ሲልቅ ትውልድ መጽናናትን ያገኛል። እንደ እኔ ሙሉ
ዕድሜውን ወጣትነቱን ለገበረ ደፍሮ ለተማገደ ደግሞ ተስፋ ይሆናል። ብቻ ይጨርስላቸው።
የተመሰከረለት ሁሉ የተማገድኩለት ሁሉ በቦታው ስለሌለ ነው ይጨርስላቸው እምለው ደጋግሜ። እኔ
ቅን ስለሆንኩኝ በዕለተ አንድ ጀምሮ በንጹህ ልቤ ነው የተቀበለው አወንታዊ መንፈሳቸውን። በተመስጦ፤ በተደሞ ነውም እምከታተለው
እሳቸው የሚገኙበትን ውይይት ሁሉ። እኔ የታከትኩበት ለድምጽ አልባ የኢትዮጵያ እናቶች ድምጽ በመሆን፤ በትውልዱ ጉዳይ ነውና።
· ተጠፋፋን።
እማንተዋወቅ ሁነናል። የጭካኔ ድምጽ ያስቀናናል። ልናፍርበት ሲገባን። በሚሆነው ነገር ሁሉ አብረን
ማፈር ይገባናል። አልሠራነም። አቅምን ማኔጅ የሚያደርግ ቀናነት አይቼ አላውቅም። ምድረ በዳነት ብቻ።
https://www.youtube.com/watch?v=c7-A3WwOAKQ
•Jul 25, 2020
አሁን እኮ ያለው ነገር በሰውነት ልክ ስታዩ ከእኛ ቀድመው ያለፉትን ጊዜ ያስናፍቃል። መጻፍ
እያቃተኝ ነው እኔ። ተጠፋፋን። እዬጠፋንም ነው ያለነው። አንዱ ለሌላው ማዘን የለም። ሁሉም በዬራሱ ጎጆ ነው ያለው። 12 አካለታችን
ሳይቀር በክልል አካተነዋል። ልብ /// ኩላሊት /// አንጀት
/// ጉበት /// ጨጓራ /// ዓይን /// ጆሮ /// ህሊና ለምን ቢባል ሊያስፈርድም አይገባም። በደሉ ከረፋና።
የዛሬን ብቻ ሳይሆን ከ30 ዓመት በፊት ያለው፤ የነበረው ግፍ ማንሳት አይፈቀድም። ስለ አዲስ
አበባ ያለችበት ሁናቴ የሚያንገበግባው ስለ ወልቃይት፤ ጠገዴ ራያ አይመለከተውም። ስለ ማይካድራ፤ ስለ ስሜን እዝ ላይ አማራ ተነጥሎ
መጨፍጨፍ አይመለከተውም፤ መተከልን ኦሮምያን ሲያነሳ ትግራይ ላይ ያው የኖረው ጭፍጨፋ እና ሰቆቃ የትናንቱ ይዘለላል። ይህ ያሳዝነኛል።
በወልቃይት በጠገዴ ልጆች የሚጠሩት በእናታቸው ነው። እኔ ከ10 ዓመት በፊት በጻፍኳቸው የግጥም
መድብሎቼ መታሰቢያነቱ ለእናነኛ ማንም ላልነበረላቸው እህቶቼ፤ እናቴቼ መታሰቢያ ጽፌያለሁኝ። የትዳር አጋራቸው ከፊታቸው ተገድለው፤
ተሰውረው ሚስቶች ይደፈራሉ። ቁጥር ስፍር የለውም ግፉ። አገዳደሉ ጉድጓድ ውስጥ በጢስ ነበር። እኔ በስማ በለው አይደለም የምሰማው
የቤተሰቦቼ መኖር ያ ስለነበር ነው እምጽፈው። በፈረንጆች አቆጣጠር 2013 ዋ! ዬወልቃይት እና የጠገዴ ህዝብ ከተነሳ ብዬ ሁሉ
ጽፌ ደጉ ዘሃበሻ አትሞልኝ ነበር።
ኢትዮጵያዊነት ይህንንም ፈተና ማለፍ አለበት። የትግራይ ኢትዮጵያዊ አዛውንታት ዕውነቱን የተናገሩትም
