የእኛ መከራ ማለቂያ የለውም። ሞት ስንቃችን ሆኑ። "በጉጂ ዞን ወርቅ በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች መሬት ተንዶባቸው ሕይወታቸው አለፈ" BBC
"በጉጂ ዞን ወርቅ በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች መሬት ተንዶባቸው ሕይወታቸው አለፈ" https://www.bbc.com/amharic/articles/c70kn2y5pn8o ከ 3 ሰአት በፊት "በጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ በተባለ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ላይ የነበሩ ሰዎች መሬት ተደርምሶባቸው መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ውስጥ አደጋው በደረሰበት አካባቢው ነዋሪ የሆኑት ኢዮብ ጂሎ እንዳሉት ለአደጋ መንስዔ የሆነው በማሽን የተቆፈረ መሬት ነው። "መሬቱ በሁለቱ ቦታ በማሽን ተቆፍሮ ነበር። ሰዎች በተቆፈረው መሬቶች መካከል ገብተው ነበር ወርቅ ሲፈልጉ የነበረው። በዚህም ምክንያት መሬቱ ተደርምሶ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል" ሲሉ ተናግረዋል። አደጋው ሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም. ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ መድረሱን የዓይን እማኙ ተናግረው ሁሉም ሟቾች ወንዶች መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በማሽን እና በባሕላዊ መሣሪያ ታግዘው በአደጋው ከመሬት በታች የተቀበሩትን ሰዎች ለማዳን ለአምስት ሰዓታት ያህል ቁፈሮ ካደረጉ በኋላ ግለሰቦቹ ሕይወታቸው አልፎ አስከሬናቸውን ማውጣታቸውን ተናግረዋል። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች እንደሌሉ እና መሬቱ ተንዶባቸው ተቀብረው የነበሩት የሁሉም ሰዎች አስከሬኖች መውጣታቸውን አክለው አስረድተዋል። የጉጂ ዞን የኮሚዩኔክሽን ኃላፊ አሸናፊ ዳንቁ በአካባቢው በባሕላዊ መንገድ ማዕድን የሚቆፍሩ ሰዎች ላይ መሰል አደጋዎች እንደሚከሰቱ ገልፀዋል። "በባሕላዊ መንገድ ማዕድን የሚያወጡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። አንድ ጉድጓድ ውስጥ በርከት ብለው ነው የሚቆፍሩት። ይህ ደግሞ አደገኛ ነው" ብለዋል። አክለውም በባሕላዊ መልኩ ወርቅ የሚያወ...