ልጥፎች

ከጁላይ 18, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሐይሌ ገብረስላሴ ከበቀለ ሞላ ሰረቀ || እነሱ ከሀይሌ ገብረስላሴ ሰረቁ || ምኑን?

ምስል

ፋኖን ወደ አንድ ዕዝ ማዕከል ማምጣት ይቻል ይሆን?

ምስል

ዕውነት #ጋራጅ #የለውም። #የአማራ #የማንነት #ተጋድሎ፦ 2) #የአማራን #የህልውና #ተጋድሎን ውስጥ ማድረግ ይገባል።

ምስል
  # ዕውነት #ጋራጅ #የለውም ።   #ጤና ይስጥልኝ።           እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት? #በርትታችሁ አደራችሁ? ትናንት ጦር ግንባሩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር። ካቴና ላይ ያሉ ወገኖቻችንም ይታወሱ። የተፈቱም ይኖራሉ።   መሬት ላይ ትክክለኛ ዘጋቢ ስለለ ነው። ቢፈቱም መልሰው ያስሯቸዋል። ልቀቁ ነው። እዬለቀቁላቸው ነው። በውነቱ ለእስረኛ #ሙግት ቀርቷል። እንደ ነውርም እዬታዬ ነው።   ሲያነክተን ውሎ በሚያድር የምጠዬፈው " #የሰበር ዜና" ቁምነገር የማሳት አቅሙ ልክ የለውም። የሰበር ዜና ሚዲያው ወዘተረፈ እንደ ሥልጣኔም የታዬ ይመስለኛል። ነርብን፤ ካርቲሌጅን የሚሰባብር ።   ብዙ ወገኖቻችን እንዳጣን ይሰማኛል። ብዙወቹ የእኔ ቅኔው ጎጃም ነበሩ። እስካሁን አልመጡም። እንጃ ኢንተርኔቱ ካልተሟላ አላውቅም።    ቸር ያሰማን። ቸር እንሁን። ቅንም እንሁን። ቢያንስ ለተጎዱ ወገኖቻችን #ስስ አንጀት ይኑረን። ትናንት ሙሉ ቀን ፌቡ የዋልኩት ህዳር ከታጠነ ወዳጆቼን አገኛለሁ በሚል ነበር።   #የገዘፈውን … ጣምራ የተጋድሎ አመክንዮ አንኳር አጀንዳ ይሁን። ማህንዲሱም፤ ፓስተሩም ስለተበራከተ እንጂ ብዙ እጅግ ጥንፍ ተጋድሎ አማራን ይጠብቀዋል። ዛሬ ይህ ከሆነ የዛሬ 15/20 ዓመት ይታሰብ። እኔ ብቻም ነኝ የትግሉ ዘርፍ በዚህ መልኩ የማቀርበው።    1) #የአማራ #የማንነት #ተጋድሎ ፦ 2) #የአማራን #የህልውና #ተጋድሎን ውስጥ ማድረግ ይገባል። እያገረሸ የሚፈትነን የቀራንዮ ሥነ ስቅለት እያለብን በሰናፍጭ ጉዳይ አቅም አናባክን። ሊቃናቱ ይገናኛሉ። ማገዶነታችን በልክ ይሁን። ሁሉም ጥሞና ቢወስድ መልካም ይመስለኛል።    "የቤትህ ቅናት በላኝ። "   ሸበላ ቀን። ኑሩልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 2024

ታላቁ ተልዕኮው።

  መ ሪነት # አቅም # መፍጠር ነው ታላቁ ተልዕኮው። የ ፈጠረውን አቅምም በቅጡ ለ መምራት የራሱን የ ምምራት # አቅም ፦ # ክህሎት ማሰልጠንም ይገባዋል።   ይ ህን አዋዶ ህዝብ ጠቀም ማድረግም ሌላው የመሪነት የ ጥበብ ዘይቤ ነው። ሥርጉትሻ 2024/07/17

ዋ! #መራዊ ስለአንቺስ?

