ክፍል ስድስት ርትህ።

ርትህ።
ክፍል ስድስት።
ከሥርጉተ ሥላሴ02.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት
 ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዕን ናችሁ“
(ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፲፩ )


  • ·         መነሻ።

„ጠ/ / አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar“

በዚህ ውስጥ የሠማራውን ጉባኤ መዳሰስ የምፈልገው ከ20.38 ባለው ደቂቃ ብቻ ያደመጥኩትን ነው። ቀሪው ክ/ጊዜ ደግሞ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህን እማደርግበት ዋናው ምክንያት ዛሬ ያለው የለውጥ ተስፋ እና እኛ ያለን መጣጠም መቀራረብ እንዲኖረው ለማድረግ ነው። ክፍተት ከኖረም መገጣጠም ስለሚያስፈልገው እንደ ዜጋ የግል ዕይታዬን ለማካፈል ነው።
  • ·       ኢህአዲግ እና ሁኔታው።

 ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጋ ማዕዶት ናት። ኢትዮጵያን የፈጠራት ኢህአድግ አይደለም። ቀን እና በለስ ተገናኝተው ነው ለዚህ ዕድል የተበቃውም እንዲሁ እጅግ በርካታ አምክንዮ አሉበት። ደግነቱ እንደ መረረ ስላልቀረ አሁን ተስፋ ቢታይበትም ቀጣዩ በዘበጠ መልኩ መሆን ስሌለበት መርህ ይግዛኝ ማለት አለበት ግንባሩ። ኢህአዴግ እራሱ ለአንድ የፓርቲ ግንባር መርህ ነው ህይወቱ እና ሂደቱ እንዴት እና እንዴት ናቸው ለሚለው፤ እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ለማዬት ሁሉ የሚቸገሩ ስንክሳሮች አሉበት። ግን ኢህአዴግ እንደ ግንባር የሰምምነት ሰነድ ብቻ ወይንስ የፓርቲ መሰረታዊ ሠነዶች አሉትን?   
  • ·       ልባም ጉዳይ።

በዚህ ገላጻ ልባም ጉዳይ ያገኘሁት በቃ አገር ምድሩን ሲቆጣጠር የነበረው ኢህአዴግ መሆኑን ነው አበክረው ጠ/ ሚሩ የገለጹት። ይሄ መቼም የልቤ የሚባል ጉዳይ ነው።

አንድም የተፎካካሪ ፓርቲ መሪ የሆነ አባል በዬትኛውም የሃላፊንት ቦታ አለመገኘቱ ኢህዴግ እንደ ግንባር ሊያፍርበት ይገባል። ውርዴትም ነው። ለዚህ ውርዴት አሁን ያለው አመራርን ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ባይቻልም፤ በዚህ ገለጻ እኔ እንደገባኝ በጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ባይታዋርነት በውስጥ አጀንዳ ተመስጥሮ የቆዬ ስለመሆኑ ፍንጭ አግኝቻበታለሁኝ። እንዴት ቅቤ እናዳጠጡኝ። ይባረኩ!

ስለዚህ በዚህ መስመር የተሻለ ሁኔታ ሊኖር ይችላልም ይገባልም ብዬ አስባለሁኝ። የዚህ ስጋት ምንጩ የአውራውን ፓርቲ ፍላጎት ለማስፈጸም፤ አውራ ስል ለእኔ ኢህአዴግ እንደ ግንባር ነበር የሚለው የሽወዳ ፓለቲካን የመቀበል አቅሙ የለኝም ማለት አልፈቅደውም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ነበር አውራው ፓርቲ። ስለሆነም  በአውራው ፓርቲ መንፈስ ውጪ ከተሆነ ይቸግራል ነው ፍሬ ነገሩ። ስለዚህ አውራው ፓርቲ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን የተጸዬፈ ስለነበር የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በዬለም የተጠቀለለ የመከራ ዘመን ነው ያሳለፈው።

ኢህአዴግም አባል ሆኖ የወያኔ ሃርነትን ኢትዮጵያን የመጸዬፍ አመክንዮ የማይቀበል ነፍስ ቦታ አልነበረውም። ለዚህ ነው እኔ ለቁንጣቁንጢ ሳይሆን ዜጋን እኩል እንደ ሰው የሚይ፤ ትውፊቶቿንም እንደ ዜጋ የሚይ፤ ታሪኳንም እንደ ዜጋ የሚይ፤ የተፈጥሮ ሃብቷንም እንደ ዜጋ የሚይ ለሥርዕቱ መፈጠር እንትጋ የምለውም። ዜጋን በአቅሙ፤ በልኩ፤ በብቃቱ የሚላካ የሚመዝን ቦታ ለመስጠት የማይሰስት ህጋዊ ሥርዓት መገንባት ትልቁ አውራው ጉዳያችን ሊሆን ይገባል።

