ልጥፎች

ከኦክቶበር 26, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም። Gebet. Beruhige dich. Geduld.

ምስል
·       ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም። ሥርጉተ ሥላሴ 10.12.2017 ከጭምቷ፡ ሲዊዘርላንድ። „ እግዚአብሄርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብ እና ማስተዋል በባህር ዳር እንዳለ አሽዋ የልብ ስፋት ሰጠው። “ ( መጸሐፍ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 4 ፬ ቁጥር ፳፱)   ·       ማስተዋል በቅን ልቦና ስለማግሥት ሲባል። ሃዘን ለሌላ ሃዘን በመገባበዝ እርካታ አያስገኝም። ጥላቻን ጥላቻን ሊያክመው በፍጹም አይችልም። በጥላቻ ውስጥ መዳን የለም። በጥላቻ ውስጥ ምህረት የለም። በጥላቻ ውስጥ ተፈጥሮ የለም። በጥላቻ ውስጥ ዕምነት የለም። በጥላቻ ውስጥ ሃይማኖት የለም። በጥላቻ ውስጥ ሰብዕዊነት የለም። በጥላቻ ውስጥ ማግሥት የለም። በጥላቻ ውስጥ ዘመን የለም። በጥላቻ ውስጥ ትውልድ የለም። በጥላቻ ውስጥ ያለው ቂም ነው። ቂም ደግሞ በቀልን የወልዳል። በቀል አጥፊ እንጂ አትራፊ አይደለም። የበቀል መንገድ ነገን ያቃጥላል። ከሞት የሚገኘው አመድ ብቻ ነው። ጥላቻ ሆነ በቀል ትንፋሹ የጸላዬ ሰናይ ነው። ከፈጣሪ ጋርም ያጠላል። አበሶ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ እናትነቷ አብዝታ ታዝናለች። ጥላቻን የሚያድነው ሀኪሙ፤ ዶክተሩ ፍቅር ነው። ፍቅርን የሥነ - ልቦና ተግባር እንጂ የኣዋጅ አይደለም። ለዚህም ዘግይቷል። ግን አብዝተን ማተኮር እና በዚህ ዙሪያ መስራት አለብን። አሁንም ቢሆን ከግብታዊነት ወደ መረጋጋት፤ ከስሜታዊነት ወደ መስከን ሊመልሰን የሚችለው ጸሎት ብቻ ነው። ከፀሎትም መዝሙረ ዳዊት። እነሱ አውሬ ይሁኑ፤ ጨካኝ ይሁኑ፤ ሌላው ይህን የአውሬነት እና የጭካኔ መንፈስ እንደ መልካም ነገር መጋራት አይኖርበትም። ትግራይ የሚኖረው ህዝብ አ...