ልጥፎች

ከሜይ 27, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስትለጥፋ አክሰሱ ያላቸውን ታዳጊወች እያሰባችሁ ይሁን።

  እባካችሁን ለሙሉ ዕድሜ ላለነው እጅግ #የሚሰቀጥጡ ፖስተሮችን ስትለጥፋ አክሰሱ ያላቸውን ታዳጊወች እያሰባችሁ ይሁን። ፍርኃት አብሯቸው እንዲያድግ መፍቀድ ነው። ይህ ደግሞ የሥነ - ልቦና ዝበትን ያመጣል። ኃላፊነት ሊሰማን ይገባል በዬምንተጋበት ዓውድ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/26

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታመሰው #የማንነት #ቀውስ ባለባቸው ሰወች ነው።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታመሰው #የማንነት #ቀውስ ባለባቸው ሰወች ነው። እራሱ በፖለቲካ ምልከታው የማንነት ቀውስ አለው፤ በዞግም ማንነት ቀውስ ያለባቸው አሉ። እርግጥ ለመሆን #ስስ ነገር ከኖረ። ሌላው እራስን ለመግለጽ የኮንፊደንስ ቀውስም ያለባቸው አሉ። ይህን ሁሉ ጓዝ ተሸክሞ ምኞቱን የማይመጥን ህልም ይያዝና በቃ መተራመስ፤ ማተራመስ። በኢህአዴግ ዘመን ብአዴን፦ ደህዴን፥ ኦህዴድ አንድ ሰው እንዲህ ይገላበጥ ነበር። ከብአዴን፦ ህወሃት፦ ከህወሃት ብአዴን፤ ከብአዴን ብልጽግናም አለ። ያ ሰው የፖለቲካ ተንታኝ ወይንም ጋዜጠኛ ወይንም ሞደሬተር ሆኖ ሲመጣ ከእነጓዙ ነው። ይህ ነው ህመሟ የእማማ። ሥርጉ2024/05/25 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

#መሪነት።

  #መሪነት ። ገጣሚነት ብቻውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ፀሀፊነትም ተማላውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ተዋናይነት ቢሆን፤ ጋዜጠኝነትም ቢሆን የመሪነት አቅምን ሊያጎናጽፍ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትነት፤ የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁርነትም መሪ ሊያደርግ ብቻውን አይችልም። መፈለግም መመኜትም መብት ነው። መብቱ ብቻውን ግን የመሪነት ክህሎትን አያጎናጽፍም። ተጽዕኖ ፈጣሪነትም የመሪነት አቅምን አያጎናጽፍም። መሪነት #ቅባዐ ነው። መሪነት መክሊትም ነው። መሪነት መሰጠትም ነው። መሪነት ግልፅነት ነው። መሪነት ታማኝነት ነው። መሪነት #ቅንነት ነው። መሪነት #አወንታዊነትም ነው። መሪነት መረጋጋት ነው። መሪነት የውስጥ ሰላም #ስፍነትም ነው። መሪነት አድማጭነት ነው። መሪነት አብዝቶ መቀመጥን ይጠይቃል። መሪነት ተመክሮን ይሻል። ለመሪነት ልምድ ያስፈልጋል። መሪነት ወቅትን የሚመጥን ሐሳብ አፍላቂነትም ነው። መሪነት መታመንን ይጠይቃል። መሪነት በመንፈስ መደራጀትን ይጠይቃል። መሪነት የማደራጀት አቅምንም ይጠይቃል። መሪነት #ጥሞናን ይጠይቃል። መሪነት ሲዩት ግርማ ሞገሱ ድንግጥ ሊያደርግ ይገባል። መሪነት #አደብ ነው። አቅል የለሽ ሰብዕና ለመሪነት ግጥሙ አይደለም። መሪነት ወጥኖ ማጠናቀቅን ይጠይቃል። መሪነት ለውሳኔ አለመቸኮልን ይጠይቃል። መሪነት ሰብዓዊነትን ማስቀደምን ይጠይቃል። መሪነት ቲም ወርክም ነው። መሪነት ተተኪን ማፍራትን ይጠይቃል። መሪነት በስልጠናም ይገኛል። መሪነት ማስተዋልም ነው። መሪነት ወጥ ፍላጎትን ይጠይቃል። መሪነት የመቻል ጥበብ ነው። መሪነት ዳኝነትም ነው። ብቃት ኑሮም ተቀባይነት ላይኖሮ ይችላል። ይህን ፈቅዶ መቀበል ይገባል። መሪነት #ፍዝ ለሆኑ ሰብዕናወች አይሆንም። መሪነት ርቱዑ አንደበት ይጠይቃል፡ መሪነት ቆፍጣናነትንም ይጠይቃል። ንቁ መሆ