አሸናፊንም ተሸናፊንም ፓርቲዎች እኩል ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን ከፓርቲ ውጪ ለመኖር ለምንፈቅደው እንደ እኛ ላሉ ባለቤት አልባዎችም እንደ ዜጋ መታዬት የምንችለበት ሥርዓት መፍጠር ነው የልቤ ሊባል የሚገባው።

ዜጋ ቦታ ለማግኘት የፓርቲ አባል መሆን መገደድ የህሊና ተጽዕኖ ሊደረግበት አይገባም። እዚህ ውጪ አገር ተሰደን በምንኖርበትም ነፃነታችን ተቀምተን በግዞት የምንኖርበት ምክንያት ይሄው ነው። እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ላላ መንፈስ ነጻ ሰዎች ልቅ ዓለም ክፍላቸው ስለሆነ በልቅ ዓለም ለመኖር መፍቀዳቸው ከችሮታዋ ከእናታቸው ሊያስገልላቸው አይገባም!በማህረሰቡም ዘንድ እንደ እርግማን ሊታዩ ሊገለሉ፤ ሊወገዙ፤ ተቋርጠው እንዲቀሩ ሊደረግ አይገባውም። እንደ ፈቃዳቸው እዬኖሩ እናታቸውን በብቃታቸው፤ በችሎታቸው፤ በተመክሯቸው ልክ እንዲያገልግሎ ምንም ዓይነት ጫና እና ዕቀባ ሊደረግባቸው አይገባም። ከወገኖቻቸውም ጋር እንዲለዩ ሊደረግ አይገባም። መብት ነው የቴሎፎን የፓርቲ አባል መሆን እና አለመሆን።  
  • ·       ጥቅም አለው 

ሁሉንም በነፃነቱ ልክ እንዲኖር መፍቀድ ይሄ እጅግ ዝልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥቅም አለው። ያልተኮደኮደ ማህበረሰብ እና ትውልድ ለመፍጠርም መሰረት ነው። አሳታፊነት ከኖረ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ብቻ ሳይሆን መልእክትም ይዞ ስለሚወለድ፤ ጥሪም ይዞ ስለሚፈጠር የልምድ፤ የተመክሮ የግብይት ሥርዓቱ ማዕቅብ እስካልተጣለበት ድረስ ሰብዕና በነፃ ያስባል፤ በነፃ ይመራመራል፤ በነፃ ይፈጥራል፤ በነፃ ይጠበባል። ይህ ደግሞ ትውልድንም አገርንም - ታሪክንም - ትውፊትንም ለማስቀጠል የነፍስ ያህል አስፈላጊ እና መሠረታዊ ነው።

  • ·       ነፃነትን ሥነ  -ልቦናን አሳሪ ባልሆነ አገር፤ የወረቀት ማህበርተኛ አባል ባልሆነ አገር ከብዙ በጥቂቱ እነኝህን ለማናሙና ማዬት ይቻላል።  

v   ዜጎች ልማዳቸውን - ተምክሯቸውን - ፓተንታቸውን ለአገር ጠቀም ሁኔታ ለማዋል ይረዳቸዋል። ያልታሠረ ህሊና እኮ ነው ማሰብም መፍጠርም የሚችለው።  

v   ዜጎች ከመራራቅ ፖለቲካ መቀራረቡን ይመርጡታል፤ ዜግነት እኩልነት ስለመሆኑ ይረጋገጥበታል፤
   
v   የበላይ እና የበታችነት መልክ ይይዛል፤ ሰው መሆን መሆንን ያበሥራል። አስተዛሬ መቼም ሰው ሆነን ታይተን አንታወቅም። 

v   ሥራ ላይ በተጠመዱ ቁጥር የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችም ሆነ አባላት ለሌላ የሚያባክኑት ጊዜ አይኖርም፡፤ በሥራ ሂደት ከሚገኘው የተመክሮ ማሳም ተቋዳሽ መሆን ይቻላሉ፤ ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ የ ኢህአድግ ብቻ ሳትሆን የእኛም ናት የማለት የውስጥ እኛዊነትን ይፈጥራል። 

