ልጥፎች

ከጁላይ 3, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጌታ ሆይ! ተስፋችን ስለጠበቅክልን እናመስግንሃለን!

ምስል
ጌታ ሆይ! ተስፋችን ስለ ሰጠህን ስለ ጠበቅክልንም እናመሰግንህ አለን። ከሥርጉተ ሥላሴ 04.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ለምኑ ይሰጣችሆዋልም፤ ፈልጉ ታገኙምአላችሁ፤             አንኳኩ ይከፍትላችሁማል።“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ  ፯ ቁጥር ፯) ጌታ ሆይ! አምላኬ ሆይ! ፈጣሪዬ ሆይ! አንተ ሁሉ የሚቻልህ የሰማይ እና የምድር ጌታ፤ የሰማይ እና የምድር ልዑል፤ የሰማይ እና የምድር ንጉሥ ውስጣችን ስለ ሰጠህን እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁኝ። ዕንባችን ስላዳምጥክም አመሰግንሃለሁኝ። ጥያቄያችን ስለመለስክም አመስግንሃለሁኝ። ልዑሌ ሆይ! ህልማችን መዳፋችን ውስጥ ስለ አገባህልንም ተመስገን። አዎን አባታችን ሆይ! ዕንባ ጠራጊ ሙሴ ሰጠህን፤ መከፋታችን ዝቅ ብሎ የሚያዳምጥ ሰጠህን፤ ስለ እኛ ሞቱን የፈቀደ ሙሴ ሰጠህን ተመስገን ጌታ ሆይ! ንጉሴ ክርስቶስ ሆይ! እንደ እኛ ሳይሆን ስለቀደምቱ ደጋጎቹ፤ በዱር በገደል ክልትምትም ስለሚሉት፤ ስለሚሰደዱት ቅዱሳን ሁሉ ብለህ የይቅርታ በትረ አሮን ሸለምከን። አምላካችን ሆይ! ላንተ ምን ይሳንሃል? ከሞትም አተረፍክልን። ከመበተንም ታደግከን! እባክህን አምላካችን፤ እባክህን ጌታችን ሆይ! ክፉዎችን አስተምራቸው፤ ማስተዋሉን ስጣቸው። ወደ ልባቸው መልሳቸው። ያ የባከነ ትውልድ ቀጥሎ እናዳይባክን አንተ ሁነኛ ሁንለት ለአሜኑ ለተስፋችን። ፈጣሪያችን ሆይ! ለዋቢያችን፤ ለዋስ ጠበቃችን፤ ለተስፋችን፤ አንተ አለህለት እንል ዘንድ ያደረግከው ምልክትን በሱባኤ ተቀብለነዋል። ፈጣሪ ሆይ! ስላደረክልን መልካም ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁኝ። ቸርነትን ሰጠህን! ርህርህናን ሰጠህን! ተመስ...

የሰርገኛ ጤፍ ጦርነት።

ምስል
የሰርገኛ ጤፍ ጦርነት። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 03.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዝ።) „ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፣ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።“ (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ  ፮ ቁጥር ፴፬) ·        እ ንደ መክፈቻ። ዛሬ ሲዊዝሻ ሳይቀናት ቀረ። ጨዋታውም ማራኪ አልነበረም። እንዲያውም በግልጽ ቋንቋ የዓለም ዋንጫ ውድድርም አይመስልም ነበር። የእኔ ሲዊዝ ባትኖር ኖሮ እስከ መጨረሻውም አልከታተለውም ነበር። አሰልቺ ነበር። ሲዊድንም ከማጥቃት ይልቅ፤ ከመጫወት ይልቅ 12 መረብ ጠባቂ አሰልፎ ነበር ጨዋታው የተጠናቀቀው። በር ዘግቶ ጨዋታ።  በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ለሁለት ደቂቃ ያህል ሲዊዞች ጨዋታ ተጫውታዋል። ከዛ በተረፈ ግን ኳስም እንዳሻት፤ እግርም እንዳሰኛው፤ ጭንቅላትም ወደ ፈለገው ሲጎን ደቂቃው ተጠናቀቀ እና ሲዊድን አንዲት ግብ በአሳር አስገብቶ ለቀጣዩ ጨዋታ ቢያልፍም ያው ለዋንጫ አይደርስም ባይ ነኝ። ሁለቱም ቡድኖች የልብ አድርስ ነገር በጭራሽ አልሞከሩትም። አሁን ሲዊዝሻ የመኪና ጡሩንባ የለም፤ ጸጥ ረጭ ሁላችንም አለን። ቆቡም አልወለቀም፤ ምንኩስናችንም ይቀጥላል። ቆባችን ይጠብቅ ፈጣሪያችን። አሜን! ·        የወ ግ ገበታ። ዛሬ የተለያዩ አጫጭር ነገሮችን ሳደማምጥ ስርክራኪ ነገሮችን አዳመጥኩኝ። ያው "የሥም ግነቱ" ወደ አልተፈለገ አቅጣጫም ሊወስድ እንደሚችል ስጋት ቢጤ። እኔ እኮ ስለምን የቀደሙ ነገሮችን ለማጥናት እንደማይሞከር አይገባኝ። አሁን እከሌ ተከሌ ማለት ስልችቶኛል ደግሞም ፍርድ ለራስ ስለሆነ የተባጀበትን ታውቁታአለችሁ። „አንባገነን“ ቢሆን የአፍሪካ ደም እያለበ...

