ልጥፎች

ከማርች 25, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጎንደር እና አሳሩ በርብርብ።

ምስል
ጎንደር እና አሳሩ በርብርብ።   እቴጌ ጎንደር ከምጥ እምትገላገልበት ቀን ቢናፍቀኝም እዬራቀ መሄዱን ሳስተውል እንደ ፈቃድህ ይደረግላት ማለቴ አይቀርም። የማዝነው አንድም ተቆርቋሪ ነፍስ ማጣቷ ነው። ለምን ሲባል አብዛኞቹ ይታገላሉ ግን ለፖለቲካ ድርጅት ማልያ ነው የሚታገሉት። የጎንደር ህዝብ ደግሞ ለመላው ኢትዮጵያ ነው የሚታገለው። መፈክሮቹ፣ ሞቶዎቻ ከብሄራዊም አልፍ ሉላዊም ነው። ጎንደር ላይ በነፍስ ወከፍ ይሁን በወል የሚከወኑ ነገሮች የተደራጁ፣ የተቀናጁ ናቸው። ይህ ግን አይወደድለትም። 27 ዓመት ሙሉ ስውር የሁሉም ነገር ምንጠራ ተከናውኗል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከሰሞኑ በሰጠው ቃለ ምልልስ ከዬኔታ ዩቱብ ጋር የጎንደር እስረኞች ተለይተው ይሰለባሉ ብሎ ምስክርነቱን ሰጥቷል። በሁለመናው 27 አመት የደቀቀ ቀዬ ነው ጎንደር። ቀደም ባለው ጊዜ ተቆርቋሪ ሆነው የታዩት ጠሚር አብይ አህመድ የመጀመሪያ ዒላማ ያደረጉት ጎንደርን ነው። የኢንጂነር ስመኜው በቀለ ህልፈት ግንዱን ነበር ከመሠረቱ የነቀሉት። በዋዜማው ባለቤታቸው ጎንደር ልከው ነበር። ቀጥሎ የሆነው ገዳ ንጉሡ ጥላሁን እና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ዲሲ ተላኩ፣ ሲመለሱ የሰኔው ግርግር እና የአማራ ሊሂቃን ከጎንደር ሦስት፣ ከወሎ አንድ ተጨፈጨፋ። መቼም ለጎንደር የጦር ቀጠና ስለሆነ አንድ ዶር ማውጣት ምን ያህል ህልም እንደሆን ያለፍንበት ስለሆን እናውቀዋለን። ለሦስት ወር ስልጣን ቹቻ እና ሰኔል ተሸለመ። ጥምቀት ምን ያህል ሎድ እንደነበረ እሰቡት ጎንደር። አደጋም ደርሷል። ያ እንዳለ የግንቦቱ ኢዜማ ጎንደር ተላከ። በዛው ፋታ በማይሰጠው ሰሞናት። ጠብ ለመጫር ነው። ያዬነው ባዶ ወንበር ነበር። ግን ስብሰባው ተስተጓጎለ ተብሎ አገር ይያዝልን ሆነ። የበጠበጡ ካሉ ሊቀጡ ይገባል። ሲጠሩ አለመሄድ ሲችሉ መበጥ