ሲዊዝ የእኔ ልዕልት ለቀጣይም አዶናይ ይርዳሽ! ይቅናሽ!
ዛሬም ደጓ ሲዊዝ ለቀጣዩ ጨዋታ አልፋለች። ተመስገን!
ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.06.2018 (ከድንግሏ ሲዊዝ)
„ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል“ (መጸሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፰ ቁጥር)
ዛሬ የሲዊዝሻ ቀን መልካም ቢሆንም መጨረሻው ላይ ድራማ ነበረው። ሲዊዝ ለሰውኛ ደግንቷ ወደር እና አቻ የላትም። ሲዊዝ ቢኖራትም ባይኖራትም፤ ቢከፋትም ደስ ቢላትም ሁሉንም በልክ የማያዝ አቅም ያላት አገር ናት። ቻይ እና ሲበዛ ቁጥብ ናት። ሲዊዝ የመልካምነቷ ደረጃ ልታይ ልታይ በማለት ሳይሆን መልካምነቷ፤ ቸርነቷ፤ ርህርህናዋ ተከድኖ ነው።
ሲዊዝ ያሉ የሃይማኖት ድርጅቶች ሰው መርዳት ብቻ ነው መርኽቸው። ሃይማኖት፤ ቀለም፤ የዕወቀት ደረጃ አገር ቦታ የላቸውም። አሁን የካቶሊክ እና የፕሮቴስታት ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ቡድሃንም እስልምናንም ኦርቶዶክስንም ፕሮቴስታንትንም ካቶሊክንም አማኝ የሆነ ሰው ሲረዱ ምንም ሳይዛነፍ ለሁሉም በእኩልነት ነው። ይሄ እጅግ የሚደንቀኝ ተፈጠሯቸው ነው። ፈርሃ እግዚአብሄር ደረጃው በላቀ ሁኔታ ያለባት አገር ናት።
ሲዊዝ ውስጥ ተንጠራርቶ የሚሄድ ዲታ የለም። ዝቅ ነው። ሲዊዝ ውስጥ ለሚኖር ማንኛውም ስደተኛ በዬዕለቱ መደበኛ የሰብዕና ትምህርት ቤት ተከፍቶለታል ሳይከፍል። ደስታን በልክ መያዝን። ኑሮን ብልክ ማድረግ። ሲዊዝ ኑሮው እጅግ በጣም ከባድም ቢሆን እንደ አመላችን ከእናትም በላይ በሆነ ሁኔታ እኩል የምትይዝ አገር ናት። ከሰው ደጅ የሚያደርስ ምንም ነገር የለም።
ሌላው የሚገርመኝ ሰብዕና የፈለገ ቢሆን መንገድ ላይ ጠብ ተፈጥሮ ቢዩ የሚያሳዩት የእርጋታ ሁኔታ ይደንቀኛል። ጥልቅ የለም። ያላዩ ነው የሚመስሉት። የገለልተኝነት መርኽቸው ደማቸው ይመስለኛል። ስለ በዳይ ሰው ሲነገር አንኳን በቀስታ ነው የሚያዳምጡት እንጂ በደሉን አያሟሙቁትም።
ሲዊዝ ውስጥ የገባ ስደተኛ ከገባበት ደቂቃ ጀምሮ የጤና እንሹራንስ በነፈስ ወከፍ አለው። ሲዊዝ ዳገቱ መከራ የሚሆነው የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘቱ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ እጅግ የረጅም ጊዜ ቆይታ መኖሩ ነው። በማሃል ወጣትነትም፤ ጤናም ሁሉም ነው የሚያመልጠው፤ አሁን አሁን የተሻለ ሁኔታ ያለ ይመስለኛል አብሶ ለኤርትራኖች። ከእነሱ ለሚጠጉትም ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰላዮችም።