ምስል
  ዋ! #መራዊ ስለአንቺስ?   ስንት ሰው ነው #የተጎሳቆለው ? ስንቶችንስ #አጣን ? ስንቶቹ #ለካቴና ተሰጡ? ስንቶች #ተሰደዱ ? ስንት የመኖር ዓይነት #ተስተጓጎለ ? ስንቶች ከባዕታቸው #ተነቀሉ ? አሁን ለዓመት የተለያዬ በናፍቆት የሚገናኝበት ጊዜ በሆነ ነበር። ስለአጣናቸውም ዝክረ -መስዋዕትነት ልናደርግ ይገባ ነበር። የሃዘን ቀን ሊኖረን በተገባ።  አቅም ያለውም የተጎዱትን በጎጥ፤ በመንደር ሳይሸነሸን ተጠንቶ የሚችሉ እንዲረዷቸው ዳታ ማጠናቀር ይገባ ነበር። ያ ግራጫማ ወቅት፤ ያ #ደመመን የተጫነው #ጨጎጎት ወቅትን ለተቋቋመው ህዝባችን ብሩህ ተስፋ እንዲሰንቅ ማድረግ በተገባ ነበር።  በድንጋጤ አደጋ ላይ የባጁ ወገኖችም አሉን። የአባቶቻችን ዊዝደም የተሰጠው ባለ ቅባዕ ቢገኝ ዛሬ የሲቃ ቀን ነበር።  በመገናኘታችን ትንሽ እፎይ፤ ስለተለዩን ሃዘን፦ እንዲህ ከአንድ ፍጥጫ ወደ ሌላ ፍጥጫ ሽግግር የሚደረግበት ባልሆነ ነበር። የደብረ ኤልያስ ቅዱሳን ሰማዕትነትንስ፤ የመራዊን ሰቆቃ ዋይታስ በምን  ይካስ?????  ሥርጉትሻ2024/07/17

#ጊዜ #ይዳኛል።

  #ጊዜ #ይዳኛል ።    ለተመሳሳይ ዓላማ እና ፍላጎት እዬሠሩ የሚለያዩ ነገ ይገናኛሉ። ኢብን ፍላጎት እና ዓላማቸው የተለያዬ የሆነ እንኳን አብረው የሚሆኑበት አጋጣሚ ይፈጠራል።  አሁን በህልም ይሁን በዕውን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በአንድ መስመር ይሆናሉ ብሎ ማን ያስባል? ግን ሆኖ አዬን። ነገ ደግሞ ሊለያዩ ይችላሉ።  ስለዚህ #አቅማችሁን #አታባክኑ ። #ውስጣችሁን #አታቁስሉ ። ጊዜ ይዳኛል። መቼውንም #ከመርኽ እና #ከዕውነት ጋር ቁሙ። ጤና #የሚሰጠው ፦ #ጊዜም የሚቆጥበው ይኽው ነው።  መረጋገሙም ጥሩ አይደለም። ነገ እነሱ ይገናኛሉ። የኢትዮጵያ የፖለቲካን ባህሪ ከውስጡ አጥኑት። ልታደርጉት የሚገባው ቁምነገር የእኔ ለምትሉት #ድጋፋችሁን መቀጠል ነው። ዴሞክራሲ መርሁም ይኼው ነው። ሥርጉትሻ 024/07/17

