ልጥፎች

ከጃንዋሪ 2, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ነገረ ዛለአንበሳ፤ ነገረ አልበሽር እና ዕድምታው

ምስል
ነገረ የዛለአንበሳ         እና       ዕድምታው እንደ ሥርጉተ ዕይታ። „ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።“ መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.01.2019 ከእማ ዝምታ - ተሲዊዝ ። ·        እንደ መግቢያ። እንዴት አላችሁልኝ ቅኖቹ። ዝምታው ቀጥሏል። እሰከ ረፋዱ ድረስ የመኪና ጩኸት እንኳን አልሰማሁም። ኳኳ - ኳኳ  አደረኩኝ - በቀስታ፤ ደወሉን አልጫንም። በእጄ ነው እማንኳኳው። ጉዳዬ ለጎረቤቶቼ አላችሁን ልል ነው እገረ መንገዴንም እንኳን አደረሳችሁ ልል? „አለን ደህና ነሽ ግቢ“ አሉኝ። ልጆች አሉን ስል ቀጥዬ ጠዬቅሁኝ። እነሱ ረበሹሽ ይሉኛል እዬተሳቀቁ እኔ ደግሞ የቤተ ክርስትያን ማህሌት የመስማት ያህል ደስ ይለኛል ልጆች ሲጫወቱ ሳዳመጥ። ልጆቼ ናቸው አትሳቀቀሙ እላቸዋለሁኝ - አዘውትሬ። ጥያቄዬ ቀጠለ ትላንት ነበራችሁ? „ቤት ውስጥ ነበርን። ምናው አንኳኩተሽ ነበርን፤ አልሰማነሽም አሉኝ“ ሲሉ ጠዬቁኝ። ቀልጠፍ ብዬ አላንኳኳሁም ድምፃችሁ ስለጠፋብኝ ነው። „የስልክ ደወል እንኳን አለሰማሁም አልኳቸው።“ የእማ ዝምታ ነገር ሰውንም አደበኛ ነው እምታደርገው አብሶ እንዲህ የዓውዳ ዓመት ሰሞናት ጭር ነው። ዝጉም ሁለት ቀን። ዛሬም ጥር 2 ቀን 2019 ነው ሥራ የለም በገዳማዊቷ ሰፈር ከሆስፒታል እና ከድንገተኛ ክሊንኮች በሰተቀር ሱቁ ሁሉ ዝግ ነው።  ·        ጉዳይ - ለማዕልቲ። ዛሬ እንደ ጉዳይ እማነሳ...