የሆነ ሆኖ ሲዊዝ ከሁሉም የሚመርከው የሞራሏ ልዕልና ነው። ቀስ - ዝግ - ሰከን - ረጋ ያለች አገር ናት ሲዊዝ። ሲዊዝ ቅድስት ናት። እህቴ እንዳለቻት ገዳማዊ አገር ናት። መቼም ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ያህል ነው የሚሰማኝ። ድምጽ የበዛበት ቦታ ለእኔ እእ ስለሆነ። ክድን ብሎ፤ ሽሽግ፤ ክውን ብሎ መቀመጠም ግጥሜ ስለሆነ።
ዛሬ ሲወዚሻ ከኮስተሪካ ጋር ጠንከር ያለ ፉክክር ላይ ነበረች። ከምድቧ ከብራዚል ለጥቃ ሁለተኛ ደረጃ ነው ያለችው። እኔ በዬዓመቱ በጨዋታቸው ብዙም አልረካም። ምክንያቱም ስለምን ታነሳላች ሲዊዛ በሚል እንደ ሌሎች አገር ተጨዋቾች ሁሉ እኩል ስለሚደረግላቸው ስለምን ጥንካሬ ያንሳቸዋል ስለምል።„የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንደሚለው ልብ አምላክ ዳዊት። እናቴ ወለጄ ት/ ቤት ሁለተኛ ከወጣሁኝ አንደኛ ለወጣው የተለዬ ትምህርት አልተሰጠውም አንቺ አብረሽ ቁጭ ብለሽ ተመረሽ እንዴት ሊበልጥሽ ቻለ ትለኝ ነበር። ሲዊዝም አውሮፓ እንዳሉ አገሮች ተጨዋቾቿ ሙሉ የሆነ አያያዝ እያላቸው ስለምን አንሰው ይገኛሉ ነው የእኔ ዕይታ የነበረው። ዘንድሮ ግን ደስተኛ ነኝ።
ዛሬ የምወድሽ ልክ 30.30 ላይ በኮስቲ ላይ አንድ ግብ አስቆጥራለች ገዳማዊቷ አገር ሲዊዝ። እንደተ ለመደው ነው ዛሬም ያው ፈንደቅኩኝ። ስለምን? የኮስቲ ጎል ጠበቂ እጅግ ጠንካራ ከሚባሉት ከጀርመኑ፤ ከጣሊያኑ አሁን አሁን ደግሞ አብሶ ከ2014 የዓለም እግር ኳስ ወዲህ ያልተወቀበት ግን ልብ አንጠልጣይ ቡድን ከሆነው የቤልጀሙ ጎል ጠበቂን ፈርጣማ ክንድ አልፎ ኳስ ከመረብ ጋር ማገናኘት ከድንቅ በላይ ነው።
በነገራችን ላይ ቤልጀም እጅግ የሚገርም ቡድን ነው አቅሙ ጠንካራ ነው። ግን ብዙም ሰው አጉልቶ አይናገረው እንጂ ጥንካሬው የግለሰቦች ሳይሆን የቲም የሚባል ነው ልክ እንደ ኦህዴድ። ጠይም ዕንቁዎችም በርከት ይሉበታል። ሲዊዝም አሏት ጠይቅም ዕንቁዎች።
የሆነ ሆኖ በዛሬው ጨዋታ 87 ደቂቃ ላይ ሁለተኛው ግብ ሲዊዛ አስቆጠረች። በዛው ቅጽበት ኮሰተሪካ የፔናሊት ዕድል የሚመስል ነገረ ነበራቸው። ዘንድሮ ደግነቱ ማረጋጋጫ ሞኒተር ስላለ ሲዊዝሻ የመጀመሪያው ፕናሊቲ ቢያልፋትም ሁለተኛውን ቅጽበታዊ ሁኔታ ጋር ግን ከፔናሊቲ ልታመልጥ አልቻለችም።
ሌላ ፔናሊቲ አደጋ ላይ ጎል ጠባቂያዋ ያን ሶመር ገጠመው እና ባለቀ ደቂቃ ኮስቲ ሁለተኛ የግብ ዕድል አገኝታ እኩል ለኩል 2 በ 2 በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።
እኔ እንደማስበው የሲዊዝ 11 ቁጥር በጣም መጋፋት ያበዛል። በቀይ አለመውጣቱም በቸርነቱ ነው። ለሲዊዝ ግፊያ አያምርባትም። እርግጥ እሱም አንዱ የጠይም ዕንቁ ቤተኛ ነው። አዲስም ነው …
አሁን ጸጥ ብላለች ሲዊዝ የመኪና ጡረንባ እንብዛም ነው፤ አልፎ አልፎ ነው እያደመጥኩ ያለሁት፤ ምንአልባት ነገ የሥራ ቀን ስለሆነ ሰዓቱም 22.00 ስለሆነ ህጻናት ላለመረበሸም ሊሆን ይችላል። ከ22.00 ሰዓት በኋዋላ ኮሽ የለም በኮሽ አይሏ መንደር ።