v    በትውልዱ እና በመንግሥት መካከል ጤናማ ግንኙነት ይፈጣራል፤ በበላይ እና በበታችነት ሳይሆን በቤተሰብ መካካል እንዳለ ዓይነት ስሜት ይፈጥራል። ይህ ቀላል ነው ስጽፈው ግን ትርፉ ረቂቅ ነው። አለኝ ማለት መኖር ነው። መሪ አለኝ፤ መንግሥት አለኝ ማለት መኖር ነው። 

v   ልምድን፤ ተመክሮን፤ ክህሎትን በማቅናት እና መሸመት እና በመሸመት ማቅናት ጤናማ የቅርርብ ውርርስ ይፈጥራል በቀጣይም፤ አሁን እኮ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መታመንን ባጡ ቁጥር መንፈሳቸው እዬራቀ መሄዱ ግድ ነው። ባይታዋር ናቸዋ። ሌላው ተከታዮቻቸውም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ማዬት የተገባ ነው። እኔ የዶር አብይ እህመድ ተከታይ ሲሆኖ መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓመት እኔን ያዬ ያ ሁሉ የሐዘን ዘመኔን እርግፍ አድርጌ ነው የረሳሁት። ደጋፊውም ተከታዩም ጭምር ፈውስ ያገኛል። ለዛውም የመንፈስ። 

    ኢህአዴግ ሲያስርም ሲፈታም አንድ ሰውን አይደለም። ደጋፊውም ይታሠራል አብሮ፤ ሲፈታም ያ/ ያቺ የነፃነት አርበኛ እኩል ይፈታሉ አብረው። የመንፈስ ብክነት አይኖርም። የመንፈስ ብክንት ካልኖረ ነገሮችን ከውስጣቸው ለማዬት ይፈቀዳል። በግርፍ ከመቃወም ብቻ ሳይሆን ከ አሉታዊ ማህበርተኝነት ይወጣል። ይህ በስብዕና ግንባታ ላይ ሰፊ በረከት አለው። አሉታዊነት ቅንቅን ነው ነቀዝ። ግን የግድ የሚሆንበት ደግሞ ጊዜ ይኖራል። ይህን ማመጣጠን የሚያስችለው ተመጣጣኝ ሚዛናዊ መሪ ሲገኝ ነው። አሁን ክብሩ ይሰፋ ለእኔ መንፈስ ተሳክቶልኛል፤፡ 

v   ተፎካካሪዎች አሸናፊ ቢሆኑ ብሎ ማሰብ ይገባል። አንድ ለ አገሩ ተቆርቋሪ ነኝ ብሎ የሚያስብ ፓርቲ ቢሸነፍ ውጥኑ ስለመቀጠሉ እርግጠኛ መሆን የሚችለው ተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችን እያለማማደ ከመጣ ብቻ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን የልምድ እጥረት ስለማኖርባቸው የተጀመሩ ጥረቶችን የማስቀጠል አቅም አይፈጠርላውም። ይህን ትብትብት ለምፍታት ሃሳቡ በጽንስ ደረጃ እንዳለ ነው በሠመራው ጉባኤ መልስ ላይ የተረዳሁት። ይህን ተግባራዊ መድረግ ከተቻለ የአማራር ውርርስ እና ተከታታይነት ይፈጥራል፤

v   በዚህ ከ አግላይነት ፖለቲካ መውጥት ከተቻለ የሥነ ልቦና ትርፉ ሊመረመር ሊለካ ከቶውንም አይችልም፤

v   የባለቤትነት ስሜት፤ የአገልጋይነት ስሜት በፍጹም ሁኔታ ይበለጽጋል፤

v   ዜጋው በሙሉ ከመንግሥታዊ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለ27 ዓመት ተገሎ መኖር መቼም ግዞት ነው። ለዚህም ነው አሁን እርሾ አልባ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማዬትም ማድመጠም አቅም የጠፋው።

v  ትውልዱ ይማርበታል በማዬት ብቻ፤ ምክንያቱም ወላጆቹ የፓርቲ አባል ሳይሆኑ ሃላፊነት ታማኗቸው በመንግሥት ከተሰጣቸው በራሱ ተቋም ነው ለልጆች። እኛ ስለምንሥራው እያንዳንዱ ነገር ልጆችን እዬረሳን ነው የምንሠራው። ነገር ግን ሰብዕናን ለመቅረጽ እንዲህ ዓይነት መስኮች እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው። አንድ ወላጆቹ  የኢህአድግ የግንባሩ አባል የሆነ ልጅ እና አንድ ያልሆነ  ልጅ እኩል ት/ ቤት ላይ ሲቀመጡ ሁለቱም ወላጆቻቸው በአቅማቸው፤ በክህሎታቸው እኩል በሥርዓቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ሥነ - ልቦናቸው የልጆች በእኩ ልነት ነፃነት ላይ ተገንብቶ ያድጋል። ልጅ ከወለዱ በዋላ የሚፈቱ ትዳሮች ለልጆች የሚያሳድሩትም ተጽዕኖ እንዲሁ ነው። 

