የአማራ ሊሂቃን የሞት ፍርድ?

ይገርማል?
ዝንቅንቁ የሰናፍጭ
  እና
 የጤፍ ፍጭቱ ግብረኛ?

„ዋይታ ለማን ነው? ሃዘን ለማን ነው?
ጠብ ለማን ነው? ጩኽት ለማን ነው?
ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው?
የዓይን ቅላት ለማን ነው?“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፳፱)
ከሥርጉተ© ሥላሴ
27.08.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

የኔዎቹ ዛሬ በመደዳ ነው የምሄድበት፤ አሜሪካኖች ማን ይገኝ አይገኝ ሙግት ላይ ናቸው ከኢንባሲው ጋር፤ እኔ ደግሞ አገር ቤት ያለው ጭጋጋዊ ጉሙ ያስጨንቀኛል፤ እንቅልፍ ነስቶኛል።

አዬር ላይ ራሱ አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት ምን ይገጥመው ባይ ነኝ።  የገረመኝ በዶር አብይ አህመድ ሰብዕና ዲሲዎች ተደናግጠዋል፤ ይገርማኛል ሰው እኮ ጥሩ ልሁን ቢል በአንድ ጊዜ አይችልም። ሰብዕናው አብሮ ካልተፈጠረ። ለነገሩ ተራራ ሲያ ለባጀ ሊደንቅ ይችል ይሆናል …
  
ግን ወገኖቼ የት ነበሩ? የመረጃ ምንጫቸው በቃ ሚደያው ያደማባቸው ማህበርተኛ ብቻ ነበሩን? አንድ መሪ ሲመጣ ግድ የሚሉ ነገሮች ይኖራሉ።
ወደፊት የመጡ ሰዎችን ማጥናት እኮ የዜግነት ግዴታ ነው። የመምርጥ መብት ላይኖር ይችላል፤ ግን በመንፈስ ለመቀበልም ላለመቀበልም ቅድመ ጥናት ማድረግ ይገባል … አብይ ሆነ ለማ ዛሬ አልተፈጠሩም፤ አሜሪካ ስለተገኙም አይደደለም ጥሩ ሰዎች የሆኑት።

 … ሰብዕናቸው እና እምነታቸው አስተዳደጋቸው እና ተፈጥሯቸው ይሄው ነው። ራሱ ቡድናቸው የሚመሰጥ ነው። ቡድናቸው ስል የፖለቲካውን ማለቴ ሳይሆን ሃይማኖታዊውን ወይንም የሰውን ህሊና ለበጎነት ለማሳናዳት ያላቸው የትትርና ማህብር ማለቴ ነው። የሆነ ሆኖ … ዛሬን ንዑስ እርስ ላስኬደው ነው … በመደዴው

ሞትና የአማራ ሊሂቃን በተቀደ ሁኔታ። …

ይግርመኛል የመግለጫ ሰጪዎች ብዛት እና ጭብጡ፤ የቀብር ሥርዓት ዝርዝር መረጃ ይህን ስሰማ ሞገድ የሚባል አንድ መጸሐፍ አንብቤ ነበር። በስጦታ ነበር ያገኘሁት ...  የመጸሐፍት ቀበኛ ነበርኩኝ አገር ቤት እያለሁኝ፤  የመጸሐፉ ጭብጥ እንዲህ ነበር ...

አንድ ዘረፋ ይከሄዳል በአንድ ሚሊዮን ብር ወጪ ሊሆን ይችላል። ወንጀሉ በተፈጸመበት ቅስፈት ደግሞ ጋዜጣው ታትትሞ ይወጣል፤ ሦስት ሚሊዮን ይሸጣል ... እና የሰሞኑ ነገር እንደዚህ ነው እኔ የሚታዬኝ ... 

ሁለት ድንቅ ሊሂቃን ሞት በተከታታይ ቀናት ታወጀባቸው። የአብርሃም በጎች … የዘላለም ስንብት አደረጉ። ለመስዋዕትነት የፈቀዱ … እዬተነዱ ሄደው እሬሳ እርክክብ። ግን ባለቤት የሌላቸው ጥንዶች፤ የተገፋ፤ ብትን አፈር ያጣው ማህብረሰብ ልጆች!ደመ ከልብነት። መርማሪውም፤ ዳኛውም፤ ፈራጁም፤ ገዳዩም አስገዳዩም ... 

እንዲህ ሆነ ለመሆን በፈቀደው ሁኔታ …  

እኔ ትናንት ዜና ሳዳምጥ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ማክሰኝት እንደ ተወለዱ አዳመጥኩኝ። ማክሰኝት ማለት ከጎንደር አዲስ አባባ መስመር ላይ የምትገኝ ትንሽዬ የገጠር ከተማ ናት። አዋራጃዋ ጎንደር ዙሪያ አውራጃ ይባላል። ወረዳው ደግሞ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሲሆን የወረዳው ከተማ ደግሞ የበቃ የቆርቆሮ ቤት የሌላት ጠዳ ትባላለች።

በጎንደር ትናንሽ ከተሞች በድህነት በሽታሽቶሽ በዬሥርዓቱ ይከትከቱ እንጅ እጅግ የሚመሰጡ ብሄራዊ የትውፊት ማህደሮች ናቸው። ብዙ ያላተነገረላቸው ግን ለዘመናት ትውልድ የእኔ ብሎ በዛ ውስጥ ሰፊ የምርምር ሥራ ቢሠራባቸው የፕሮፌስር ደረጃ ዕውቅና ሊያሰጥ የሚችል ተዝቆ የማይልቅ የመንፈስ ሃብታት መሰረት ናቸው።

ባለፈው ጊዜ አንድ ቪዲዮ ሳይ በደርግ ዘመን ይሁን በዓጤው የተተከሉ በዬከተሞች የስልክ እና የኤሌትሪክ ማቆሚያ ምስሶዎች እጅግ አርጅተው እራሳቸውን ችለው መቆም ተስኗቸው ተጋድመው ነበር ያዬኋዋቸው።

ያው ባለቤት ለሌለው ቀዬ የተገባ ስለነበር ብዙም አልደነቀኝም። ወደፊትም እንዲሁ ነው። ተስፋን እግዚአብሄር ማድረግ መደበኛ የእኔነቴ መግለጫ ቢሆንም ሁሉም ጎንደር ላይ ሲደርስ ጀርባውን እንደሚሰጥ ከታሪክም፤ ከሂደትም አሁን በእኔ እድሜ ከማዬው ሁሉንም ነገር ማስተዋል ችያለሁኝ።

ስለዚህ ጎንደር ነገ ለሚለው ማገዶነቱ በቀጣይነት፤ ሞቱ እና ፍልሰቱ በቀጣይነት፤ ድልድይና መናጆነቱ ደግሞ በቀጣይነት አይቀሬ ነው። የሥነ ልቦናው ወቀጣውም። አሁን ኢቲቪ ሆን ብሎ እዛ አካባቢ ሲደርስ የሚያደርገውን የግለት ድቅደቃ ልብ ላለው ሰው ብዙ የሥነ - ልቦና ድቀት ዘመቻ ላይ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም ለነገ ተስፋየ ደመናማ ይሆናል ማለቴ ምን አልባት ይህ ጨልምተኝነት ሆኖ ሊታይ ይችል ይሆናል። ነውም። ግን የእውነት ፖስተኞች የሚነግሩን ይህንኑ ነው።

