የማረተው የደራጎን ዝልቦ አይዋ ጎርምድ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። የማረተው የ ደራጎን ዝልቦ። “ … ስለዚህ ክፉዎች፤ በፍርድ፤ ኃጢያተኞችም በፃድቃን ማህበር አይቆሙም፤ እግዚአብሄር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና። የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች። መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ከ፭ እስከ ፮ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 16.02.2019 ይህ የሆነው ለላንቲካ አይደለም! · መነ ሻ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/94071#comments “ ጎንደር የራሱን ክልል መመስረት አለበት ” – የጎንደር ሕብረት ፕሬዚዳንት ዶ / ር ሙሉጌታ ካሳሁን እም! እማይሰማ የለም? እነ የሙት መሬት ባልደረባዎች እነ አያልቅበት ሌላ የሰላ ባለሦስት ጥንዙል የጨለማ ማቃዊ - ድቅድቅ - ሙርቅርቅ ዜማ ደግሞ ይዘው ከች ብለዋል። እነ የጎንደር ህብረት። ለጎንደር ህብረት ዛሬ ሥም ላወጣለት ፈለግሁኝ። ጎርምጥ ብዬ። ውዶቼ ደህና ዋላችሁልኝ። ደህና ናችሁ ወይ? ናፍቆት በናፍቆት በብራና ፍቅርም ይላክላችሁ የእውነት ንፍቅ ብላችሁኝ ነበር የሰነበታችሁት። እኔ ግልጽ እና ቀጥተኛ ሴት ነኝ። የምላችሁ የሆንኩትን ነው። የጎንደር ህብረት መርዝ አላባራ አለሳ? ...