ስለምን???

 ስለምን??? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለምቾት የሚገነቧቸውን ፕሮጀክት መዋለ ንዋይ ስለምን ለዩንቨርስቲወች ድጎማ፤ ለሠራተኛ ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው አብይ ሠራሽ ክልሎች አይመድቡም። ደቡብ ደሞዝ መክፈል ካቃተው፤ ደቡብ ዩንቨርስቲወችን መመገብ ከተሳነው ዛሬ ደቡብ ሰላም ነው ነው የሚባለው ይደፈርሳል። የማይቆም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አመጽም ሊነሳ ይችላል። ዳቦ ለሚጠይቁም ቀለሃ ሊታዘዝባቸው ይችላል። ችግር ደርሶ ማኔጅ ለማድረግ ከሚያቅት በእጅ ባሉ ነገሮች ቢያንስ ችግሮችን ለማስታገስ ጥረት ለምን አይደረግም። የኮሪደር፤ የጫካ፤ የሪዞልት ወዘተ እያሉ በፈንታዚ ከሚጓጓዙ። ድግሱም እንዲሁ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል። የክልል አለቆችን በአጃቢነት ከማሰለፍ የፀጥታ ኃይሎች በቂ ናቸው ጉዞ ካስፈለገ። ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የፃፍኩት 2011 መግቢያ ላይ ነበር። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው። ቅን ለሆነ ህዝብ ቅንነት የነጠፈበት ፖለቲከኛ በምን ሂሳብ ሊደማመጥ ይችላል? አይመጣጠንማ! ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት። ግልፍተኝነቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ ሆኖ የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን እንደምን መያዝ እንደሚገባው እንኳን አያውቅም። ለዘርፋ ደም የሚያፈላ እርምጃ፤ ደም የሚያፈላ ንግግር ይደረጋል። ከዛ ፀጋ ይደፋል። ፀጋ ከተደፋ በኋላ ደግሞ ልምምጥ ይመጣል። አብሶ #ካድሬወቹ #በዲፕሎማሲ #ጉዳይ ላይ #እንዳይዘነቁሉ #በህግ #ሊታገዱ #ይገባል ። ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ደረጃ የማይመጥናት ላይ ናት። በሌላ በኩል #በዘርፋ #ሙያ #ጠገብ #ኢትዮጵያውያን #በነፃነት #እንዲሠሩ #ሊፈቀድ #ይገባል ። ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ አመጣሽ ሰብዕና ረቂቁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። ኢብን ሙሁራን ቢሆኑም። ኢትዮጵያ በትርፍ ተናጋሪወች ልትለካም አይገባም። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ ለሁላችን ከብዳናለች የምለው። ለአገር ክብር ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተቋም አለ። ውጭ ጉዳይ ሚር። የዳበረ ልምድ ያለው። በነፃነት ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለት። ከዞግ እሳቤ ተወጥቶ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/2

Liyu and me on various issues ...

ምስል

Zerihun and me on various Ethiopian issues ተክሌሻ የምሞግተው ሲጠፋ ደግሞ የሚናፍቀኝ ሰው ነው፨

ምስል