#እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።

 

#እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።
 
"አቤቱ እንደበደላችን ሳይሆን
 እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን። አሜን።"
 
 
እንዴት አደርን? መንጋት አይቀርም ነግቷል። አሰቃቂነት፤ ፀያፍነትም ስንቃችን መሆኑ እንደምን እያደረገን ይሆን? በዚህ 6 ዓመት በይፋዊ፤ በአደባባይ የሚታዩ አረማዊነት ከዬትኛው ዘመን፦ ከዬትኛው አገር ሥርዓተ - መንግሥት ጋር አኽቲ እንደሚያደርገን አላውቀውም። በዘመነ ህወሃት፤ እዛ በቀደሙት ሥርዓቶችም መሰል ጭካኔወች በሃፍረት ካሊም ተጎናጽፈው ተከውነው ሊሆኑ ይችላሉ። የዚህ ዘመን የሚገርመው አስደንጋጭ እና ሰቅጣጭ ሁነቶች #የኦክስጅን ያህል ለሰውነታችን ተዋህጂ መሆኑ ነው።
 
መደበኛ ዜና ዘጋቢወች ወይንም ተንታኞች " #ሰበርን " መለያቸው #ሎጓቸው ሲያደርጉት ስንት የሰውነት ኦርጋን፤ ስንት ነርብ እንደሚበጣጥስ አይረዱት ሆነው ነው ለማለት አልችልም። ምክንያቱም በሰለጠነ ዘመን ተቀምጦ፤ በሰለጠነ አገር እዬኖሩ #ስጋትን ሎጎ ማድረግ እርስ በእርሱ የሚቃረን ስለመሆኑ ያጡታል ብዬ ስለማላስብ።
#የደስታ #ሰበር እንኳን አደጋ አለው እንኳንስ የሃዘን።
 
 ስንቃቸው ይህ የሆኑ ሰብዕናወች ስንቶችን ለሥነ ልቦና ህመም፤ ለልብ ምት መጨመር ወይንም ማቆልቆል፤ ወይንም ለደም ግፊት መጨመር እንደዳረጉ ቢያውቁት። ሰው ሆኖ ለሰው ልጅ ጤንነት አለማሰብ ጨካኝነትም ነው ለእኔ። እኔ በሕይወቴ የመልካም ነገር ሰርፕራይዝ የሚባል ነገር አልወድም፦ እንኳንስ የክፋ ነገር ሰርፕራይዝ። ዕንባዬ ፈቃዴን ሳይጠይቅ ነው የሚወርደው። 
 
ውህድ እዬሆነ የመጣው የስጋት ነጋሪት፤ ጭካኔውንንም እኛኑ እያደረገ አቅርቦልናል። መገለጫችን፤ መለያችን ጭካኔ??? ተከድነው፤ ተንተክትከው፤ በውስጥ ታምቀው ግን ውስጥን አኮማትረው፤ ተስፋን አበልዘው የቀሩ ገጠመኞች ከፈጣሪ ጋር በተጣልንበት ዘመን ሁሉ ይኖራሉ። በጣም በቀደሙ ዘመኖችም በታሪክ የሚሰሙ አሰቃቂ ድርጊቶች እንደነበሩ ሰምተናል፤ አንብበናል። 
 
እንደዚህ ዘመን ግን #አረማዊነት፤ መጨካከን፤ #እንሰሳዊ ዝንባሌ ቀን ሰጥቶት ታይቶ የሚታወቅ አይመስለኝም።
 
#የት ይድረሱ ህፃናቱ?
#የት ብን ብለው ይጥፋ ምንዱባን ኢትዮጵውያን ህፃናት?
#እንደምን ይናፍቁት መወለዳቸውን ጽንሶችስ?
#ጋብቻ እራሱ እኮ ቀራኒወ ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው ስደት ላይ ናቸው። ለምን?
 
