ልጥፎች

ከጁላይ 27, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ ሊሂቃን የሞት ፍርድ?

ምስል
ይገርማል? ዝንቅንቁ የሰናፍጭ   እና  የጤፍ ፍጭቱ ግብረኛ? „ዋይታ ለማን ነው? ሃዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኽት ለማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው?“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፳፱) ከሥርጉተ© ሥላሴ 27.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) የኔዎቹ ዛሬ በመደዳ ነው የምሄድበት፤ አሜሪካኖች ማን ይገኝ አይገኝ ሙግት ላይ ናቸው ከኢንባሲው ጋር፤ እኔ ደግሞ አገር ቤት ያለው ጭጋጋዊ ጉሙ ያስጨንቀኛል፤ እንቅልፍ ነስቶኛል። አዬር ላይ ራሱ አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት ምን ይገጥመው ባይ ነኝ።  የገረመኝ በዶር አብይ አህመድ ሰብዕና ዲሲዎች ተደናግጠዋል፤ ይገርማኛል ሰው እኮ ጥሩ ልሁን ቢል በአንድ ጊዜ አይችልም። ሰብዕናው አብሮ ካልተፈጠረ። ለነገሩ ተራራ ሲያ ለባጀ ሊደንቅ ይችል ይሆናል …    ግን ወገኖቼ የት ነበሩ? የመረጃ ምንጫቸው በቃ ሚደያው ያደማባቸው ማህበርተኛ ብቻ ነበሩን? አንድ መሪ ሲመጣ ግድ የሚሉ ነገሮች ይኖራሉ። ወደፊት የመጡ ሰዎችን ማጥናት እኮ የዜግነት ግዴታ ነው። የመምርጥ መብት ላይኖር ይችላል፤ ግን በመንፈስ ለመቀበልም ላለመቀበልም ቅድመ ጥናት ማድረግ ይገባል … አብይ ሆነ ለማ ዛሬ አልተፈጠሩም፤ አሜሪካ ስለተገኙም አይደደለም ጥሩ ሰዎች የሆኑት።  … ሰብዕናቸው እና እምነታቸው አስተዳደጋቸው እና ተፈጥሯቸው ይሄው ነው። ራሱ ቡድናቸው የሚመሰጥ ነው። ቡድናቸው ስል የፖለቲካውን ማለቴ ሳይሆን ሃይማኖታዊውን ወይንም የሰውን ህሊና ለበጎነት ለማሳናዳት ያላቸው የትትርና ማህብር ማለቴ ነው። የሆነ ሆኖ … ዛሬን ንዑስ እርስ ላስኬደው ነው … በመደዴው ሞትና የአማራ ሊሂቃ...