ልጥፎች

ከኤፕሪል 13, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፌስቡክ ተቀናቃኙ ጠ/ሚር ሌጋሲ ዶከክብኝ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  „ወደ ትዕቢተኛ እና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው“ መዝሙር ፴፰ ቁጥር ፬ የሩኽ ስቅዛት። ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie  13.04.2019  ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።                                      ጀግኖቼ! ድንግልዬ ትጠብቅልኝ ጽናቶቼን! እንዴት ናችሁ ውዶቹ ውቦቹ? ይህን ጹሑፍ ስጽፈው ከራሴ አገር በአፅህኖት  እዬታገልኩኝ ነው። በተለይ እነዛን 100 ቀኖች ሳስባቸው እና ዛሬ ያለውን  እውክ ድባብ ሳስተውለው አቅም የሚያሳጡኝ በርካታ የህሊና ሙግቶች ናቸው  ያሉብኝ።  የወረት የሆኑ ጉዳዮች ለባከነው ትውልድ ካሳ አይሆንም። እንዲሁም መድህን ነው  ብዬ አላስብም። ቋሚ የሆነ ዛሬን ለነገ በጽናት ሊያበቅልል የሚችል ተከተታይነት  ያለው የተግባር ስንቅ ያስፈልጋል። እንደ አንድ አገር መሪ የተግባር ትልም እና  ክንውን። ጊዚያዊ ደስታ ፈጥሮ የማይተን የማይበን። ጤዛም ጎርፍም ያልሆነ። ዛሬን የሚያኖር  ነገን የሚተከል፤ ከነገወዲያን የሚያበቅል ልባም ተግባር ያስፈልጋል። አንዲት ሻማ  ስትበራ ብርሃኗ ለብዙ ትደርሳለች ስትጠፋ ግን ያው መልሶ ድቅድቅ ይሆናል።  እኔ ብዙም በጠንካራ ጎኖች ላይ ማተኮሩ የሚበቃ ይመስለኛል። ውዳሴውም  ይበቃል ባጀንበት። ይልቁንም ትኩረት ባጡ ወይንም ትኩረትን አቅምን ወደፊት  ሊሻሙ በሚችሉ ውጥን መሰናክሎ...