ኢህአዴግ 7 ሚሊዬን አባል አለኝ ይላል። ከዛ 7 ሚሊዬን አባላት ውስጥ „የነፃነት ሃይሉ“ ገደልኩ የሚለው ፈልጎ ጎንደሬው ነው። ተዋጋሁ ሲልም ተገደለ የሚሰማው ያው ፊት ለፊት  ጎንደሬው ነውን። አሁንም ለለውጡ ማያያዣ ተገደለ ተብሎ የምንሰማው አሁንም ጎንደሬው ነው። ሌላው ለልማቱ ተስፋ አለው። ብዙ ዓይነት ተስፋ እያደማጥኩኝ ነው። ጎንደር ደግሞ ተስፋው ሞት ነው። የጎንደር እናት ዘመን ተዘመን መስቃ እና መቃ ትልበስ። ኢትዮጵያዊ ዜጋ አይደለችምና …

የገረመኝ የስለት ልጁ ኢንጂነር ስማኘው በቀለ በተፈጠሩበት ዘመን እና ለትምህርት በደረሱበት ዘመን በዚህ ዘመን ት/ ቤት መሄድ ጣር ነበር። ት/ ቤት የሄደውን ኢህ አፓ መማር አያስፈልግም የሚል መርህ ይከትል ስለነበር ይገድለዋል፤ የኢህአፓ መሪዎች የተፈጠሩበት ቀይ ግን ተማሪው ቀጥ ብሎ ካለምንም ስጋት ይማራል። ትምህርት አቁሙ ጎንደር ላይ ነው። 

ት/ ቤት ሲከድም በነጭ ሽብር ባንዳ በማለት ዕድሜ ሳይለይ ያልቃል፤ ወይንም የመንፈስ ጫና ይፈጥርበታል። ቤት ውስጥ በዬቤታችን በር ሥር የሚላክ በራሪ ጹሁፍ ነበር። ደርግ ደግሞ ት/ ቤት አልሄድክም ብሎ ያሥረዋል፤ ይገርፈዋል፤ ያሳድደዋል። ዕድሜ አይጠዬቅም።  

ፋሲል ግንብ በጅምላ እስር ነበር። አብዛኞቹ ታዳጊ ወጣት ነበር። መንገድ ላይ ነው እዬታፈስን የታሠርነው። ባዶ ወለል ላይ ነበር ያደርነው። በጉልበታችን በጠጠር ላይ ተንበርክከን እንድንሄድ ተደርጓል። 

ይህም ብቻ አይደለም የጠጣናው ውሃ ይገርም ነበር። የጎርፍ ውሃ ነበር በእሳት አደጋ ተጭኖ መጥቶ እዬተሻማን የጠጠነው። ዳቦ ከዬት እንደመጣ የማይታወቅ ለውሻ የሚሰጥ ዓይነት የከሰለ  በእንክርዳድ የተጋገረ ይመስል ነበር። ጫካው በባሩድ ጭስ የታወደ ነበር፤ የጎንደር እናት ሌት ተቀን ታነባ ነበር። ሌለቹም በከባድ ወንጀል እስራቸው ቀጥሎ ያው መከራና መርዶ ሆነ፤ ከፊሉም ቤተሰቡን በትኖ ጫካ ገባ።  ወላጅ አልባ በስጋት እና በውጥርት፤ መካራው በጣምራ ነበር በዬቤተሰቡ …

 በዛ ውስጥ አልፎ እዚህ ደረጃ መድረስ ለእኔ እውነት አልመስልሽ አለኝ። የነበረው አማራጭ ወይ ጫካ መግባት፤ ወይ መታስር፤ ያ ቢቀር ደግሞ በአጭሩ ሥራ አፈላልጎ ከአንዱ መሸጎጥ። ወይ ደግሞ ዕድሜያቸው የደረስ ውትድርና መሄድ። ወይ ደግሞ እንደ አባት አደሩ ትምህርትን ትቶ ቤት መቀመጥ ሴቶች መስፋት እና መፍተል ወንዶች ብይ መጫወት።

ለዛም ሜዳው ሰላም ስሌለው ወላጅም ስለማይፈቅድ እዛው እንደ ሰርዲን ክምችት ብለን ቤት ውስጥ ማሳለፍ። የገበሬ ልጅ ደግሞ እርሻውን ቀጥሎ አግብቶ ጎጆ መውጣት።  በዚህ ማህል በቀዩም በነጩም ሽብር በዬቀኑ መርገፍ ይታከልበታል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ የእክሌ ልጅ ታሠረም አለበት … 

ብቻ ዘለዓለሟን ጎንደር የጉም ቤተኛ ናት።  ከቶ ምን ላድርግልሽ እምቤቴ የእኔ ውስጥ እትብቴ?

ጥዋት ት/ ቤት መሄድ አይቻልም። እንደዛ ጥይት ሲወርድ አድሮ፤ መንገድም ላይም ሞት ነው፤ ከአጠገብ ሲወድቅ ብቻ ነው የሚታዬው፤ ገዳዩም አስገዳዩም አይታወቀም። መኪናው ሌሊቱ ሁሉ መሬት የተንቀጠቀጣ ያህል ሲያርድ ታድሮ ደብተርን ሰብስቦ ት/ ቤት መሄድ ህልም ነው። ቢኬድም ዴስክ ላይ መተኛት ነው።

ለመሄድም ት/ ቤት ቤተሰብ አብሮ መሄድ አለበት። ሌሊትም መብራት አብርቶ ማጥናት አይቻልም። ሁሉ ነገር ጨላማ ነበር። በዛ ጨለማ ውስጥ ታልፎ ያውም ማክሰኝት ላይ ወገን ጠቀም ለሆነ ብሄራዊ ዕድል መብቃት በሰማይ ታምር እንጂ እኔ የምድር ነው ማለት አልቻልኩም።

በነገራችን ላይ በፍጹም ኢንጂነር ስመኛው በቀል የጎንደር ልጅ ይሆናሉ ብዬ አላስብም ነበር። በምን ሁኔታ ታልፎ? ሌት እና ቀን ጦርነት ነው። ሌት እና ቀን ሞት ነው። ሰው ሰላም አልባ እንዴት ተረጋግቶ ይማራል። መኖር እራሱ ጎንደር ላይ ተፈጥሮ አያውቅም። 

ሁሉ ሰላሙን ተጠቅሞ ኖሮ ዛሬም የተደላደለ ነገር ላይ ሲበቃ፤ ጎንደር ግን በዛ ጢሳማ ዘመን አንድ እንደ ወልዴ ወጥቶ አስፓልት ላይ እንደ ወጣ መቅረት … ጎንደር ግን አንቺ ምንድነው ዕጣ ፈንታሽ? ስለምንስ የኢትዮጵያ አካል ታምሳልነት ተሰዬመለሽ? አንቺ ግዞተኛ እስቲ ተናገሪ … በሞቴ የበሞቴ እናት አድባሬ?