አብሮ ባዶ 6 በልቷቸዋል። ዛሬም በትግራይ ውስጥ የኤርትራ ሠራዊት በወልቃይት በጠገዴ እናቶች እህቶች ህወሃት ሲፈጽመው የነበረውን
ግፍ ይህንኑ በተጋሩ እህቶቻችን፤ በተጋሩ እናቶቻችን ላይ በጭካኔ ይፈጽማል። ሁሉ ነገር አመድ ሆኗል። ሰብል ሳይቀር። ጦርነቱ የተጀመረው
በአዝመራ መሰብሰቢያ ወቅት ነበር። ይህን ግፍንም የእኔ ማለት ይገባል። ኢትዮጵያዊነት ይህን ፈተና ማሸነፍ አለበት።
የትናንቱም ህወሃት የፈጸመው፤ የዛሬውም የኦነጉ ኦህዴድ ከግንቦት 7 ጋር ተቀናጅቶ የሚፈጽመው
እኩል መስተናገድ የሚችለው ኢትዮጵያ በውስጣችን በታቦትነት ከኖረች ብቻ ነው። ግማሽ፤ ሩብ፤ ሲሶ ኢትዮጵያዊነት የለም እና። መሬቱ
ብቻ ሳይሆን በባርነት ለመኖር አይፈቀድለትም ነበር የወልቃይት የጠገዴ ህዝብ። ጎንደር ህየውቱ ያለፈ የጠገዴ የወልቃይት ሰው ሄዶ
ለመቀበር እንኳን ብትን አፈር አይፈቀድም ነበር። ልክ እንደ መተከል ህዝብ። ነገም የአጣዬ፤ የማጀቴ፤ የኤፍራታ፤ የደራ፤ የኬሚሴ፤ የአዲስ አበባም፤ የሙለ ሽዋ፤
የሙሉ ወሎ፤ የከፊል ጎጃም ዕጣ ፈንታው ይህ ይሆናል። ጦርነቱ ሲነሳ ይህን አበክሬ በተደጋጋሚ ገልጬ ነበር።
ለዚህ ሁሉ መከራ ቁጥር አንድ ተጠያቄ ግርባው ብአዴን ነው። ለትናንቱም፤ ለዛሬውም፤ ለወደፊቱም
ለሚቀጥለው መከራ። ኢትዮጵያን ያፈረሷት፤ ያስፈረሷት አቶ ደመቀ መኮነን ናቸው። ለዚህ ነበር እሳቸው ተጠያቂ እንዳይሆኑ የጠቅላይ
ሚኒስተር እጩነታቸውን ያነሱት። የጭቃ እሾህ ናቸው።
ስለዚህ ነው ዛሬ „አንተ ሞት የማትለምድ ጉትን“ ግጥሜን ሥጦታው ለግርባው ብኤደን እና ለጌታው
ለኦነጋዊው ኦህዴድ እንዲሆን ያደረግኩት። በውነቱ ግጥሙን እምሸልመው ክስተት አልነበርም። ዘመኑ አነባቢ ያገኜ ያህል ነው ይህን
የዛሬ መሰናዶ ሳዘጋጅ የተሰማኝ።
እኔ እምጽፈው ዕውነት ለሆኑ ወገኖቼ ነው። ተግቼ እምሰራውም ለቅኖች ነው። ጠማሞች ጎባጣቸው
ቀንቶ ሰው ቢሆኑ እና ቢያደምጡኝ ይፈቀዳል። እያንዳንዱ ቃል፤ እያንዳንዱ ሐረግ፤ እያንዳንዱ ስንኝ የግርባው ብአዴን የ30 ዓመት
የሙት መሬት የህይወት ጉዞ ያጠይቃል።
ቀጣዩ ጊዜ እዬሞተ ለመኖር ከተፈቀደለት ሸጋ ነው ለምድር እንቧዩ ለብአዴን። መቃብርም ሥፍራ
ካገኜ እንደማለት። ሾተላዩ አብይዝም እዬለቀመ መሬት ውስጥ ይከዝነዋል። አይጠግብም ገድሎም፤ ዋሽቶም፤ አሸብሮም፤ ቀጥፎም፤ ቀርጥፎም፤
አጭበርብሮም። ባሰበው ልክ ከብርኃን በፈጠነ ሁኔታ እዬተጓዘ ነው። መካች አላገኜም።
