የበቀል ሞት!
· ፎሪን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ሰብዕና አላወቀውም ወይንም አላጠናውም። „ ከአፌ ቃል ፈቀቅ አትበል።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፭) ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላድን።) መነሻ። ስለፎሪ https://www.youtube.com/watch?v=Qrd5D12Z8hw awaze news ን ካነሳሁኝ ፎሪን ለአማራ ተጋድሎ የሰጠው ዕውቅና እና ክብር እጅግ አስደስቶኛል። በቃ „የነፃነት ሃይሉ“ የፉከራ እና የቀረርቶ ሞገድ ተንሳፎ የብል ራት ሆኖ ቀረልኝ። ተመስገን! ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን … ዛሬ ጥዋት አዋዜን አዳመጥኩት፤ እናም ይህን መልስ ከስሩ ለጠፍኩኝ። ምን አልባት ታዳሚዎቼ ካለነበባችሁት፤ ካላገኛችሁት ብዬ በድጋሜ ብሎጌ ላይ መለጠፍ ግድ አለኝ። በዚህ የዓለም አቀፉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ትንተና ላይ ከግላዊ ስሜት በፍጹም ሁኔታ የራቁ ግን የነጠሩ እና የበለጡ እጅግ ብልህ የሆኖ የኢትዮጵያን ፖለቲካው መንፈስ በውል የመረመሩ ጉዳዮች ተነስተዋል። ጋዜጠኛ እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ከስሜት ርቆ ግን ፋክቶችን ፈልፍሎ አቅጣጫ ማመላከት፤ ቅን ጉዳዮች የበለጠ እንዲበረታቱ መሠረት ያለው ተግባር መከወን። እንጂ የራስን ስሜት በሚገፋ ስጋውን እንደተነሳ ውሻ የህዝብን መንፈስ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚመሩ ጫሪ ፤ ቆስቋሽ መንፈሶችን እያነካኩ ማቆሳሰል አይደለም። ከሁሉ በላይ አሁን ያለንበት ዘመን መሪ ያለበት ዘመን ነው። መሪ ነኝ ለሚለውም ተፎካካሪ ፓርቲ ሁሉ መሪ አልባ ሆኖ የኖረበት ረግረጋማ ጨቀጨቆች ተወግደው ጥርት ያለ ብሩህ የስውኛ መስመር የተዘረጋበት ነው … በተለመደው ዙረህ እቀፈኝ የመገዳ...