የደርግ መኮንኖች ት/ ቤት ሲመጡ ከጠረጴዛ ውስጥ ሁሉ እንገባ ነበር። መንገድ ላይ ፋቲክ የለበሰ ላለማዬት ሹልቅልቅ መንገዱን መከትል ግድ ይል ነበር። በአስፓልት አንሄድም ት/ቤት፤ ሠፈር ላሰፈር ኮረኮንች ስለሆነ ምርጫችን ጫማችን ተሎ ተሎ ነበር የሚያልቀው። ሜዳ ወጥቶ ሰኞ ማክሰኞ፤ ቅልሞሽ፤ ገበጣ፤ ኳስ፤ ብይ፤ ገና መጫወት አንችልም ነበር። የልጅነት ወጋችን አይታወቅም ነበር።

ግን ልጅነት ለጎንደር ልጅ ምን ማለት እንደሆን አይደለም ትናንት በ27 የትግራይ መሳፍንት ዘመንም አያውቀውም። የሚታደነው፤ የሚገደለው። ዘሩ እንዲጠፋ የሚደረገው እሱ ነውና። ዛሬ በወንድ የዘር ማፍሪያ ሽቦ የሚገባበት ለጎንደር ብቻ ዘመን ላይ እኮ ነው ያለነው። መንኮላሸቱም እንደዚሁ።

ትግራይ ላይ ሰው እህል ውሃ ቀምሶ ማደሩ እራሱ ይገርመኛል። ነገስ እዬራዊ ቁጣው ምን ይሆን? የሚሰማው ሁሉ ለትግራይ ቀጣይ ትውልድ መባረክ አደጋው ሰፊ ነው? ይሄ ቀን ያልፋል፤ የእዮር አደባባይን መቅሰፍ ደግሞ አዬር መቃዋሚያ አያስቆመውም። ዛሬ ሊሆን አይችልም ግን ሰለነገ ዋስትና የለም ግፍ ቁጣን ያመጣል። ቁጣው ደግሞ ይግባኝ የሌለበት ነው።

የሆነ ሆኖ በዚህ ስሌት ስሄድ በምን ታምራዊ ገድል ኢንጂነር ስመኛው በቀል ለዚህ የተረጋጋ የመንፈስ ሁኔታ በሚጠይቅ የቀንበጥ ጊዜ ያን ሁሉ የመንፈስ የሥነ - ልቦና ጫና አልፈው እዚህ ሊደርሱ ቻሉ? ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ሰብዕና አላቸው ማለት ነው። እኔ አልቻልኩማ።

ሌላው እንዴትስ የወያኔ ሃርነት ትግራይን አምነው እዛ ኢትዮጵያ ሊኖሩ ፈቀዱ? ውሳኔው ከባድ ነበር። ከባዱ ውሳኔም ከባድ መስዋዕትነት አስከፈለ። ነገስ የእሳቸውን ቦታ ተተኪው የትኛው ሰው? የዬትኛው ጉልበተኛ ማህበረሰብ አባል? ለሱስ የሚደረገው ጥበቃ እና ለእኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ የተሰጠው አትኩሮት እና አክብሮት ምን ያህል ነው? ልዩነቱን በማዬት ህሊናችን ፍርድ ይሰጣዋል።
እኔ የቀብር ሥርዓቱ ወዘተረፍ ጉዳዬ አይደለም። 

በዚህ እሳት ዘመን ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባ ነበር። እንዲህ እንደዋዛ፤ እንዳልባሌ ነገር ደመ ከልብ ሆነው መቅረት የሚገባቸው አልነበሩም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ አዝኖላቸዋል፤ ፍትህን ጠይቆላቸዋል። ግን መንግሥት ቅሱሙ መሰበሩን ብምን ካሳ ያሰዬዋል? ያው ፍቅር አይከሰስም? መደመር አይወቀስም በሚል ይሆን? ስለትናንት ይቀር ለማለት በደል ቀጥሎ በምን ስሌት? ህሊና ላለው?

ከገዳዮቻቸው የሳጅን በረከት ጋንታ በስተቀር ንጹሃን ዜጎች ሀዘኑ ግበቷቸውል። የሚገርመኝ የ27 ዓመቱ ወንጀል አትንኩት፤ አታንሱት እዬተባለ ይሄም ተከድኖ ይቅር እንደሚባል፤ ወይንም እንደሚንዘላዘል፤ ወይንም ገዳዮቹ ምቹ ሁኔታቸው እስኪአደላድሉ ድርስ ዕድል ለገዳዮች እንደሚሰጥ ነው እኔ እማስበው፤
 የ154 ቁስለኛ፤ የ2 ሰማዕት እረፍት ብቻ ሳይሆነ የሚሊዮኖች የህሊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እስከ አሁን ፍንጭ ጠፍቶ አይመስለኝም  ….  እንዲህ የዳታ የቅልቅል ሰርገኛ የሆነው ጉዳዩ …

ሌላው የገረመኝ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ጎንደሬ አማራ ሆነው ሲዖሉ አቶ በረከት ስምዖን እንዴት እስከ አሁን ዕድል ሰጧቸው? እኛ የማናውቃቸው ብዙ ጎንደሬዎች እኮ ድራሻቸው ጠፍተው ቀርተዋል። በማንኛውም ሁኔታ የሥራ ሃላፊነት የነበሩ፤ ግን ብቁ እና ንቁ ጎንደሬዎች ላይ የዘር ጭፍጨፈው በሳጅን በረከት ስምዖን ኔት ወርክ በስውር ምንጠራው ሲከውን ነው 27 ዓመት ሙሉ የኖረው።

አይደለም ጎንደር ተውልደው ያደጉት ጎንደሬ አማራዎች ሌላ ቦታ ተወልደው አድገው ግን ቤተሰቦቻቸው ጎንደሬ አማራ ከሆኑ በቅለው ሳይጨርሱ ተቀንጥሰው ይቀራሉ። ምክንያቱም የበታችን የፈጠረው ጉዳይ ነው። የማናቸውም ሰውር ሴሬ ተፈጻሚ ናቸው የሚሆኑት ጎንደሬዎች። 

አሁን ፕ/ እምሩ ስዩም ጎንደሬ ናቸው የአልፋ ጣቁሳ ሰው፤ ግን ያደጉት ባህርዳር ነው። አዲስ አበባ ላይ ታድነው ታክሲ ውስጥ ግን ተገድለዋል። የዩንቨርስቲ መምህር ብቻ ናቸው። በዬትኛውም ዕውቅና መድረክ የሉም፤ አልነበሩም። ፎቷቸውን እንኳን እኔ ስንት ጊዜ ሞክሬ ጉግል ጋላሬ ላይ ላገኘው አልቻልኩኝም። ደመ ከለብ ሆነው የቀሩ አንጡራ ሃብት ናቸው።

ፕ/ እምሩ ስዩም ባህርዳር ባያድጉ ኖሮ ጎንደር ቢኖሩ በትምህርታቸው ገፍተው ለዚህ ዕድልም አይበቁም ነበር። ሆነ ሆኖ እንደ ወጡ ነበር የቀሩት፤ ለእህታቸው ሬሳ ብቻ ነው የተላከላቸው። ይሄ ነው ሲዖሉ በረከት ስምዖን ማለት። ነገም ይቀጥላል ... የሞት መንደር በ ዓይነት ሳጥን ሰኔል ዙቻ አዘጋጅታ ትጠብቅ እንደለመደባት ...

