ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 14, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ህም። #እምም። #የፈንጅ እና #የቦንብ አደጋ የሙዚቃ ኮንሰርት አይደለም። #ማን #ይፈጽመው ማን??

ምስል
  #ህም ። #እምም ። #የፈንጅ እና #የቦንብ አደጋ የሙዚቃ ኮንሰርት አይደለም። #ማን #ይፈጽመው ማን??   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"         ማህበረ ቅንነት እንዴት አድራችሁ፦ አርፍዳችሁ ዋላችሁ።   ትንሽ ቆራጣ ነገር ልል ወደድኩኝ። #የፈንጂ ፤ #የቦንብ #ፍንዳታ ምኑ ያስፈነድቃል። ይህ ካስፈነደቀ የትኛውም ዓይነት የሰማይ በረራ፤ የምድር ጉዞ በሚደርስ ድንገተኛ አደጋ የፌስታ ኢቬንት ቤተኛ መሆን ማለት ነው። እንዴት ብሎ ነው በጦርነት ማህል፤ በግጭት መሃል፤ የእሳት አደጋ፤ የፈንጅ አደጋ ድንገተኛ አስደንጋጭ ክስተቶች የሰውን ልጅ #ሲቀጥፍ ፤ የነዋሪውንም የአለምንም መኖር ሲያውክ፤ መኖር ሲስተጓጎል የህዝብ የኗሪው #የተረጋጋ መንፈሳቸውን ሲዘርፍ "ወሸኔ፤ ማለፊያ" ዜና የሚሆነው።    ምነው ሰውነታችን ከላያችን ላይ እንዲህ #እንዲፋቅ ፈቀድን? ማን ይሁን ማን ይፈጽመው// በዬትኛውም አግባብ ይፈጸም፦ ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሃን መንገድ ላይ መቅረትን የሚነግር መርዶ #ፖለቲካ ተብሎ ሊቀርብ ፈጽሞ አይገባም። እራሱ የፈንጂ የቦንብ አደጋ ሞት ብቻ አይደለም። ዘመቻው #አካል #ይጎድላል ፤ ጦሪ የነበረው ተጧሪ ይሆናል። ስቃዩ፤ የሞራል ድቀቱ፤ የተስፋ ማጣት ስቃዩ #ተመን ይወጣለታልን????    ልጆችስ ተብትነው ሲቀሩ፤ ሰርክ #በስጋት ሲናጡ ይህ እንደ ሸበላ ገጠመኝ ሊታይ ይሆን? አዝናለሁኝ። በየትኛውም ሁኔታ የምናጣቸው ወገኖች ሃዘን አይበቃንም? ከእስር ቤት በድብደባ፤ ከሥራ መልስ በባሩድ፤ ያልተነገረው በስውር #በምግብ #ብክለት ፤ ስንት ወገን አጣን? ባልተገባ የመረጃ ፍሰት፤ ባልተጠና እና አቅምን ባልመጠነ #ኦፕሬሽን ቀንበጦቻችን አላጣነም። ...