ልጥፎች

ከዲሴምበር 15, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ወጣቱ ለራሱ ሲል ለውጡን ይጠብቅ!

ምስል
ለውጡ ለኢትዮጵያ       ወጣቶች የልብ አድርስ ነው። „እጃችሁን ለእግዚአብሄር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሄርን አምልኩ።“ መጽሐፈ ዜና መዋል ምዕራፍ ፱፰ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie   15.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ጠ ብታ። ውዶቼ እንዴት ናችሁ ያቻላችሁ ፌስ ቡክ ያላችሁ ይህን መልዕክት ከፌስ ቡካችሁ ብትለጥፉልኝ ደስ ይለኛል። ምስጋናዬም ከንጹህ ልቤ እንሆ። ወጣቶች ከብክነት የማውጣት ትውልዳዊ ድርሻ አለብን። የእኛ ይበቃል። ወጣቶች የሚሸሹበት ምክንያት ሙሉ አቅም ስላላቸው ነው። ይህ ለውጥ የሚመራው የአብይ ካቢኔ ደግሞ በወጣቶች አቅም ለመጠቀም ስንዱ ነው። ስለምን? እርካቡን የያያዙት ወጣቶች ስለሆኑ። እነሱን የሚተካ ተከታይ ሃይል መፍጠርም ዋንኛ ዓላማቸው ስለሆነ። ጥቃቱ ደርሶባቸውም አይተውታል። https://www.youtube.com/watch?v=irRwk5vK7A8&t=17s Ethiopia - Dr Abiy ahmed Synergy የ " መደመር " እዉነት ሲገለጥ … ·        የወ ግ ገበታ። ወጣትነት ዕድለኝነት ነው። ወጣትነት ሃያልነት ነው። ወጣትነት አቅማዊነት ነው። ወጣትነት ጉጉታምነት ነው። ወጣትነት ፍጥነትነት ነው። ወጣትነት ግንባር ቀደምትነት ነው። ወጣትነት ምናባዊነትም ነው። ወጣትነት ድፍረትነት ነው። ወጣትነት ችኩልነትም ነው። ወጣትነት ግብታዊነትም ነው።  ወጣትነት ግንፍልተኝነትም ነው። ወጣትነት ስሜታዊነትም ነው። ወጣትነት እውቀት ፈላጊነትም ነው። ወጣትነት አዲሳዊነትም ነው። ወጣትንት ስኬታማዊነት ነው። ወጣትነት ፍቅራ