ልጥፎች

የአማራ ቀን በጎንደር …

ምስል
የአማራ ቀን በጎንደር … https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92836#respond የአማራ ተጋድሎ የተጀመረበትን ቀን በማስመልከት ኮል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ጎንደር ላይ ያደረገው ምርጥ ንግግር የኔዎቹ ቅኖቹ ዘሃበሻ እጅግ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁኝ። እንኳን ደስ አለን ያን ያህል መከራ አልፎ ዛሬ ይህን ቀን ለማዬት አበቃን። በቃ የደስታ ቀን። ጧፍ በርቷል። አማራ እንኳን ደስ አለህ። እኔ ለጎጃም የተለዬ መንፈስ ስላለኝ ጎጃም እንኳን ደስ አለህ። ዕንባዬን መቆጣጠር ስላልቻልኩ ከዚህ በላይ መጻፍ አልቻልኩም። አገልጋያችሁ ሥርጉትሻ።

ሐምሌ አምስት የአማራ ተጋድሎ ቅዱሱ ቀን!

ምስል
ገናናው የአማራ ተጋድሎ የጎንደር ጎጃም አብዮት በሁለገብ ትጋቱ በአጭር ጊዜ ለድል የበቃ ክህሎቱ ስለትንግርት ነው። „ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።“ (መፅሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 12.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        መነ ሻ። ሐምሌ አምስት አቦዬ ናቸው አነባበሮ የሚዘጋጅበት። አነባባሮ በኑግ አና በተልባ የሚዘጋጅ ነው። እንደ እሙሃይ ቂጣ ወይንም እንደ ዳቤ ያለ። አቦዬ ከጎነደር ለተማ በርቀት ስለሚገኙ ጉዞው አድካሚ ነው። ስንመለስ ግን ከትንሿ ገብያ ጉዝጓዟን ገዛዝትን ጠበላችን ይዘን ስነገባ ቤቱ ደግሞ እልባብ ባልባብ ሆነ ይጠብቅናል። ያው የሐዋርያት ፆምም መፍቻ ነው። አንድ ሐምሌ አቦ ግን ሌላ ፈተና፤ ፈተናውም ታምር ይዞ መጣ ያም እንዲህ ሆነ። ዘመናይነት።  ሰሞኑን የአቶ አባይ ወልዱ ባለቤት በአውስትራልያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አንባሳደር ወ/ሮ ትርፏ ኪዳነማርያም ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ ቃለ ምልልስ ከSBS አድርገዋል። ለውጥ ስለ አመጣው ሃይል የተለመደውን ቧልታቸውን አስደምጠውናል። ለውጡ በኦሮሞ ንቅናቄ ብቻ እንደመጣ አድርገው ነበር ያቀረቡት። እንደ መልካም መግለጫም ታይቶላቸው በዬቦታው ተለጥፎላቸው አይቸዋለሁኝ። ይሄ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ጭቆናም ነው።  ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለማትረፍም ሆነ ሥልጣናቸውን ሊያቆይላቸው ይችላል። በዚህ ቦታ ተቀምጦ ከእውነት ጋር ተጣልቶ ከእውነት ጋር ተፋልሶ፤ ከእውነት ጋር ተቃቅሮ ግን ከሆነ ነፍስን የመፋረዳት እዮር አለ።  ቦታው እራሱ የህሊናን ስልጡነንት ይጠይቃል። እሳቸው የኢትዮጵያ ተወካይ እንጂ የባለቤታቸውን ሴራ ሸፋኝ እንዲሆኑ አልነበረም ይህ ታማኝት የ100ሚሊዮን ነፍስን እ

የቀራንዮ መባጃ በትንሳኤ መባቻ!