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማነው?

ምስል
ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም  ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውን ይወዳል  ወይንም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውን  ይንቃል ለ እግዚአብሄር እና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም“ (የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ ፮ ቁጥር ፳፬)                                            ባለ ክታብ መከታ                                        የተግባር ወራንታ                                  አለኝ ይሆን ይሉኝታ?          ...

"ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ..."

ምስል
ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን    በፊታቸው እንዳታደረጉ ተጠንቀቁ።“ „የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ ፮ ቁጥር ፩“ እ ርሾ ነስቶ ሲደነፋ-ሲ ያ ንኮራፋ ዘመን የሰጠው ዶ ፍ                            ሲ ቀር ፍ …                    … ሲ ዘር ፍ                    ሲ ወር ፍ …           … ሲ ሞተል ፍ        ሲ ነድ ፍ …      ሲናደፍ    … ሲ ል ፍ ጎርፍ …  የሚወርፍ ጥ ርቅምቃሚ -ጥንዝል- ዝንጥል፤ እንኮፍ- ሸንኮ ፍ ። ·         ተጣፈ  ...  ታህሳስ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ሲዊርላንድ ·        ለህትምት የበቃ በተስፋ መጽሐፍ። ·        እርእሱ ...

ክፍል ስድስት ርትህ።

ምስል
ርትህ። ክፍል ስድስት። ከሥርጉተ ሥላሴ02.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት  ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዕን ናችሁ“ (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፲፩ ) ·          መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c „ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar“ በዚህ ውስጥ የሠማራውን ጉባኤ መዳሰስ የምፈልገው ከ20.38 ባለው ደቂቃ ብቻ ያደመጥኩትን ነው። ቀሪው ክ/ጊዜ ደግሞ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህን እማደርግበት ዋናው ምክንያት ዛሬ ያለው የለውጥ ተስፋ እና እኛ ያለን መጣጠም መቀራረብ እንዲኖረው ለማድረግ ነው። ክፍተት ከኖረም መገጣጠም ስለሚያስፈልገው እንደ ዜጋ የግል ዕይታዬን ለማካፈል ነው። ·        ኢህአዲግ እና ሁኔታው።  ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጋ ማዕዶት ናት። ኢትዮጵያን የፈጠራት ኢህአድግ አይደለም። ቀን እና በለስ ተገናኝተው ነው ለዚህ ዕድል የተበቃውም እንዲሁ እጅግ በርካታ አምክንዮ አሉበት። ደግነቱ እንደ መረረ ስላልቀረ አሁን ተስፋ ቢታይበትም ቀጣዩ በዘበጠ መልኩ መሆን ስሌለበት መርህ ይግዛኝ ማለት አለበት ግንባሩ። ኢህአዴግ እራሱ ለአንድ የፓርቲ ግንባር መርህ ነው ህይወቱ እና ሂደቱ እንዴት እና እንዴት ናቸው ለሚለው፤ እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ለማዬት ሁሉ የሚቸገሩ ስንክሳሮች አሉበት። ግን ኢህአዴግ እንደ ግንባር የሰምምነት...