አሁን የኢንጂነር ስመኛው በቀለን የአባታቸውን ቃለ ምልልስም አዳመጥኩኝ፤ ከማክሰኝትም ያነሰች ሸንበቂት ከምትባል ገጠር ወደ ወገራ መስመር ካላች ባዕት አንደሚኖሩ አዳመጥኩኝ፤ የስለት ልጅ እንደሆኑም ከቃለ ምልልሱ ተረዳሁኝ። እናታቸው ሙሉቀን እንደሚሏቸው ሁሉ አዳመጥኩኝ። ይህን ሁሉ የሚያውቀው የሲዖሉ የበረከት ጋንታ እስከ አሁን እንዴት ሊያቆያቸው ቻለ ነው ጥያቄ?

ስለምንስ አሁን ጊዜው ተመረጠ? ምን የተፈራ ነገር ነበር? ምንስ የተፈራ ነገር አለ? ያው ማህንዲስ እኮ ቁጭ ብለህ ሥራ ብትለውም አይችለውም። የመስክ ሠራተኛ ቢሮ ተቀምጦ መሥራት ተፈጥሮው አይፈቅድም። ሌላ ስጋት ኑሮ ከሆነ …

ራሱ ይህ የሃላፊነት እርከን ታምኖ ለጎንደሬ ለአማራ እንዴት ተሰጠ?  እራሱ ለዘር መብቃታቸው የሚገርም ነው። ለትዳር ለወግ ለማዕረግ መብቃትም እንዲሁ። ቀጣዩስ ልጃቸው ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል? በሥነ - ልቦናው ላይ እና በጤናው ላይ ምን ሊመጣ ይችላል የልጆቻቸው? ምን አቅደዋል ገዳዮቹ የማፍያ ስኳዶች?

እንጂነር ስመኘው በቀል ከዚህ ቀደምም ሁለት ፕሮጀክቶችን ለግብ እንዳደረሱ አዳምጫለሁኝ። ሦስተኛው ተልዕኮ አጅግ በውስብስብ ፖለቲካ የታመቀ ግን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የ100 ዓመት ህልም መናጆነት ነበር። አሁን ህልሙ ሲቀለበስ የፕሮፓጋንዳው ሰልፍ የሃይል አሰላለፉን አሳምረው በደም ለነገ ደግሞ የበቀል ጥሪት ነው …

ይህ ጉዳይ የጎንደሮች የአማሮች ብቻ አይመስለኝም፤ የአባይ ብርሃን የተስፈኞች ሁሉ እንጂ … ለዚህ ነው የአዲስ አበባ ህዝብ ፊት ለፊት ወጥቶ እንባውን እያፈሰሰ የሚገኘው። ወይ አዲስ አባባ በቃ በዬወሩ የሰማዕታት መንደር ሆንሽ ለዛውም በዘመነ አብይ? ይገርም።

ነገረ አባይ የኢራቅ እና የኢራን፤ የፍልስጤም እና የእስራኤል፤ የቱርኪ እና የኩርድሽ ጉዳይ ዓይነት ነበር። ዓባይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ መሰረታዊ አንኳር ነው። ያው ነገረ ኢትዮጵያ ስለሆነ በምዕራቡ ዓለም ይህን ያህል አጀንዳም ባይሆንም። 

ግን ለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ  ሥር ነው?ለዚህ ሃላፊነት ብቁ ነው ተብሎ ጎንደሬ አማራ መታጨቱ ራሱ ውስጤ ለመቀበል የከበደው ነገር ነው። ዓላማው ምን ነበር? እኛን ጎንደሬዎችን የሚያቃረብ የሚያምን መንግሥት ከወዴት ተገኜ? ለዛውም ዘራችን ከነቀለ፤ ታሪካችን ካፈለሰ፤ ማንነታችን ከቀማ፤ ትውፊታችን ከዘረፈ፤ ደማችን ከቀበረ የትግራይ መሳፍንት መንግሥት ይህ ዕውቅና የሚያስገኝ ቦታ እንዴት ተሰጠ? ስለምን ተሰጠ? ደግሜ እምናገረው እስከ ትናንት ድረስ እኔ ጎንደሬ መሆናቸውን አላውቅም ነበር። 

አመኜ ለመቀበል አሁንም ጋዳ ነው። እኔ ተግባሩን እንጂ ዘር መልቀም ስላለደኩበት። ያው ነገረ አባይ ግድብን በገለልተኝነት ነበር እምከታታለው። ልክ እናት ቤተ ክርስትያኔን ቅድስት ተዋህዶን እምለከተው እንደ ነበረው፤ ወቀሳም ነቀሳም ትችትም አቅርቤ አላውቅም። በዝምታ የማልፋቸው አመክንዮዎች አሉኝ። ምንም አስተያዬት የማልሰጥባቸው። 

አሁን እኔ እዚህ ሲዊዝ ስኖር ስብሰባ ላይ ተጋብዤ ክፈችልን ስብሳባውን ካልተባልኩ በስተቀር እጄን አውጥቼ አስተያዬት መስጠትን አልፈቅደውም። ዝም ማለት ምርጫዬ ነው። አባቴ የበዛ ዝምተኛ፤ እናቴ ደግሞ የበዛች ሳቂተኛ ናት። እኔ ደግሞ ዝም ማለትን የምፈቀድ፤ ጫጫታ እና ሁካታን ለደቂቃ ለማስተናገድ የማልፈቅድ 

… ይህም ሆኖ …

ምንም ሳናደርግ ዘግተን በስደት ለመቀመጥ እንኳን ሰላም የሰጠን፤ የሚሰጠን፤ ሰላም ሊሰጠን የሚፈቅድ ነፍስ እኔ ገጥሞኝ አያውቅም ከነጮች በስተቀር። እንደ ድርጅት የአንድነት የሲዊዝ ደጋፊዎች መንፈሳቸው ቅርቤ ነበር። 

ብቻ ሁለመናችሁን ሰጥታችሁ ግን ልባችሁን በሌላ እንዲገጠም ቀጣዩ ዘመቻ ይሆናል። ግን ለምን? ስለምን ጎንደር ክ/ሀገሩ እራሱ ተፈጠረ? ስለምንስ መከራችን ማለቂያ አጣ? መቼስ ነው የጎንደር እናት ከእንባ፤ ከጥቁር ልብስ፤ ከጭንቅ ማጥ የምትወጣው? መቼ ነው የጎንደር እናት ከስጋት የምተላቀቀው? አቧራ ለብሳ እንኳን አልተፈቀደላትም መኖርን። በእሷ ልጆች ደም ግብር ሌሎች ይፏልላሉ … እሷ ግን አሁን ተቀብራ ታነባለች? ግን እስከመቼ?