ምስል
የሦስት ሺህ ዘመን አረንቋ በ100 ቀናት የተሻገረው የቀራንዮ መባጃ ሰውን ያበጀ New Era። አለዛሯ ኢትዮጵያ መድህኗን አግኝታለች። „ልጄ ሆይ ቃሌን ብትቀበል ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት ጆሮህን ጥበብን       እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፤ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“  (ምሳሌ ምዕራፍ 2 ቁጥር  1 ) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 12.07.2018 (ከገዳማዊት ሲዊዘርላንድ)    v  „ቃል።“ የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ነው። ቃልን የፈጠረ እሱ ነው። ሥጋ እና ደምን አርግቶ ሰውን የፈጠረም እሱ ነው። ትወልድን የፈጠረ እሱ ነው። አገራትን፤ አህጉራትን የመሠረተ እና ያስመሰረተም እሱ ነው። ውቅያኖስን ወንዞችን፤ ተራራ ጋራ ሸንተረሮችን መስክ መሬት ምህዋርን ነፍስን በሙሉ የፈጠረ እሱ ነው። የልዑል እግዚአብሄር ቃለ ምህዳን መሬት ላይ ወርዶ የሃጢትን መርገምት ጥሶ ሰንሰለቱን በጣጥሶ ትንሳኤን ያሳወጀው እሱ ነው።   v  ውልደት። የሰው ልጅ ሲወለድ ንጹህ ህሊናን ይዞ ነው የሚወለደው። ያረጋው ደም ረግቶ ሰዋዊ ተፈጥሮ ይዞ ወደዚህች ምድር ሲመጣ ያለቅሳል፤ ያን የጸጥታ እና የአብሮነት፤ ያን የፍስሃ እና የሰናይ፤ ያን የንፅህና እና የፍቅርን ባዕቱን ትቶ ሲወጣ የሚገርፈው ወጀብ እንዳለ፤ የሚቀቅለው የክፉ ነገር ገሃነም እንደሚኖር፤ የሚያናውጠው ማዕበል እንዳለ፤ የሚቆምባት መሬት ድውያን ቋያ እንደምትሆንበት፤ የሚጠጋው እሾህ የጠናበት ስለመሆኑ፤ የቀኗ ብርሃን የሚግርዱ የሴራ ድሮች እንደሚፈትኑት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ምርር ብሎ ያለቀሳል። ይህቺ ምድር ታስለቅሳለች ከውኑ ላለ መንፈስ። ሁሉ ነገር አላት ግን ላላት ነገር ብቁ አይደለችም። ይህቺ ዓለም ሲመጡባትም - ሲኖሩባትም ሲሄዱባትም ታ

ሁለተኛው ምዕራፍ የኳስ ዊድንግ ሻውር ... በመስኮ።

ምስል
124 ደቂቃ በመስኮ „በችሎቱ አምስግኑት በታላቅነቱ አመስግኑት።“  (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፶ ቊጥር ፪) ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) 90 ደቂቃ አልበቃኝም አለች። ናፈቀችው የኮራን ድልቃ እናም እሲከ በቃት ድረስ ተደቃች፤ ተሰለቀ፤ች ታሸች፤ ተሸከረከረች፤ ዳናሰች እስክሰክታውንም አስነካቸው….   ሁለተኛ ምዕራፏን ዊድንግ ሻውሯን ከኮራ ጋር አሳምራ ከውና ኮከቤ ለኮራ አሰኝቶኛል ስትል ወሰናች እቴዋ ድንቡልቡሊት ለዋንጫ ከመረጠቸው ጋር ከፈንሳይ አገር ሰንበት እንገናኝ ብላለች። ኮራዝድንገቴ ናቸው። እንደ ሽምቅ ተዋጊ አደጋ መጣል ይችላሉ። የሰውነት አቋማቸው ጠንካራ ነው። እንዳልኩት ኮራ ለዋንጫ ውድድር ከፈራንሳይ ጋር ይጋጠማሉ ብዬም ነበር ትናነትና። ባለፈው ሳምንት መሸኛ ላይ የጨዋታ ጊዜ ተራዝሞ ያም አልሆን ብሎ በፔናሊቲ ነበር ኮራ ራሺያን በባዕቱ ስደት ልኮ ነው ለዛሬ ቀን የበቃው …. እንግሊዞች በጥዋቱ ቀንቷቸው ነበረ። ብዙ ጊዜ ነፃ ምት ክርስቴኖ ሮናልዱ ነበር ለግብ የሚበቃው፤ ዛሬ እንግሊዞችን ቀንቷቸው የመጀመሪያ ግባቸውን አገኙ። በጥዋቱ ነበር ደስታ እንኳን ደህና መጣችሁ ያላቸው። ኮራ ትንሽ ግፊያ አብዝተው ነበር የቆዩት በሰጨኝ ብለው። የሆነ ሆኖ 68ኛው ደቂቃ ላይ ቀናቸው እና ቀጥለው ተፋልመው 90ው ደቂቃ በእኩል ነጥብ ጨዋታው ተራዘም። ጎሏ አገባቧ የነፍስ ያህል ነበረች። ወርቅ ነበረች። መጨረሻ ከሁለተኛ እረፍት መልስ ኮራ አቅሙ አጣናክሮ በትጋት እና በተከታታይ የማጥቃት ጥበብ ጥረቱ ተሳክቶ 109 ዲቂቃ ላይ ለስኬት በቃ።  ስለሆነም እንግሊዝን 2 ለ 1 በመሸኝት ለዋንጫ ከፈርንሳይ ጋር   የመጨረሻው ጨዋታ ይኖረዋል። ጨዋታን ከአሸነፈ የመጀመሪያው ዋንጫ ነ

