ልጥፎች

ከኦገስት 18, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ምነው ህጋችን ላላ ልጄን አልቀበርኳትም ብዙ የምናገረው አለኝ የሄቨን አባት | Yegna tv | EBS Mezna...

ምስል

የቀድሞዋ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ደስታ ጥላሁን አነጋጋሪ ሃሳብ ሰነዘሩ! | አርትስ ወቅታዊ @ArtsTvWorld

ምስል

#እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።

ምስል
  #እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።   "አቤቱ እንደበደላችን ሳይሆን  እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን። አሜን።"     እንዴት አደርን? መንጋት አይቀርም ነግቷል። አሰቃቂነት፤ ፀያፍነትም ስንቃችን መሆኑ እንደምን እያደረገን ይሆን? በዚህ 6 ዓመት በይፋዊ፤ በአደባባይ የሚታዩ አረማዊነት ከዬትኛው ዘመን፦ ከዬትኛው አገር ሥርዓተ - መንግሥት ጋር አኽቲ እንደሚያደርገን አላውቀውም። በዘመነ ህወሃት፤ እዛ በቀደሙት ሥርዓቶችም መሰል ጭካኔወች በሃፍረት ካሊም ተጎናጽፈው ተከውነው ሊሆኑ ይችላሉ። የዚህ ዘመን የሚገርመው አስደንጋጭ እና ሰቅጣጭ ሁነቶች #የኦክስጅን ያህል ለሰውነታችን ተዋህጂ መሆኑ ነው።   መደበኛ ዜና ዘጋቢወች ወይንም ተንታኞች " #ሰበርን " መለያቸው #ሎጓቸው ሲያደርጉት ስንት የሰውነት ኦርጋን፤ ስንት ነርብ እንደሚበጣጥስ አይረዱት ሆነው ነው ለማለት አልችልም። ምክንያቱም በሰለጠነ ዘመን ተቀምጦ፤ በሰለጠነ አገር እዬኖሩ #ስጋትን ሎጎ ማድረግ እርስ በእርሱ የሚቃረን ስለመሆኑ ያጡታል ብዬ ስለማላስብ። #የደስታ #ሰበር እንኳን አደጋ አለው እንኳንስ የሃዘን።    ስንቃቸው ይህ የሆኑ ሰብዕናወች ስንቶችን ለሥነ ልቦና ህመም፤ ለልብ ምት መጨመር ወይንም ማቆልቆል፤ ወይንም ለደም ግፊት መጨመር እንደዳረጉ ቢያውቁት። ሰው ሆኖ ለሰው ልጅ ጤንነት አለማሰብ ጨካኝነትም ነው ለእኔ። እኔ በሕይወቴ የመልካም ነገር ሰርፕራይዝ የሚባል ነገር አልወድም፦ እንኳንስ የክፋ ነገር ሰርፕራይዝ። ዕንባዬ ፈቃዴን ሳይጠይቅ ነው የሚወርደው።    ውህድ እዬሆነ የመጣው የስጋት ነጋሪት፤ ጭካኔውንንም እኛኑ እያደረገ አቅርቦልናል። መገለጫችን፤ መለያችን ጭካኔ??? ተከድነው፤ ተንተክትከው፤ በውስጥ ታምቀው ግን ውስጥን አኮማትረው፤ ተስፋን

ፍረዱት።

ምስል
 

ብዙ የማትታወቀው የክርስቲያኖች ሀገር ገባሁ

ምስል