የሚገርመኝ አሁን ሌላ ሞት ተጎዝጉዞ ተሰናድቶ ለተረኛ መጠበቁ ነው። መንግሥት አለ ወይንስ የለም? መንግሥት አለ ከተባለ ወደፊትም በዚህ በፍቅር ጉዞ ከወንጀለኞች ጋር ህግ ተረግጦ፤ ፍትህ ተዛብቶ፤ ደም በዬመንገዱ እዬፈሰሰ፤ ንጹሃን እዬተገደሉ ህዝብ አብሮ መኖር እንዴት ይቻለዋል? ቂም በቀልስ እንዴት ሊመክን ይችላል? እንዴት ብዬ በፍቅር ፕሮጀክቴ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ፍቅራዊ ጉዞ ልጻፍ? በውነቱ አቅም አንሶኛል።

ለመሆኑ አሁን አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ እጬጌው አቡነ መርቅርዮስ ወደ መንበራቸው ተመለስዋል አገር ቤት ሊገቡ ነው። ይህ መቼም የሰማይ ታምር ነው። የዘወትር ምኞቴ ነበር። ሐሤት አድርጌለሁኝ። ቀሪ ዘመናቸውን አገር ገብተው ለማህበረ ምዕመኑም ትልቅ እርካታ ነው።

ግን ህይወታቸውስ? እኔ ከሰሞናቱ ብዙም ጥርጣሬ አልነበረኝም፤ ልክ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ስትጀመር ጥርጣሬዬን ሁሉ አውልቄ እንደጣልኩት፤ ስጋቴን እንዳበረርኩት ማለት ነው፤ አሁን ግን ቤተ ክርስትያን አንድ ከሆነች በኋዋላ በሆነ ነገር እሳቸውን የምናጣ ይመስለኛል።

የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አደናቀፋቸው፤ ከመኝታቸው እንዲህ ሆነው ተገኙ የሚል መርዶ እንደሚመጣ አስባለሁኝ። ምክንያቱም በመሃል ያሉ ክፍተቶች መድፈኛቸው ጥንቃቄያቸው እንብዛም ነው። ባለቤት የሌላቸው ጥንቃቄ የሚሹ ክፍተቶች ይታዩኛል …

ከላይ እሰከታች እኮ ማን ነው ያለው በቤተክርስትያኗ አስተዳደር እና አመራር? የሃይማኖት አባቶች እኮ የፓርቲ አባል የሆኑበት ዘመን ነው? እና እኒህን ቅዱስ አባት፤ እኒህን የፈርሃ እግዚብሄር ባለሟል፤ እኒህን ተደብቀው በሱባኤ የኖሩ አባት እኔ እንጃ አሁን ባለው ሁኔታ አምኖ መስደድ የተገባ አይመስለኛም።
እርቁ ይቀጥል። በውጪም በውስጥም በአንድ ሲኖዶስ ይመራ ግን አባታችን አሰልፎ መስጠት ግን በፍጹም ከዚህ ግድያ ማግስት አላስበውም። መሄድ የለባቸውም የሚል አቋም ነው ያለኝ። 

ወክለው ሊልኩ ይችላሉ ግን በዚህ እርጋታ በነሳው የበቀል ማገዶነት ተመቻችቶ መገኘት የተገባ አይደለም። በተለመደው መንገድ ትግራውያን ይምሩት፤ እንሱ ጠበቂ የትግራይ መንግሥት ስለአላቸው።

 የጠ/ ሚር አብይ አህመድ መንገድ የቅባ ስለሆነ ጥሪው የመንፈስ ነው። ግን በዚህ ተጻራሪ የሆነው ወገን ወንጀል እዬሠራ ተደምረሃል፤ ቀጥል ከሆነ ግን እኔ  እርቁ መልካም ነው፤ ግን አባታችን ለዚህ የእርድ መባቻ የደም ግብር ሊሆኑ አይገባም ባይ ነኝ።

ሌሎችም አባቶች ቢሆኑ ወኪሎቻቸውን ልከው የእርቁን ሁኔታ ከማስማማት ባሻገር መሬት ላይ እርግጠኛ ሰላም አለ ብለው ቢሄዱ አብሶ ለጎንደሬዎች አደጋው ሰፊ ነው።

እርግጥ ነው ባህታውያን አገር ክትር መሬት የላቸውም፤ ቤታቸው ሰማያዊ ነው። ነገር ግን እንደ ሰው ስናስበው ባላፈውም ጽፌዋለሁን ዕውቅና ያለው ጎንደሬ ሰላም አለ ብሎ አገር ቤት ለመግባት ማሰብ ዕብንነት ነው ብዬ ነበር። አሁንም እምለው ይሄንኑ ነው።

አይደለም ጎንደሬ ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ መሄዳቸው እኔ አይመቸኝም። እዛው ለሰማያዊ ፓርቲ ሥሙን ሸልመው በከብር አሜሪካን ቢኖሩ ምርጫዬ ነው። በቃ ምን ያደርግላቸዋል? ፖለቲካ ከዚህ በኋዋላ። 

ህይወታቸው ቢኖር ግን ለተከታዮቻቸው ከሁሉ በላይ ለትዳራቸው እና ለቤተሰብ መልካም ዜና ነው። ሳዬው የዶር አብይ አህመድ ቅንነት ብቻውን ይህን የቂም ቁርሾ ከልቶ አብሮነትን የሚያስቀጥል አልሆነም። በዬቀኑ በተደራጀ ሁኔታ መፈናቅል፤ ሞት፤ ቃጠሎ ነው ያለው።

አሁን በደረቅ ወንጀል የታሠሩት ወንጀላቸው ስፋት እና መጠን ተመርምሮ በምህረት ይካለሉ፤ አይካለሉ የሚለው ነገር ጊዜ ይፍልጋል፤ ግን የሚሰማው ቃጠሎ ነው። ትግራይ ላይ ግን ይህም የለም? ግን የትኛው መንግሥት ነው እዬመራ ያለው? እውነተኛው ማዕለዋ መንግሥት አለ ወይንስ የለም? 

ይህ የወንጀል እስረኛ በጅምላ ከእስር ቢለቀቅ መቆጣጠሪያ  ሥርዓቱ ተዘርግቷል ወይ? ትግራይን አይደርስባትም? አይደለም እሱ የጸጥታ አስከባሪው ከአዲሱ የአብይ ካቢኔ ጋር ነው መንፈሱ ወይንስ ከሁለተኛው መንበረ ሰውር መንግሥት ጋር ነው ያለው? ወይንስ የራሱን መንገድ አድብቶ እዬጠበቀ ነው? በጣም ዝንቅንቅ ነገር ነው ያለው።

ደስታን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሁኔታዎች አቅማቸው ምንም ነው። ፍቅር ጠበቂ ያስፈልጋዋል። ፍቅር ሙሉ ጥበቃ ከሌላው ያስጠቃል። አሁን የኢንጂነር ስመኛው ሞት ሆና የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ሞት ታቅዶ በወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ መረብ የተከወነ ነው። የዚህ አብዮት ሥረ መሠረት ማን እንደሆነ፤ ቀጣዩ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋንታ ያውቀዋል። በቀጣይም ጊዜው ሊያጥር ሊረዝም ይችላል አንድ የምሥራች ተጠግቶ ሌላ መርዶ ይኖራል …

በውሃ ብከላ ሊሆን ይችላል፤ በመዳህኒት አሰጣጥ ዝበት ሊሆን ይችላል፤ በመኪና አደጋ ሊሆን ይላል … አይታውቅም … ምክንያቱም ጉዞው ጤፍና ሰናፍጭ ተፈጭተው ፍጭት ላይ ስለሆኑ … አለዬለትም የሃይል አሰላለፉ። እንዳይለይ ያደረጉት ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባዎራዎች ናቸው።

 ነጥለውም፤ አስነጥለውም ማስመታት አይፈልጉም፤ የትግራይ ሊሂቃኑ የሰሞናቱ ጉባኤ ፍሬ ነገሩ ይሄው ነው። ዘመነ ወያኔ እንዴት ይከትማል?
  