ባለፉት የሁለት ዘመን ውድድሮች የ2010 የደቡብ አፍረካው ደከም ያለ ነበር፤ እርግጥ ነው ለዋንጫ ከበቃው የስፔን ቡድን ጋር በነበራት ጨዋታ እንድ ጎል አስቆጠር እንደ ብርቅ ነበር የታዬላት፤ የ2014 የብራዚሉ ጨዋታ ደግሞ የተሻለ የሚባል ነበር። ዘንድሮ ግን እኔ በእጅጉ የተለወጠ አቅም ነው ያዬሁት። እና የዛሬው እድል ለእኔ ከሰማይ የወረደ ነው የመሰለኝ። እጅግ ነው ደስ ያለኝ። ደጎች ስለሆኑ ደስ ቢላቸው ደስ ይለኛል።
ዛሬ የኮከቦች ኮከብ ሻካ ብዙም ጎልቶ አልታየም፤ ሸኪሪ ግን የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይቷል፤ ከተለመደው ውጪ ሲዊዝሻ ዛሬ ለቢጫ በሽ ነበረች። እጅግ ያሳዘነኝ ግን የአንበላቸው የሊሽትስታዬንር ቢጫ ነው።
የሆነ ሆኖ ማሸነፉ ነው ቁምነገሩ፤ ሲዊዚሻ ከምድቧ ሁለተኛ በመሆን ለቀጣዩ ጨዋታ አልፋለች። ዛሬ ብዙ ዕድል አምልጧታል።
እውነት ለመናገር በዚህ ዓመት በአጀማመሩ ብዙም ያልረካሁበት የጀርመን ቡድን ነው። አስልቺ ነው የአጨዋወት ስታይላቸው ዘንድሮ፤ ጥንካሬቸውም እጅግ ቀንሶብኛል። ጀርመን ሁሉ ያላቸው ናቸው። ከሁሉ በላይ ከ2010 ጀምሮ የመቻቻል ብቃታቸው ይመስጣል። እኔን የሚስበኝ ይህ ነው። አዲሱ ቡድን የዚህ ሙሉ ባለቤት ከሆነበት ከ2010 ጀምሮ ከልቤ የማከብረው ቡድን ነው።
እርግጥ ነው ዕድለኛ ስለሆነ የጀርመን ቡድን ኮተት እያለ ለመጨረሻው ደረጃ ይደርሳል በዬዘመኑ። የጀርመን ቡድን ተከታታይነት ያለው አቅም በቋሚነት ያለው ነበር። ዘንድሮ ግን እኔ እንጃ … ደካማ ሆነውብኛል። ፊሊፕ፤ ባስቲ፤ ሉካስ የሉም …
በተረፈ ዋናው መሰረታዊ ጉዳይ በሚገርም በሚደንቅም ሁኔታ፤ ባልጠበቅኩት መንገድ ሲዊዝ ከምድቧ ከብራዚል ለጥቃ ሁለተኛ ደረጃ ናት ያለችው። ለቀጣዩም ጨዋታ አልፋለች። የሲዊዝ የእግር ኳስ ቡድኑ እድገት አሳይቷል። ይህ ለሲዊዝ አዲስ ትውልድ በጣም ጠቃሚው ነገር ነው። ምክንያቱም ሲበዛ ቁጥቦች ናቸው። ቁጥብነት የት ተፈጠረ ቢባል ተሲዊዝ ውስጥ ነው።
ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመክሩት መጀመሪያ መደበኛ በሆነ የቀለም ዕወቅት ዕድል በሰጣቸው መንገድ ትምህርታቸውን ጨርሰው የአንድ ሙያ ባለቤት መሆነ ነው። ይሄ ጸጋ፤ መክሊት፤ ልዩ ችሎታ ትርፍ ነገር ነው፤ አይደንቃቸውም … አያጨበጨቡለተም። አያበረታቱትም።
ይሄ የተሻለ ዕድል የሚያገኙት ባለ ልዩ መክሊቶች እንዲያውም ጀርመን ውስጥ በሚኖረው ውድድር ሄደው በማሳተፍ ነው እንጂ እዚህ ቀጥ ብለህ ትምህርትህን ተማር ነው መርሁም፤ ዶግማውም።
ስለዚህም የዛሬው ዕድል ለቀጣዩ ትውልድ የሲወዝ ቡድን በራስ የመተመማን አቅሙን ያሳድግበታል ብዬ ስለማስብ ተመስገን ብያለሁ። ለነገ ራሱ ነገ ይጨነቅ …
ስፖርት ፍቅር ነው!
የኔዎቹ መልካም ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