ልጥፎች

ከኖቬምበር 30, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እስኪነጋ...

ምስል
እስኪነጋ ... “ከአፌ ቃልም ቃል ፈቀቅ አትበል።   አትተዋት ትደግፍህማለች፤   ውደዳት ትጠብቅህምአለች።”   መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፮ ከጸሐፊ መስፍን © ማሞ ተሰማ ( M esfin © Mamo Tessema) ሠላም ለናንተ ይሁን! አዎን እናምናለን። አዎን እየነጋ ነው። የህ ው ሃትና ህውሃታውያን ዘመነ ፅልመት እየተገፈፈ ነው። በኢትዮጵያ ሠማይ ሥር የብሩህ ቀን አጥቢያ ፍካት ይታያል። ያለጥርጥር ይነጋል። አዲስም ቀን ይሆናል። ግን ገና አልነጋም። መቼ ይነጋል? ብላችሁ አትቸኩሉ። ንጋትም ተፈጥሯዊ ዑደቱን ያጠናቅቅ ዘንድ ግድ አለውና። ንጋቱ በህወሃትና ህወሃታውያን ፅልመት እንዳይጋረድ ግድ ነውና። ህወሃታውያን እነማን ናቸው? ህወሃታውያን ማለት እነ ጃዋራውያን እነ ፀጋዬ አራርሳውያን መሰሎቻቸውና ወዘተርፈዎች ሁሉ ናቸው፤ የበቀልና የቂም በቀል የጥላቻና የጎጠኝነት ታንቡረኞች። ህወሃትና ህወሃታውያንም የኢትዮጵያን ዘመነ ፅልመት ናፋቂዎች ናቸውና። እንዲነጋ፤ የህወሃትና ህውሃታውያን መጋዝ ጥርሳቸው ሊረግፍ ግድ ነው። እብሪተኛው ጉልበታቸው ሊፈስ ግድ ነው። ለ27 ዓመት እንደ መንግሥት የረጩት መርዛቸው ሁሉ ሊመክን ግድ ነው። የታበዬ ልባቸው ሊሟሽሽ ግድ ነው። በዝርፊያ የደለበው የባንክ ደብተራቸው ይቀደድ ዘንድ ግድ ነው። እንዲነጋ፤ መከላከያ ፖሊስና ደህንነት በለውጡ ህግ ሊገዙና ሊደራጁ ግድ ነው። የሀገር እንጂ የጎጥ አገልጋይና ታዛዥ አይሆኑ ዘንድ ግድ ነው። ፍርድ ቤቶችና የህግ ተቋማት በለውጡ ራዕይ በህግና ፍትህ አርማታ ላይ ብቻ ይታነፁ ዘንድ ግድ ነው። እንዲነጋ፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ በህግ ማዕቀፍ ይከበሩ በዜጎችም ያለ ስጋት ይተገበ...

በለው! የዶር አረጋይ የማንኪያ እና የእግራምሳህን አቅርቡልን አቤቱታ!

ምስል
የዶር አረጋይ በርሄ ማንኪያ። „በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሄር ከወንዝ ፈሳሽ  ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይዋቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ © ሥላሴ ( Sergute © Sselassie ) 30.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ጠ ብታ ትንሽ ስለማንኪያ አምድነት። ዶር አረጋይ በርሄን በአካል አውቃቸዋለሁኝ። ቁንጥንጥ አለመሆናቸውን እወድላቸዋለሁኝ። ተናዳፊም አይደሉም። አንድ ነገር ከያዙ ግን ችኮ ናቸው። ·        ከበጎው ስነሳ። ተስፋ አለመቁረጣቸውን አደንቀዋለሁኝ፤ ዛሬ ካልካዱት እኔ እራሴ በተገኘሁበት ስብሰባ በፈርንጆች አቆጣጠር በ90ዎቹ መጨረሻ ላይ ከዛ ዘመን ጀምሮ ነው ውጭ የሚኖሩ ጎንደሬዎች ከህሊናቸው ጋር የነበሩት። እና የስብሰባው ተሳታፊዎች የወልቃይት እና የጠገዴ የመሬት ዘረፋ እና ወረራ ሲጠዬቁ፤ ስህተት እንደነበር ፤ ትክክል አልነበረም፤ ቦታው የጎንደር ነው ሲሉ በጆሮዬ አዳምጫለሁኝ። በወቅቱም በሉላዊ ሚዲያ ዜና ሰርቼበታለሁኝ። ዛሬ ደግሞ ዴሞካረፊው ስለተለወጡ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ይደመጣሉ፤ መቼም እንደ ሽንብራ ቂጣ መጋለበጥ ነው፤ ለነገሩ ከአራና ጋር ተዋህደው የለምን? የአረና አቋም ደግሞ ይታወቃል። ወራራ፤ ዝርፊያ ክብሩ ሞገሱ ግርማው ነውና። ስለዚህ በዚህው የቀደመው አቋማቸውን እራሳቸው በራሳቸው ሸረውታል ማለት ነው። ፈረሶ መሰራት፤ ተሰርቶ መፍረስ። ይልቅ አሁን አገር ከገቡ ያዬሁት ነገር የሰከነ ሂደት ለመከተል ያደረጉት ጥረት መልካም ነው ለስልትም ...