ልጥፎች

ከኖቬምበር 28, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። 25.11.2020

  አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። አባ ቅንዬ የአማራ ህዝብ የዘመኑን ባህሬ በማንበብ የህሊናዊነት አድማሱን ሊያሰፋ ይገባል። ከሩትን ተግባር ወጥቶ ባለ እርስትነቱን በሉላዊ ህግጋት ማስከበር ግድ ይለዋል። ሰርክ የቹቻ እና የሰኔል መሰናዶ ሊሰለቸው ይገባል። ዘወትር ሊቃናቱ ተለይተው ለካቴና፣ ለባሩድ፣ ለካራ፣ ለሳንጃ፣ ለሜጫ፣ ለእሳት ሲዳረጉ ለምን ብሎ እራሱን ይፈትሽ አማራ! በቃኝን ለምርምር ያውል። በስተቀር የኩርድሽ ዕጣ ክፍሉ ይሆናል። ማንም እንዳይኖረው ነው ሊቃናቱ በረድፍ የተረሸኑት፣ ልቅምቅም ብለው አሁንም ለካቴና የተሸለሙት የትውልዱ ተስፋ ቀና እንዳይል፣ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ነው የታለመው። የሚከወነው። አለኝታ፣ ጋሻ እንዳይኖረው ማድረግ ሙሉ ፕሮጀክት ነው የአገዛዙ። ስለዚህም የአማራ ህዝብ በማስተዋል መራመድ፣ አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር፣ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር መምከር ይኖርበታል። ቂም፣ በቀል የፀነሰ ዕለት ከሰዋዊ ውርጅብኝ በላይ ሰማያዊ እሳት ይወርድበታል። ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ፈርኃ እግዚአብሔር፣ ፈርኃ አላህ መሆኑን ሆኖ በመገኘት፣ ማክበር፣ ማስከበር ይኖርበታል። ጥላቻ አመድ፣ ክሰል፣ ትቢያ ነው። እሱ አልተፈጠረበትም። እና ለሰከንድ እንዳያስጠጋው። በስተቀር ምርቃቱ ይነሳል። ሁላችንንም ያጠፋናል። መክሊታችን ይሰረዛል። ሰብዕነታችን ፍግ ይሆናል። አደራ። ከዚህ ባሻገር ባለው ተጋድሎ ቆርጦ ትግል ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ቀን እዬቆጠረ ፀረ አማራ፣ ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ ሰው አዬሩ ይጠራል። ሥራው የመዳህኒዓለም ነውና። ከሰብዕነት ተርታ ለጠፋት ፈጣሪ የንሥኃ ጊዜ ይስጣቸው። አሜን። እኛ የተሰጠንን መልካምነት ይዘን የሚጠሉን ክፋነትን ሰንቀው ቢጓዙ ችሎቱ የእዮር ነው። ካለ ካህሊ - ሥልጣናችን ዘው አንበል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። 25.11.2020 የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?

የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?    ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተው የሚማሩት ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት የዓለም መድህን የሆነ የምርምር ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊነት አናባቢም ተነባቢም ቅዱስ በረከት ነው። ኢትዮጵያዊነት ተዘርዝረው በማይዘለቁ ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ምጥን ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት በጉልት ገብያ አውጫጭኝ አልተመሰረተም። ኢትዮጵያዊነት በውስጥህ ከኖረ ክህደት፣ ዝቅጠት፣ ስላቅ፣ ዝንፈት፣ መስቃ፣ ትዕቢት፣ ፀረ ሰውነት አያሸንፋህም። ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሯዊነትም፤ ሰዋዊነትም ነው። ኢትዮጵያዊው ሰው ፀጋው ዝልቅ ነው። ተማረ አልተማረ። ሰማዩን አይቶ የአዬሩን ባህሬ ይነግርኃል። ዛፍ ቆርጦ ዕድሜውን ይነግርኃል፣ የሰውነት ዛላህን አይቶ ውስጥህን ያነበዋል። ያብራራዋል እንደ ዘመንኛው ራዲወሎጂ በለው። ኢትዮጵያዊነት መርኽም ነው። ኢትዮጵያዊነት መንገድም ነው። ኢትዮጵያዊነት በህግ አምላክነትም ነው። ህግ ነው። ኢትዮጵያዊነትን በውስጡ ለፈቀደ ብርኃን ነው። ከፍ ቢል ዝቅ ቢል መጥኖ በቁጥብነት መኖርን ያኗኑራል። ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ኃይሌ ላሪቦ ኢትዮጵያዊነትን "ረቂቅ ሚስጢር" ይሉታል። አባ ትሩጉም አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት አፈጣጠር ኦርጋኒክ" ነው ዬሚል ጥልቅ ፍልስፍና አለው። ውስጡን ላጠናው ዕውነት ነው። ይህን የሚሸከም መሪ ማግኜት ግን አልተቻለም። ለዚህ ነው የአፍሪካ አገር መሪዎች እዬተሸማቀቁ ያሉት። አፍረውብናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ኢትዮጵያዊነት ቅኔ ነው።