እኔ እንደማስበው ነፍስ ያላቸው ዕውቅ ሰዎች ሥሩ ባልታወቀ ማፍያ ቡድን ሄዶ መማገድ ፖለቲካዊ ብልህነት አይደለም። ሁሉም ተራው ሲደርስ ያውቀዋል። ዛሬ ስናገረው ሊመር ይችላል፤ ግን ነገ የሚሆነው ነው … እኔ የምናገረው።  አንድ በአንድ እዬተለቀመ በዚህ ለውጥ ጉልህ ድርሻ ያበረከተ ጎንደሬ ይነቀላል። ስለምን? ይህ ማህበረሰብ ቅን፤ ግን ቅንነቱ እርግማን እንዲሆንበት ዘመነ - ዘመናት ፈርዶበት የኖረ ስለሆነ። አሁን እንኳን በቃህ ያለላው የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንኳን በስንት ደባ ነው እዬቀጠቀጠው ያለው? 

የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊም አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋዋለ ይላል? ይሄ ራሱ ኮሚክ ዜና ነው። ስለምን ሞት በተከታታይ ቀናት በአማራ ሊሂቃን በረከት? ነገስ ቀጣዩ ተረኛ ማን ነው? እሰከመቼ ነው ከንፈር እንዬተመጠጠ በስንት ስቃይ እና መከራ ያለፉ እዚህ የደረሱ የአማራ ሊቃንት እዬተለቀሙ የሚገደሉት?

አሁንም ሌላ ፍርሃት አለብኝ  ከንፍሮ ጥሬ ያወጣቸው አምላክ ብቅ ብቅ በማለት ላይ ያሉ የአማራ ሊሂቃን ጉዳይ? ይሄ የስልጣን ሸግሽግ አማራን ምድረ በዳ በማድረግ ባይታዋር የማድረግ ተልዕኮ ይኖረዋል። እኔ ግን ሹመቱም ሽልማቱም ቀርቶ የአማራ እናት ልጇ በሰላም ውሎ ቢገባላት እንዴት የሰማይ ፍሰሃ በሆነ ነበር። ለሹመት ለሽልማቱ መፈናቀሉም፤ መገደሉም፤ መታረዱም፤ ዘር ጥፋት፤ ህውከት፤ ጥይት፤ ስጋት፤ ፍርሃት፤ ትውር የማይልባት፤ በበአንጻሩ ፌስታ፤ እልልታ፤ ፈንድሻ የሚፍነከነክባት  ለአደይ ትግራግራይ ቢሆን ቅጭጭ አይለኝም፤

እሷ አንገተ እረጅም፤ ክንደ ረጅም ጥቃት የሚያወጣ ኡኡትን ለሌላው ባዕት የሚያከፋፍሉ ልጆች አሏት። ስለዚህ ሹመቱ ቀርቶ ጎመን በጤና ይቅደም ነው ፍሬ ነገሩ።

እራሱ ዜናው አዋሳ፤ መቀሌ፤ ይልና ጎንደር ሲደርስ ምዕራብ ጎንደር ይላል። ጎንደር“ ብሎ ለመጥራት  የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያቅተዋል። ጦርነት ለጎንደር ታውጆባታል። ግን እሷ አላወቀችም ጎንደሬት። አልገባትም ወይንም በዛው በቅንነቷ ውስጥ ለሽ ብላ ተኝታለች።

ዘመኑ የለወጡት ተባለ እና ለማ እና አብይ ተብሎ እርገት ይሆናል። ውስጡ የታመቀ እምል ነገር አለበት። የአማራ ሊሂቃን፤ የአማራን ህዝብ እና መሬትን የመጫን፤ በሥነ - ልቦና የመደቆስ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እየተደረጋባቸው መሆኑን ልብ አላሉትም።

 ስለዚህ ሌላውን ነገር እርግፍ አድርጎ አማራ የራስ ጥበቃን ማጠናከር የተገባ ይመስለኛል። አሁን አባይን ያህል የዓለም የፖለቲካ እንብርት ማህንዲስ ካለ አለ አንድ ጠባቂ ለበለሃስቦች የቁርሾ ማወራራጃ መሸለም? ይገርማል? እንቆቅልሽ የሆኑ ነገሮች አሉበት።

ለዚህ ነው „እኔ ጭንቁ ሌቦች ከእስር ተፈቱ ሳይሆን ለውጡ ሊቀለበስ ይችላል ተብሎ መታሰብ ይገባል“ ብዬ የጻፍኩት። ሁለት መንግሥት ነው ያለው። አንዱ በማሸበር ትግራይ ላይ ኮማንድ ፖስቱ ሲሆን ሌላው በማረገጋት አዲስ አባበ ላይ። በህጋዊ መፈንቅለ መንግሥት ያልተሳካው አሁን በተደራጅ ግን በተናጠላዊ ጥቃት ተጀመሯል።  

ልብ ያላቸው ሰዎች እዬሆነ ያለውን መልካም ነገር በማበረታት ግን እራስን ለማገዶነት አለማቅረብን ልብ ሊሉት ይገባል።

አሁንማ አላፈ ያለችኝ እህቴ ነበረች። ምኑ? ምኑ ነው ያለፈው? ማን ያቀደው ነገር ነው ይህን ነገር ማብረድ የተቻለው? ማን ነው አስፈፃሚው? እኮ ማን? የሚታወቅ ነገር የለውም፤ ውሎ እዬጠፋ ነው? ለዛውም ዶር አብይ አህመድ ሆኑ ዶር ለማ መገርሳ ሥልጡን ባለሙያ ናቸው በድህንነት ዘርፍ። እኔ እንዲያውም ወርቃማ ዘመን ብዬዋለሁኝ። እንደዚህ በደህንነት  ዘርፍ ሥልጡን ባለሙያዎች መንበረ እጬጌነቱን ሲይዙ ደስታዬ ወሰን አልነበረውም። ግን የሆነው ነገር ሁሉ ከመዳፍ የወጡ ነገሮች አዬታዬ ነው።

 ስለምን በደህንነት ዘርፍ ሥልጡን ባለሙያ ሆነው ይህን ሴራ የቅድሚያ ቅድሚያ መልክ ሊያስዙት ሲገባ ማገዶ አማራ እንዲያቀርብ በዬነቡት። አልገባኝም፤ አንዲገባኝም አልፈቅድም።