ምን አልባት ዓለም ሰላአደመበት ስለ ትግራይ ዕንባ ሲል አቅሙን ሰብሮ ወደ ፈለገው አቅጣጫ እራሱ
ግሎባሉ ካልገራው አያያዙ አስፈሪ ነው። እኔ ደግሞ ከ10 ወር በፊት ነበር የተመድ ሰላም አስከባሪ እንዲገባ ያሳሰብኩት። እምነት
አልነበረኝም በጫካው የገዳ ጫካ የኦዳ ቤተ መንግሥት የጸጥታ ኃይል።
የዛሬ 6/7 ዓመት ይመሰልኛል ፖለቲከኛው አቶ አሬድ ጥበቡ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሊቀ - ሊቃውን
የመልክዕምድራዊ ሳይንቲስት ጋር ቢኦኤ ውይይት ነበራቸው። „እኔ እርስ
የእርስ በርስ ግጭት አያሰጋኝም ተጋምደናል“ ሲሉ እኔ ደግሞ በደጉ ዘሃበሻ ሞግቻቸው ነበር በአክብሮት። እርስወ ዕድለኛ ነውት።
እኔ ደግሞ እንቅልፍ የለኝም እጅግ እሰጋለሁኝ ብዬ። የሆነውም። እዬሆነ ያለውም ይህ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጥሞና ያለው መሪ ይሻል። በዬጊዜው አቅም የሚባክነው አቅምን
በአቅም ልክ ማዋቀር ስለማይቻል እና ጆሮም አልቦሽ ስለሆነ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ። ዕውነቶች ርሆወች ይፈራሉ። ግለት ውግዘት ይፈጸምባቸዋል።
ስለዚህ ዕውነት ከመሬት በታች ይውላል።
„ተረኛነት“ ስትል ሦስት አመት ጥሎ መጪ አለ። ሞቱም …. አና አለ። አንድ ሚዲያ ሦስት አመት ሙሉ „ተረኝነት“ ከሚለው ሲወጣ አለዬሁም። ምን አልባት
በቀብር ሰ ዓት ሊመጣ ይችላል። ደፋሩ አምክንዮ። የገዳ ወረራ፤ የገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ ዴስክርምኔሽ ይሉን ይሆናል
ወጥ በሆነ ድምጸት አንድ ቀን ያለው ሁሉ ተደማጭ ሚዲያ ይሁን የፖለቲካ ተንታኝ ወይንም ጦማሪ። የኔታ ጎዳና ብቻ ነበሩ „የማዬው
ነገር ከተረኝነት ያለፈ“ ነው ሲሉ ያዳመጥኩት። በሁሉም አመክንዮ
የማይናወጽ ግልጽ እና ቀጥተኛ አቋማቸው ሙሁራዊ ልኩን የጠበቀ ነው። ሚዛን! ይጨርስላቸው። አሜን።
· መከወኛ።
ተከባብሮ መዋደድ፤ ተከባብሮ እንደ አገር ልጅነት መወቃቀስ፤ ተከባብሮ መተዛዘን፤ ተከባብሮ መተማመን፤
ተከባባሮ መደማመጥ የፆም ውሃ ነው በእኛ ዘንድ። ለዚህም ነው አፈር ለማልበስ እንኳን ወገናችን አራባ እና ቆቦ ላይ እምንገኜው።
ስለ አዲስ አበባ የሚጨንቀው የሚጠበው፤ ከ40 ዓመት በላይ በወልቃይት እና በጠገዴ የደረሰው
ግፍ ምኑንም አይደለም። ስለ ወልቃይት ጠገዴ፤ ስለራያም አሁን ከሆነ ጎልቶ እዬወጣ ነው የሚመለከተው ትግራይ ውስጥ ስላለው የሰባዕዊ
