ልጥፎች

ከኤፕሪል 7, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የሽብርቀን ለማኝ። ልብ ወለድ በ1980ዎቹ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የተጠፈ።

ምስል
እንኳን ደህና መጣችሁልኝ። „ፈሳሾች በዙሪያው ነበሩ፤ ማዕበልህ ሞገዱ ሁሉ በላዬ አለፉ።“ ትንቢተ ዮናስ ፬ ቁጥር ፪ የሽብርቀን             ለማኝ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 07.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ጉዑዝ ነገር ያናገርኩበትን ስለ አራት እግሩ እንጨት እና ስለ የሽብር ቀን ለማኝ አገር ቤት እያለሁኝ የፃፍኩትን አፈላልጌ እለጥፋላሁኝ ብዬ ቃል ገብቼ ነበር። አንዱ ስለተገኜ እንሆ … ኮምኩሙ … መቅድም ። ህዳር 14 ቀን 1985 እ.ኢ.አ በሥነ - ጸሑፍ ኮርስ ላይ እያለሁ መምህሬ አቶ አበበ ኬሪ የሰጠኝ የቤት ሥራ ነበር። የቤት ሥራውን የጣፍኩበት ዕለት ደግሞ  ህዳር 14 ምሽት ከ1.30 እስከ.1.57 ነበር። script ስክሪፕቱን በ16 ዓመቴ ከእኔ ከተለዬ እንሆ ዘንድሮ ከእጄ ገባ /ከእጄ ከገባ ወደ አራት // አምስት ዓመት ሆነው/። …. ገና አፍላ ዕድሜ ብቻ ሳይሆን የሥነ - ጥበብ ፍቅረኛነቴም ወጣት በነበረበት ወቅት የተፃፈ ነው። ምን ያህል እንደ አደኩኝ እንደ በሰልኩኝ ወይንም ቁልቁል አሰኝቶኝም ከሆነ መዝኑት - ክብረቶቼ … ቅኖቹ። ቅንነት መልካም ነው ሁሉን እንደተፈጥሮው ስለሚያስተናግድ። ይጀመር። በእጅ የተጻፈ ስለነበር በዘመንኛው ይቸክቸክ - እሺ! መኖር ድጉ እሱም እኔኑ ሲውዝ ድረስ መጥቶ ሊያኝ ይህን ሁሉ ወጪ ማፈሰሱን አደንቅኩለት። ያ የናዋዘው አዬር እሱንም ወግሮት ጥቁርቁር ብሏል።     የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል ይደረግለት ብዬ ይሄው ዕለተ ሰንበት እ...