የነሳጅን አዲሱ ለገስን መለከት ደህነንት ላይ ሹመህ ልብ ጥሎ መቀመጥ ነገም ሌላ የሞት ነጋሪት አለ በይፋ፤ በአደባባይ። ከላይ እስከታች የገዳይ ስኳድን ሳትነካ እንዳለ ይቀጥል ብለህ አይሆንም? ነገ የሚፈነዱ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህዝቡ ሰፊ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ማለት ብቻ ሳይሆን ችግሩን ከሥሩ የሚነቅል ርምጃ በመውሰድ መረቡን ማፈራራስ ይገባ ነበር። 

እጅግ በጣም የዘገዩ ጉዳዮች ራስንም አፍንድተው ሁሉንም እንዳልነበረ የማድረግ ዕድሉ ሰፊ ነው። ባዶ እጁን ያለ ህዝብ ምን ሊያደርግ ይችላል?
ነገ ዛሬ ለውጥ የሚመሩት እንዲህ ካንቀላፉላቸው ልጆቻቸውን፤ ወይንም ሚስቶቻቸውን አፍነው ሁሉ መደራደሪያ ሊያደርጉ ይችላሉ … 

ወያኔ ሃርነት ትግራይን ያለማወቅ ችግር ትናንትም አለብን፤ ዛሬም አልገባን ወደፊትም አይገባንም። … ለትግራይ ህዝብም አይሆንም ይህ ድርጅት። በፍጹም። በቁስ እንጂ በመንፈስ ለተፈጠሩበት ህዝብ ያስባሉ ብዬ አላስብም። ምክንያቱም መንፈሳቸው ሰውኛ ስላለሆነ፤ እንጂ ይሄ ዘመን ከእነሱ በላይ ተጠቃሚ ያደረገው አልነበረም። ከነወንጀላቸው ተሸከሟቸው እኮ ነው የተባለው። ደጉ ህዝብም እሺ አለ፤ ግን ምላሹ ሞት እና በቀል ነው …

… ግፉ ስለከረፋ ጠረናቸው ሁሉ ይጎፍንናል። ይህን ለማስታረቅ ጥረት በሚደረግበት ጊዜ እንዲህ በዬእለቱ አንጀት የሚቆርጥ ነገር እዬሰሩ ህዝቡ የነበረውን ቂም ቁርሾ እንዲያገረሽ ቢያደርጉት ተጎጂው ህዝባቸው ነው። …
በዚህ ሂደት አንድ የከፋው አንዱን ንጹህ የትግራይ ሰው እንዲገድል ሊያደርጉ ቢችሉ፤ እና በዛ ማህል አዲስ አባባ፤ ወይ ጎንደር ላይ  እሳት ቢቀጣጠል እስከ መቼውም ሊበርድ አይችልም።

በዛ ላይ በአሁን የጠ/ ሚር ቦታ የፍቅር መርበብ ደስተኛ የሚሆን ማን ነው? የቀረ የለም እኮ አሁን ሁሉም መንፈሱ አብይ ሆኗል። ዛሬ እዬሳቅኩኝ ቪዲዮዎ ሳይ ነበር፤ መንፈሱን ሲያብጠለጥሉ የነበሩት አብረው ፎቶ ለመነሳት ሲሻሙ፤  … አንድ ቀንጣ ነፍስ ሌላውን፤ የቀደመውን ታዋቂ መንፈሴ ሊለው አልተቻለውም። ስለዚህ አኩራፊው ብዙ ነው …

ገዳይ አቅፍህ፤ ገዳይ ከብክብህ፤ ገዳይ እያስታመመክ እርቅ ሰላም ከባድ ነው። ቢያቆሙ ምንም ነበር ግን እንዲህ እዬሰገረ በ100 ዓመት የማይገኝን ሊሂቅ እያጣህ ይቅርታ እርቀ ሰላም?

በዚህ ሂደት የጥል ግድግዳ መደርመሱ ሌላ የጥል ግድግዳ የሚገነቡ ነቀርሳዊ ጉዞዎችን ተሸክሞ ከሆነ ትርፉም፤ ድካሙም የውርንጫ ድካም ነው፤ ቀጣይነቱም አስተማማኝ አይደለም። ይቀለበሳል።

ምንም እኮ ማስረጃ ማቅረብ አይፈለግም፤ ለሰኔ 16ቱ ፍቅር  ፈንጅ ነው የተሸለመው፤ ለሀምሌ 19 የተዋህዶ እርቀ ሰላም ደግሞ  በሽጉጥ የሚሊዮን ተስፋ ነው ያረረው፤

ለኤርትራው ግንኙነት ግን ሰላም ነበር ሂደቱ ሁሉ የተጠነቀቀው። ይህ የወያኔ ሃርነት ሴራ ስለመሆኑ ምንም ሌላ ማስረጃ ማቅርብ አያሰፍለግም።  ከኤርትራ ጋር ተጨማሪ ቅራኔ መግባት አይፈለግም የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማፍያ ቡድን፤ ሌላው ጋር የሚፈጠረው ግንኙነት ግን ሳቅና ጥቁር ልብስ ይሸለማል። ጨዋታው እንዲህ ነው … ትግራይ መሬት ላይ ግን ያሻውን ባሻው ይከውንበታል።

ባላቅኔው ጠ/ ሚር በሃዘን ድባብ እርቅን ይገነባሉ፤ እነሱ ደግሞ ጥቁር ገበርዲን ለሃዘኑ አስፍተው፤ ቀይ ከረባት ለሳቁ ይሸልማሉ። የየአብይ መንፈስ …. ስልት እና ስትራቴጂው እዬታቀደመ ነው፤ እዬተሸራረፈም ነው።

ሽንፈቱ ሁሉን ውጦ አማድ ከማድረጉ በፊት ግን አንድ ሊባል ይገባል። ልጆች በዬጊዜው ወላጆቻችን ማጣት የለባቸውም እና … ፍጥነት በመጨመር፤ ትኩረት በእርምጃ ማቀናበር ካልተቻለ አዲስ አባባ ወዬልሽ ነው፧ በህርዳርም እንዲሁ።   
ይሄን መስል የእርምጃ አውሳሰድ ደተኛነት ሂደት የለማን ቡድን በእጅጉ ያሰጣል። የጥበቃውን ሚዛናዊነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል። 

የደህንነቱን እቅም ይመዝናል የኦህዴድን። እስከ ዛሬ ድረስ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነበር የሚወቀሰው፤ አሁን ግን ሥልጣን ላይ ያለው ኦህዴድ ነው እና ሁሉንም የመመከት አቅም ሊኖረው ይገባል።

ብሄራዊ ሃላፊነት በደህንነቱ ዘርፍም ሊሆን ይገባል። ህዝብ አስተማማኝ ደህንነተ ሊኖረው ይገባል። አሁን ት/ ቤት ስሌለ ነው እንጂ ማንም ልጁን  አምኖ ት/ ቤት አይልክም ነበር። ተመስገን የሚያሰኘው ት/ ቤት መዘጋቱ ነው። 

