ሕይወት #የሚቀለው የሰው ልጅ ለመኖር #ፍላጎት ሲኖረው ነው።
ሕይወት #የሚቀለው የሰው ልጅ ለመኖር #ፍላጎት ሲኖረው ነው። የመኖር #ፍላጎቱ ምኽዋር ደግሞ ሰላም። ለእኔ ሰላም ፲፫ኛው ፕላኔት ነው። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ለመኖር ፍላጎት ማመንጨት የሚቻለው #በስኬት ብቻ አይመስለኝም። የተሳካላቸው ፈቅደው መራራውን ስንብት ሲወስኑ ስለምናይም /// ስለማድመጥም። ለመኖር ፍላጎት መኖር #መማርም ብቻውን፤ የመኖር ፍላጎትን ያበረታታል ብዬ አላምንም - እኔው። ለመኖር ፍላጎት አስቻይ ሁኔታ የሽልማት ብዛትም አይመስለኝም። ሽልማቱ ሲቀር ወይንም ሲቀንስ መኖር #በቁዘማ ውስጥ ሊታክት ይችል ይሆናል። የመኖር ፍላጎት እንዲቀጥል ቤተሰብ መመስረት፤ ልጆች መኖር፤ ጥሩ ቢላ ሠርቶ ምቾትን ማስተናገድ ብቻውን ለመኖር ፍላጎት መጨመር ሚና ሊኖረው ይችላል ብዬም አላስብም። መኖርን የሚያኖረው #የውስጥ #ሰላም ፤ የከባቢ ሰላማዊ አየር፤ ከጭንቀት ጋር የማይነካካ ገጠመኝ ሲኖር የሰው ልጅ መኖርን ሊፈልገው፤ በመኖሩ ተስፋ ሊያደርግ፤ መኖሩን እንደ አንድ #በኽረ መሪ ኃይል አድርጎ ሊወስደው ይችላል ብዬ አስባለሁኝ። #ሰላም ። ቁልፍ ግን የሰው ልጅ ለሰላም ያለው አትኩሮቱ ቀጫጫ። የመፍትሄ ጎዳና ግን የሰው ልጅ ለሰላም ያለው አክብሮቱ ስስ። የውስጥ ሐሤት አመንጭ ሆኖ ግን የሰው ልጅ ውስጡን ያሸፈተበት። ሰላም የማሰብ አቅምን አፋፍቶ የህሊና #ብቃትን የሚያጎለብት ግን የሰው ልጅ የሚሰጠው ትዕግስት ኮሳሳ። የፍልስፍና ልቅና ገላጭነት ባለቤት ሆኖ ግን የሰው ልጅ በመቻል አቅም ጥብቆነት እንዲሰቃይ የሚደረገው። የሰላም ጎዳና፤ ሰላሚዊ - እርምጃ፤ ሰላማዊ - ሩጫም፤ ልቅናም ይሁን ልዕልና፤...