መብት ረገጣም ለዛውም በጎረቤት አገር ጥቃት ሲፈጸምበት አይመለከተውም።
ሱዳን አራጣ ጎንደርን ይዛ እዬደነፋች ያም ለሌላው አይመለከተውም፤ የሱማሌ እና የአፋር ጉዳይ
ያዘለው ሌላው መከራ ከጁቡቲ፤ ከግብጽ ጋር ያለው መከራም እንዲሁም የአፋር እና የሱማሌ ጉዳይ ነው። ደቡብ ሱዳን እና ጋንቤላም
የታመቀ ፈንጅ ነው። ተነክቶ አያውቅም አጀንዳው። የስሜን ፖለቲካ አምድነትም ዋቢ ያለገኜ ጉዳይ ነው። ይህንንም የስሜን ፖለቲካ
ውድመትን አቶ ጎዳና ያቆብ በአጽህኖት ሲተነትኑት አድምጫለሁኝ። ሌሎቻችን ግን ሥም የለሾች ሁነናል። የማንገናኝ። የማንተዋወወቅ።
የተበተን። ወይንም እንደ ሎጥ ዘመን …. ?
የአርጄንቲና እና የጋና ህዝብ ዓይነት ነው የሆነው። በግሎባላይዜሽን ዘመን ጋና እና አርጀንቲና
የዓለም ዜጎች ናቸው። የዓለም ዜጎች ለመሆን ብሄራዊነታቸውን ያከበሩ ስለሆኑ። እኛ ሉላዊነት ቀረቶብን ብሄራዊነታችን የለም በውስጣችን።
ሰርጓል። የፖለቲካው ሙግትን ስታዳምጡ … „ተረኝነት“ ላይ ነው ያለው።
እኔ ታህሳስ 16/2019 ተረኝነት አይደለም የአገር ምስረታ ነው። ለአፍሪካም ለዓለምም መከራው ያሰጋል ብዬ ጽፌ ነበር። ደጉ ሳተናውም ለጥፎት ነበር።
አድማጭ የለም። መጋለብ ብቻ … ግልቢያው ሰው ቢያደን ምንኛ መልካም በሆነ ነበር። ግርዶሹ ለሰው መድህን ቢሆን ምንኛ ጥሩ በሆነ
ነበር። መረጃ ሲደርስ ይታፈናል። በወቅቱ ብዙ ነገር ማትረፍ ይችል
ነበፍ። ብቻ አዎን ብቻ …. ተያይዞ መስመጥ።
· ይህን ለማድመጥ የፈቀደ አልነበረም።
· የተፈቀደው
„ህወሃት የውደቅ እንጂ ትርፉ ገብስ ነው“ ነበር ሰፊ ሽፋን ሲሰጥ የባጀው።
https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post_29.html
የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}
https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤
ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
እህ! „ተረኝነት?“
እም! „ተረኝነት?“
ኦ! „ተረኝነት“ ሲታጠናቅነን እናውቅህ ይሆን?
እግዚአብሔር
ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15.04.2021
እጬጌው ተስፋ ሆይ ምነው ራቅከንሳ?
ጎዳናዬ ሰውኛ ተፈጥሮኛ ሥርዓትን መናፈቅ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