"አልወለድም።" የታላቁ ፀሐፊ አቤ ጉበኛ ትንቢት ኮተት እያለ እዬደረሰ እኮ ነው። አዬሩ በጭካኔ ተበከለ። እኛም እራሳችን በጭካኔ አዬር ተከበብን። እኛነታችን ማጣታችን እኛነታችን ስለመፍሰሱ ይተረጉምልናል። መንግሥት ባለበት አገር ሰከንዷ እንዲህ ምጥ ስትሆን ለገ እንደምን ማግሥት ይታለም?
 
ለዚህ ነው እኔ እኛ የእኛ ስለኛ ለመሆን ስለተሳነን ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ተፈጥሯዋ የምትመለስበት መንፈስ ብቻ መዳኛችን ነው የምለው። እኔ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅትም ያስፈልጋታል ብዬ አላምንም። ካለ አባቱ ዶሮ ባጓቱ ሆኖባታል። ፖለቲከኞች አላወቁበትም። ስኬቱ ጭካኔ፤ ትርፋ ዕንባ እና ዋይታ ነው ዬሆነው።
 
ኢትዮጵያ #አጽናኝ #አይዟችሁ የሚል ቲም ያስፈልጋታል እምለውም ለዚህ ነው። የሚያስደነግጠውም፤ የሚያስፈራውም፤ የሚያሰጋውም ነገር ለሁላችን እኩል ሊሰማን አልቻለም። እንዲያውም ለፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ መሳ ለመሳ የበደሎች ልኬታ ሲፎካከሩ እመለከታለሁኝ። ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ለህፃናት አለማሰብ፤ ለህፃናት አለማዘን ጨለማነት ነው። 
 
በጣም ለረጅም ጊዜ ዩኒሴፍን የመሰለ የህፃናት መብት አስከባሪ ተቋም እንዲመሰረት የአማራ ህፃናት እንደዛ ሲያልቁ፤ ወላጅ አልባ ሲሆኑ ለፀሐፊ መስከረም አበራ ፕሮፖዛሉን ሁሉ አቅርቤላት ነበር። አቅሙም ስላላት። የእሷም ልጆች እንዲህ አይሰቃዩም ነበር። ግን ማን ያደምጠኛል?? ያው እሷ ወደ ሚዲያው አዘነበለች። ያን ጀምራ ቢሆን የበለጠ አቅሟ ግሎባል የመሆን ዕድል ነበረው የዚህ ሁሉ ስቃይ ሰለባም ላትሆን ትችል ነበር። አዲስ ማንነት ስለሚፈጥር።
 
……… ? በዚህ - ሁኔታ ነገ እንደምን ይጠበቅ?
……… ? ዛሬስ - እንደምን ተውሎ ይታደር?
…………? ከነገ - በስቲያስ ምን ይመጣ ይሆን?
 
በውግዘቱ የምንታደም ወገኖች የጠራ ንፁህ ሰብዕናን አምጦ ለመውለድ ምን ዝግጅት አለን???? እንችላለን??? እራስን መግዛት ማረም መገሰጽ ትልቁ ጋዳ ጉዳይ ነው? ውስጣችን እዬተናደ ነው። እዬፈረሰም። ግን ለምን እራስን ማዳን ተሳነን? ለምን????
ለዛች መከረኛ እናት የዕድሜ ልክ ሃዘን ነውና እግዚአብሄር አምላክ ጽናት መቀነቱን ይስጥልን። አሜን። 
 
የግፋ ግፍ ደግሞ እናት ሃዘን መሸከሟ ላይበቃ ሌላ ተጨማሪ ጫና ስጋት እንዲታከልባት መደረጉ ነው። አይዞሽ ልትባል፤ የሥነ ልቦና እገዛ ሊደረግላት ሲገባ፤ በቂ ጥበቃ ሊደረግላት ሲገባ ዛቻ??? ለነገሩአቅመ ቢስ ከሆነ ሥርዓት ከአናርኪ ውጭ ምን ሊታሰብ ይችላል? 
 
የውነት ክፍትፍት ብሎኛል። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/08/024
ሰው ለመሆን ያብቃን። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።