"በቀኃሥ ዘመነ መንግስት ወቅት፤ የሠራዊቱ ልሳን በመሆን ያገለግል የነበረው ጋዜጣ ስሙ "ወታደርና ዓላማው" ይባል ነበር።

ምስል
  የከፍተኛ መኮንኖች ሹመት በዘመነ ቀኃሥ ዘመን!   Eyasu Eyasu     "በቀኃሥ ዘመነ መንግስት ወቅት፤ የሠራዊቱ ልሳን በመሆን ያገለግል የነበረው ጋዜጣ ስሙ "ወታደርና ዓላማው" ይባል ነበር።   ይህ ጋዜጣ በደርግ ዘመን ስሙ "ታጠቅ" በሚል ተቀይሮ እስከ ግንቦት 1983 ዓ.ም. ድረስ የሠራዊቱ ድምፅ በመሆን አገልግላል። እዚህ ጋዜጣ ላይ የምትመለከቷቸው የወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር አዛዥ መኮንኖች በግርማዊ ቀኃሥ ሹመቱ የተሠጣቸው፤ በ1954 ዓ.ም. ላይ የነበረ ሲሆን፤ ዜናው በወቅቱ "በልዕልት እቴጌ መነን" እና "የልዑል ሳህለሥላሤ" የሞት ሀዘን ምክንያት ዘግይቶ "በወታደርና አላማው" ጋዜጣ ላይ የወጣው ከአመት በኃላ ጥቅምት 24/1955 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ከሜጀር ጀነራል እስከ ኮሎኔል የማዕረግ እድገት ያገኙት የጦር መኮንኖች የሚከሉት ናቸው። 1. ሜ/ጀ እያሱ መንገሻ፤ 2. ሜ/ጀ ዋቅጅራ ሰርዳ፤ 3. ሜ/ጀ ወልደስላሴ በረካ፤ 4. ሜ/ጀ አማን ሚካኤል፤ 5. ብ/ጀ ጃገማ ኬሎ፤ 6. ሌ/ጀ ኢሳያስ ገ/ስላሴ፤ 7. ብ/ጀ አበበ ገመዳ፤ 8. ብ/ጀ ወልደዮሃንስ ተክሉ፤ 9. ብ/ጀ ሽፈራው ተሰማ፤ 10.ብ/ጀ አበበ ተፈሪ፤ 11.ብ/ጀ ኃይሌ ባይከዳኝ፤ 12.ብ/ጀ ወልደዮሐንስ ሽታ፤ 13.ብ/ጀ አበበ ወልደመስቀል፤ 14. ኮ/ል ይልማ ሺበሺ፤ መሆናቸው ጋዜጣው አስፍሯል። #enkssm "

ምራቅን መዋጥን ....

  ከተንከለከለ ፖለቲካ ጋር መንከልከል አይገባም። #ከሚንቦጀቦጅ ፖለቲካ ጋርም አብሮ #ማረግረግ ተገቢ አይመስለኝም።  ፖለቲካ ለሰው ነው። ለሰው የሆኑ አመክንዮወች ደግሞ ርጋታን ይጠይቃሉ። አመክንዮ በራሱ #ስኩን ነው።  የአመክንዮ ርጋታ ቢስ የለም። ለረጋ አምክንዮዊ ጉዞ የሰከነ፤ የረጋ፤ ለህግ የሚገዛ፤ አንደበቱ የታረመ ሰብዕና ይሻል። #አቅልየለሽ ፤ #አደብዬለሽ ሰብዕና ፖለቲካ ልኩ አይደለም። በፍፁም።  ፖለቲካ ሳይንስም ፍልስፍና ነው። ያ ደግሞ ምራቅን መዋጥን፦ መጨመትን፦ ከሌላው የተለዬ የማስተዋል ልኬታን ይጠይቃል። ፖለቲካ ከቅጽበታዊ ሰብዕና መዳፍ ከገባ ሲሰራ እና ሲፈርስ ውሎ ከማደር ሌላ ዕጣ ፈንታ የላውም። ችግሩ የመስዋዕትነቱ መግዘፍ እና እና #ኩርምትምት የሚለው የተስፋ ጉዞ አብሮ መታወኩ ነው። አይጣል ነው። ሥርጉ2024/07/17

#መሪነት

ምስል
  #ጤነኛ #መንፈስ #በገንዘብ አይገዛም። #ስክነትም #አይሸመትም ። #የተመረቁት ብቻ #ፀጋ ነው። ሥርጉትሻ 17/07/025   #ቅፅበታውያን የሚኖሩት ለህዝብ ሳይሆን፦ #ለበርጋጊው #ፋንታዚያቸው ነው። ሥርጉትሻ17/07/024   #መሪነት #ግርግር #አይደለም ! ሥርጉትሻ17/07/024