የሰኔ 16ቱ 2010 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ክሽፈት።
የሰኔ 16ቱ የ2010 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ክሽፈት እና ቀጣይ ዕጣ። ከሥርጉተ © ሥላሴ 27.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „እኔ በእድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁኝ።“ (መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፪ በቁጥር ፮) · እፍታ። ብዙ ሰው በጠ/ሚር አሜኑ አብይ አህመድ ላይ ብቻ የተቃጣ ጥቃት አድርጎ ነው የሚገምተው። አብረዋቸው የነበሩትን የካቢኔ አባላትን ሳይ እኔ በጣም የሚቀርቧቸው ከሳቸው ጋር ለመስራት ሙሉ ፈቃደኛ የሆኑትንም በአንድ ላይ ለመፍጀት እንደ ታሰበ ነው የሚገባኝ። መቼም ከጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህምድ ጋር ለመሥራት ትልቁ መሥፈርት ሌት እና ቀን እንደብረት መትጋት የግድ ይላል። ይህን በቀደመው ጊዜ በሚገባ አብራርቼ ጽፌዋለሁኝ። ሰውዬው ሰርተው የሚደክሙ አይደሉም። የጸሐይ ጉልበት ያላቸው ጉደኛ ፍጥረት ናቸው። ይህን ፈቅደው በሚተጉት ላይም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከአቅሙ እና ከቁጥጥሩ ውጪ በላይ መሆኑ እረፍት አይሰጠውም። የትኞችንም አይፈልጋቸውም። · ጥ ራት ፍጥነት ብቃት በሙሉዑነት። ገራሚው ነገር የሥራቸው ጥራት እና ብቃት ፍጥነት ስኬት በድምሩ ሲታይ ደግሞ Quality የሚባል ዓይነት ነው። የረገጡት ሁሉ ለምለም ነው። የነኩት ሁሉም የተሳካ ነው። የአሮን በትር እንደሚባለው። ይህ ደግሞ የዛሬ አይደለም። በተገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ የተሰካ ውጤትን የሚያስመዘግቡ ናቸው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች አሉ፤ ተራራን ንደው ለጥ ያለ ምቹ አስፓልት ለ...