አንድ ብልህ የዩንቨርስቲ መምህር ሲነግረኝ በቅንጅት ጊዜ፤ ቅንጅት አሸንፎ አዲስ አባባን ተረክቦ ቢሆን አዲስ አበባን ጥበቃ አልባ አድርጎ የሽፍቶች መናህሪያ የማድረግ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ንድፍ እንደ ነበር አጫውቶኛል። አሁን እዬሆነ ያለው ይሄው ነው። ይህ እዬገነነ ከሄደ አፍሪካንም የሚያውክ ይሆናል።
  • ·       ነገረ አማራ እንደ መከወኛ።

 ይህ ዘመኑ ጤፍ እና ሰናፍጭ ተፈጭተው ሲፋጩ ይታዬኛል። በትግሉ ውስጥ የገቡት በመንፈስ ማለቴ ነው፤ ገናም ተጋድሎውን እንቀላቀላለን በመንፈስ የሚሉት፤ ለመቁረጥ ተስኗቸው በይደር ለቀጠሩት፤ አያስፈልግም የአማራነት ተጋድሎ ባዮች ጋር ሁኔታዎች በተደሞ ሲመረመሩ አማራ በልተደራጀ አህታዊ የመንፈስ አንድነት በአገረሸ መከራ መጪውን ዘመን እንዲጋፈጥ ግድ ይለዋል። ተጨማሪ ቤተ ሙከራ ላይ ነው አማራ። 

አማራ እፎይ የሚልበት ዘመን ገና መሆኑን ያመለክታል የሰሞናቱ ጠቅላላ ሂደቶች። ዜናዎችን በሙሉ ጊዜ ወስዳችሁ መርምሯቸው።

ከአማራ ቀጥሎ ያለው ተጠቂ የማይቀርለት ደግሞ ተረኛ ኦሮሞ ይሆናል። ዛሬ አይታዬውም። የአማራ ዘር ሲነቀል ለእሱ የሚደርስ አልመሰለውም ነበር። እኔ በ2013 ጽፌው ነበር። አሁን በቀን 600 ከመቅበር 700 ሺህ በላይ ኑሮን ማጣት ተከሰተ። 

አሁን ባለው ማዕከላዊ የሥልጣን ብረት መዝጊያነት ያሉ ሊመስላቸው ይችላሉ፤ ዛሬ አይመስልም፤ ሊመስልም አይችልም የቦታ ሽግሽግ ስላለ፤ ግን ለነገ የቂም ማወራራጃ መሆኑ አይቀሬ መሆኑን አውቆ የቲም ለማ ቡድን በሥልጣኑ ማዕከላዊ የጥበቃ አውታር ውስጥ ለአማራ ተጋድሎ  ሰፊ አትኩሮት ልዩ ጥበቃ ማድረግ ያለበት ይመስለኛል።

አማራ ያልሆኑ፤ ሊሆኑም የማይፍቀዱም አማራዎችም ቢሆንም ግን ዕዳውን መሸከማቸው አይቀሬ ነው። እዬታደኑ ይለቀማሉ። በፊት በጅምላ ነው፤ አሁን እንደዛ አይደለም። ሞቶ ተገኜ ዕለታዊ ዜና ማሟቂያ ይሆናል። ግዴታ ያለበት ታሪካዊ ድርሻውን የተወጣው ኦህዴድ ነውና ባሊህ ሊለው ይገባል … ሲበዛ „ማርም ይመራል“ እና …

ጉዞው መልካም ነው ትግሬ የሆነ ሁሉ በዳይ አይደለም ነው፤ ግን ይህ ይቀጥላል ወይ? ፈጣሪ ይወቀው በሞት ላይ ቂምን ረስቶ በቀልን አልሰማህም ብሎ የሚቀጥል ነፍስ የሰማይ መላዕክትም ቢሆን አይችለውም። መላዕክት ቁጡ ናቸው።

አንድ ነገር አጠንክሬ ልናገር? ልድገመው የፈለገ ምቹ አዬር ይኑር ቅድስት ቤተክረስትያናችን በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ትመራ፤ ከሁሉም ሳልሆን ቤተ ቁጭ ያልኩትም ለዚህ ነው፤ ግን የብጹዑ ወቅዱስ አባታችን የአቡነ መርቆርዮስ እና የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ መግባት ነፍሳቸውን ለበለሃሰብ መሰጠት ነው … 

አሁን ስለ ግንቦት 7 ሳነሳ ግር የሚላችሁ ወገኖቼ ልትኖሩ ትችላላችሁ፤ ድርጅቱን እምተቸው ፖለቲካዊ አወቃቀሩን፤ ስልት እና ስትራቴጂውን፤ አፈጸጻሙን ስስነት እንጂ የሊሂቃኑ ህይወት ግን ጥብቅ አጀንዳዬ ነው።

አሁን ያለው ሁኔታ አስተርጓሚ አያስፈልገውም … ከዚህ በላይ ራዲዮሊጂ የለም። …. ስለምን በዚህ ሁኔታ ላይ ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ጥበቃ ሳይኖር ቀረ? ስለምንስ የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ሞት አሜሪካ እንዲሆን ታቀደ - ተፈለገ?

የአማራ ሊሂቃን ሞታቸው በቅድም ተከተል ስለምን ተደረጀ? ማን አደራጃው? ነገስ ተረኛው ማን ነው? የትግራይ ንጹሃን ነፍስ ቀጣይ ህይወት እንዴት ይሆናል? የጤፍ እና የሰናፍጭ ፍጭት ፍጥጫ ነው።  

ይቅርታ መንግሥት በይፋ ጠይቋል፤ በይቅርታው ላይ ግን የግድያ እንቅርቱ ቀጥሏል … ይሄው ነው ለዛሬው …

ማን ገባ አሜሪካን ኢንባሲ? ማን አልገባም? ምን ተጋበዘ? የትኛው ከያኒ እኔን ያገናኛኛል? በማን ምልጃ?  ማን መድረክ ይምራ? ማን አይመራ? ማን ቅርበኛ ሆነ የዲሱ ጉግስ ነው።

 የእኔ ደግሞ የህዝቤ የቀጣይ ህልውና ጉዳይ ነው … ለተባጀበት ከልጅነት እስከ እውቀት ለተኖረበት ማይክ፤ ዝናና ስም አጀንዳዬ ሆኖ እምወድቅበት እምነሳበት ጊዜ የለኝም፤ ትልቁ ጉዳይ የተዋህዶ ነበር እሱ እንደሚሆን ሆኖ ተሳክቷል፤ አረረም መረረም … ከአንጀት ደረስም አልደረሰም። ኤንም ቢንም ሲንም እንዳይከፋው ሆኖ እና ተኋሁኖ።

ለእኔ ቁምነገሬ ትልቁ ነገር አማራ ነፍሱ እንዴት በባዕቱ ይቀጥል ነው … ይህ ሊሆን ይገባል ትውልዳዊ ድርሻችን ለቅኖች። አማራም ሰው ነው ከእሳር ከእንጨት ከቅጠል አልተፈጠረንም ሰው ነን። እኩል ጥበቃ፤ እኩል አክብሮት፤ እኩል አውቅና ሊሰጠው ይገባል ለዚህ ባለውለታ ማህበረሰብ። 

ፈጣሪ ሆይ! ፍትህን ቀን ስጣት እባክንህን? አቤቱ ተለመነን!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።