መሆን ይቅደም!

ምስል
ህልምህን ስታገኘው በህልምህ ውስጥ ለመኖር ፍቀድ። „አስተዋይ መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭) ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) ·        ጠብታ። የሚገርሙኝ ነገሮች እጀግ በራካታ ናቸው ዛሬ ጥዋት ዩቱብ ያቀረብልኝ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኛው የአቶ አለምነህ ዋሴ ዶር ለማ መgርሳ ለጨፌ ኦሮምያ ጉባኤ ያደረጉትን ንግግር መሰረት ያደረገ ነበር። „የያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር“ ነው እንዲሉ ያገኘነውን ወርቅ አያያዝ እንወቅበት የሚል ሁለንትና ዕድምታ አለው። እኔ ደግሞ የቀደመውን ብሂል ገልበጥ ላድርግ እና የያዙት ወርቅ ከመዳብ ሳይሆን ከብረትም አንሷል ባይ ነኝ። አዎን ዘመናይነቱ፤ ቅልጣኑ፤ የኬክ ቁረሱልኝ አቃቂሩ ስለሚያቅለሸልሸኝ። የትም ዓለም በዚህ በ100 ቀን ታይቶ የማያውቀውን ትንግርት ነው አላዛሯ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለችው፤ ዕውን አላዛሯ ኢትዮጵያ ናት ይህን ሁሉ የተግባር ዕንቁ በመሰብሳብ ላይ ያላቸው ያሰኛል? እኔ የጠበቅኩት ነው። ከመጀመሪያውም ጀምሬ የተጋሁበት ነው። እንዲያውም ይህ በግራ በቀኝ ውጥረት እና የሰላም ህውከት እዬተዋከበ የተከወነ ሲሆን የተረጋጋ ሁኔታ ቢገጥመው ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስበው እራሱ ደረጃም፤ ልክም ለማውጣት ይቸግረኛል። ህውከቱን የወያኔ ሃርነት ትግራይ በፊታውራሪነት ያልታደለ በሉትና፤ ሌሎቹ ደግሞ የቤተመንግሥቱ ወንበር ቀረብን ያሉ ናቸው። ለውጡን ሊደግፉ ሲገባ ለውጡ ተቀልብሶ ለእነሱ የቀይ ምንጣፍ አሸሼ ገዳሜ እንዲውል ነበር ያለሙት። መከራው ይሄው ነበር። ቢሰጣቸው እኮ ለግማሽ ቀን አይችሉትም። ምክንያቱም ትንፋሻቸው ያጠረ፤ ዓይናቸው የጠበበ፤ ትእግስት ያልፈጠራላቸው፤ ሃሳብ ማፍለቅ እርማቸው የሆነ ስለሆኑ …