    ለዚህ ነው እኔ „እርግብ በርን“ ትዳርን ስኬታማ ማድረግ ለቀጣዩ ትውልድ መሰረታዊ ጉዳይ ነው በማለት አንድ መጸሐፍ የጻፍኩት። ያው ታሽጎ ተቀምጧል በጉልበተኞች። ዜጋ አይደለሁኝም በእንሱ ቤት። በገንዘብ መብቴን መግዛት ስላልፈቀድኩኝ። መብት በገብያ ህግ አይተዳደርም። መብት ዕዮራዊ ነው። በሌላ በኩልም መረገጥንም ስለማልቀበል። 

   አጃቢነት እና መናጆነትም ክፍሌም ስላልሆነ። ልብ ማስገጠም ከሮበትንት ውጪ ስላልሆነም። የእኔ የምለው ሰብዕና እና ማንነት እንዲሁም የራሴ መርሃዊ ሃሳብም አለኝ። የምንም ሥነ - ልቦናዊ ጉዳይ ተጠዋሪ አይደለሁኝም ስለምልም። ስለ እኔ ማህንዲሷ እኔው ባለቤቷ ሥርጉተ ሥላሴ እንጂ አንድ ቀንጣ ነፍስ ያዘጋጀው ወረቀት አለመሆኑን በጽኑ ስለማምንበት። 

   ራሳቸውን ያስቀምጣሉ በዛው ይዘልቃሉ። ማን መረጣችሁ ቢባሉም እራሱ መልስ የላቸውም። ስፈቅድና ስመርጥ፤ የመረጥኩት ስለሰናዳው ሰነድ በስማ በለው ሳይሆን ፈቃዴን ጠይቆኝ፤ አምኜበት መቀበል ካልቻልኩኝ ስለሌላው ለመኖር እንደ ቴንብር ሳልሆነ ስለራሴ መኖር ነው የተፈጠርኩት። ስለ እኔ ነፃነት መታገል የተሳነኝ ስሌላው ነፃነት ለመታገል ሞራሉም አይመጣም። አራባ እና ቆቦ ነው …  
  • ·       ወጥነት።

በዚህ በሠመራው ጉባኤ ያደመጥኩት በኽረ ጉዳይ እንዲሁ በተባባራሪ ሁኔታ ሲደመጥ የነበረው ኢህአዴግን ወደ አንድ ወጥ ፓርቲ የመሸጋገር ትልም ነው። ይሄ ከባዱ ፈተና ነው የሚሆነው ለኢህድግ ቀጣይነት ነው ። አሁን እኮ የአብይን መንፈስ ንጽህና የመከተል ጉዳይ፤ ድንግልናው ምን ያህል ነው በማህብርተኞቹ አባልት ዘንድ?ይህ ንጽህና እና ቅድስና የግንባሩ የወል ወለል ካልሆነ ምን ያህል ሊያሰኬደው ይቻላል?

ህዝብ በባይታዋርነት የኖረበትን ዘመን ማክተማያውን ለማመቻችት እጅግ ፈታኝ እና ፈታይ ተራራዎች አሉበት ኢህአዴግ ወጥነቱን ከፈቀደው።  ወያኔ ሃርነት ትግራይን በቀጣይነት ለማሰመረጥ በወጥነት ከሆነ ከሁሉም የገዘፈ ችግር ሚገጥማቸው ኦህዴድ እና ብአዴን ናቸው። አንድም መንፈስ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመመረጥ፤ ድምጽ የመስጠት አቅም ከዬትኛውም የህዝብ ጉባኤ አላዳመጥኩኝም ከአፋር እና ከቤንሻጉል ጉምዝ በስተቀር። ይሄ እውነት ስለሆነ ነው የምጽፈው …
   
 ስለዚህ በምን ስሌት እና አቅም ወያኔ ሃርነት ትግራይ በግንባሩ ውስጥ ኖሮ ይመራኛል ብሎ ህዝብ ድምጹን ለመስጠት ያስችለዋል ጥያቄ ምልክት ነው? በደንብ ሊፈተሽ ይገባዋል። ከምርጫ በዋላ ውህደትም ከሆነ የአብይ ንጽህና ችግር ይገጥመዋል። ግልጽነት ህይወቱ ስለሆነ። 

