#መሪነት።

 

ገጣሚነት ብቻውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ፀሀፊነትም ተማላውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ተዋናይነት ቢሆን፤ ጋዜጠኝነትም ቢሆን የመሪነት አቅምን ሊያጎናጽፍ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትነት፤ የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁርነትም መሪ ሊያደርግ ብቻውን አይችልም። መፈለግም መመኜትም መብት ነው። መብቱ ብቻውን ግን የመሪነት ክህሎትን አያጎናጽፍም። ተጽዕኖ ፈጣሪነትም የመሪነት አቅምን አያጎናጽፍም። መሪነት #ቅባዐ ነው።
መሪነት መክሊትም ነው። መሪነት መሰጠትም ነው። መሪነት ግልፅነት ነው። መሪነት ታማኝነት ነው። መሪነት #ቅንነት ነው። መሪነት #አወንታዊነትም ነው። መሪነት መረጋጋት ነው። መሪነት የውስጥ ሰላም #ስፍነትም ነው። መሪነት አድማጭነት ነው። መሪነት አብዝቶ መቀመጥን ይጠይቃል። መሪነት ተመክሮን ይሻል። ለመሪነት ልምድ ያስፈልጋል። መሪነት ወቅትን የሚመጥን ሐሳብ አፍላቂነትም ነው።
መሪነት መታመንን ይጠይቃል። መሪነት በመንፈስ መደራጀትን ይጠይቃል። መሪነት የማደራጀት አቅምንም ይጠይቃል። መሪነት #ጥሞናን ይጠይቃል። መሪነት ሲዩት ግርማ ሞገሱ ድንግጥ ሊያደርግ ይገባል። መሪነት #አደብ ነው። አቅል የለሽ ሰብዕና ለመሪነት ግጥሙ አይደለም። መሪነት ወጥኖ ማጠናቀቅን ይጠይቃል። መሪነት ለውሳኔ አለመቸኮልን ይጠይቃል። መሪነት ሰብዓዊነትን ማስቀደምን ይጠይቃል። መሪነት ቲም ወርክም ነው። መሪነት ተተኪን ማፍራትን ይጠይቃል። መሪነት በስልጠናም ይገኛል። መሪነት ማስተዋልም ነው። መሪነት ወጥ ፍላጎትን ይጠይቃል። መሪነት የመቻል ጥበብ ነው። መሪነት ዳኝነትም ነው። ብቃት ኑሮም ተቀባይነት ላይኖሮ ይችላል። ይህን ፈቅዶ መቀበል ይገባል። መሪነት #ፍዝ ለሆኑ ሰብዕናወች አይሆንም። መሪነት ርቱዑ አንደበት ይጠይቃል፡ መሪነት ቆፍጣናነትንም ይጠይቃል። ንቁ መሆን አለበት ራሱን ለመሪነት ያጬ ሰብዕና።
ውዶች ደህና አምቩ። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።