ስለዚህ ይህ የወጥነት መንፈስ ስለገደልከኝ፤ ስለ አፈናቀልከኝ፤ ስገዛህኝ ስለነቀልከኝ ቀጥልልኝ እንደ አፋር ህዝብ ሌላው ሊል አይችልም። በፍጹም። የፈለገ የምህረት፤ የፍቅር ነገር ይሰበክ። አብሮ ለመኖር እንጂ እንደገና ቀንበር ለመጫን መንገዱ ዳገት እና ዳጥ ነው። ኦህዴድም ብአዴንም ተጨፍልቀን ድምጽ እናገኛለን ብለው ካሰቡ የሚሆን አይደለም። 

ደቡብም ያው የተጠና የቀርንበት ገፊ የሰላ ስልታዊ ሃይል አለበት። አሁን እንዲህ የሚዲያ ንግሥና የተፈለገበት ምክንያት እንተዋወቃለን የብልጥነቱን ፖለቲካ። የሆነ ሆኖ የታሪክ ሽምያውን ለባለቤቶች ለፖለቲካ ነጋዴዎች ትቼ በአዎንታዊነት  የሚታዬው መነቃቃት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ለቀደመው የመግዛት ዘመን መዘላያ እንደልብ የሚያስኬድ መንገድ እንደሌላ ያስኬዳል። 

የግንባሩን የአሰራር መመሪያዎች እናሻሻል አለን ብቻ ሳይሆን ሥርዓተ ህግጋት እንዲገዛው እንደርጋለን ከሆነ ይቻላል። ግን በወጥ ፓርቲነት ወያኔ ሃርነት ትግራይን ተይዞ ምረጡኝ በህልም ባይታሰብ ነው የሚሻለው። አጨልሞታል። ደህና ሰዎች አሉ ለማለት እንኳን የሚችል መንፈስ የለም። ሊሂቃኑም በዚህ ላይ አይሰሩም። እውነትን መድፈር ይሳናቸዋል።

ምክንያቱም አንዲት ሳር ስተመዘዝ ከታላቋ ትግራይ ህልም እና ራሮት ጋር የተያያዘ ስለሆነ። ሌላው እራሱ ትግራይ ውስጥ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ራሱን ችሎ ለመቆም የሚያስችለው አቅም አለው ወይ ቢባል እንደ ፖለቲካ ሰውነቴ አንድ አውራጃ ላይ ብቻ አንድ ብሄረሰብ ብቻ ቸክለህ የሚሆን አይደለም።

ትግራይን ህዝብ መሠረት አድርገው የሚነሱ ተፎካካሪዎች እርግጥ ነው በቅርጽ እንጂ በይዘት አንድ ናቸው ምንም የጭብጥ ልዩነት የላቸውም። በቴክኒክ አፈጻጸም ነው የሚለዩት። በለዬላቸው የእውነት አጀንዳዎች ላይ ከቅዱስ አቶ ገ/ መድህን አርያ በስተቀር የሉም። የሾለኩ ናቸው። 

ከኢትዮጵያዊነት በላይ ትግሬነትን የሚያከብሩ እና የሚያስከበሩ ለዛም የሚተጉ ናቸው። ስለ ሰው ልጅ መጨፍጨፍ፤ መፈናቀል፤ እራፊ ማጣት የማይጨንቃቸው ቁስ አምላኪዎች ናቸው። ስለዚህ በፖለቲካ ፍልስፍናዊ ዕሳቤ እና በአፈጻጸሙ መሃከል አልተገናኝቶም ለ እኔ ሃሳቡ። ውጤቱን ለማሰብ መንግዱ ጨላማ ነው ... ወያኔ ሃርነት ትግራይን አብሮ በወጥ ፓርቲነት መሳቀጠል የሚሆን ሂሳብ አይደለም። እኔ የምወደው የወደድኩትን ሰብዕና ብቻ እንጂ ያ ሰብዕና የወደደውን ሁሉ አይደለም። በፍጹም። 

ውዶቼ ቀሪ ክፍል ይኖራል። ከ20.38 እስከ 55.38 ያለው ይደመጣል፤ ይኬድበታል። ያው እኔ እማቀርበው የግል ዕይታዬን ብቻ ነው። ገፊ እና ተጫኝ ሃይል የለበትም። ቁልጭ ብላ ነው ሥርጉተ ሥላሴ ራሷን እምታቀርበው።

ኢትዮጰያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

ቅኖቹ ማለፊያ ጊዜን በኑሩልኝ።
  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።